ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ፣ ቢቢሲ፣ አሶሼትድ ፕረስ እና ፍራንስ 24 የተሰኙ የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን በአራት ቀኖች ውስጥ ብቻ በኢትዮጵያ ላይ 72 የሀሰት ዜናዎችን መልቀቃቸው ታውቋል።
በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ የሚተላለፈው የ”ቴክቶክ” ፕሮግራም አዘጋጅ ሰለሞን ካሳ በትዊተር ገጹ ላይ ባሰፈረው መረጃ፤ ምዕራባዊያኑ መገናኛ ብዙኃን ሆን ብለው በህዝቡ ውስጥ ሽብር ለመፍጠር የሀሰት ዘገባዎችን በስፋት እያሰራጩ ናቸው ብሏል።
ዛሬም የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ በህይወት አለ ያለው ሰሎሞን፤ ከሰሞኑ የሚሰራጩት ሀሰተኛ ዘገባዎች ዋና አላማም አዲስ አበባ በሽብር ቡድኖች እንደተከበበች በማስመሰል ሽብር መንዛትና ሥነ ልቦናዊ አለመረጋጋት መፍጠር ነው ብሏል።
እሁድ እለት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ባደረጉት ሰልፍ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ላይ የሚያሰራጩትን የሀሰት ዘገባ በማውገዝ የተቃውሞ ድምጻቸውን ማሰማታቸው ይታወሳል። (ኢፕድ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply