• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኃይል ለማመንጨት የሚረዳ ግንባታ ሊጀመር ነው ተባለ

October 12, 2021 09:52 am by Editor Leave a Comment

የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኢነርጂ ከመሬት ውስጥ እንፋሎት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችል ፕሮጀክት ሲሆን፣ የሀይል ማመንጫ ግንባታውን ለማካሄድ መታቀዱን በቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኢነርጂ ድርጅት የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ነዚፍ ጀማል ገልጸዋል።

ነዚፍ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት ይህንን ግንባታ ለማካሄድ ጨረታ የወጣ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት የሀይል ማመንጫው ቁፋሮ ላይ የሚገኝ የግንባታ ሂደት ነው ብለዋል።

በፈረንጆች 2020 የወጣው የመጀመሪያ ጨረታ ሰባት ትልልቅ አለም አቀፍ የተርባይን አምራች ድርጅቶች መወዳደራቸውንና በአሁኑ ሰዓት ኹለት ድርጅቶች ስራውን ተቀብለው ለመስራት እየተጠባበቁ መሆናቸውን ነዚፍ ጠቁመዋል።

በአሁኑ ሰዓት ጨረታው ላይ በቀረበው የቴክኒክ ብቃት መሰረት ከሰባት ድርጅቶች ውስጥ ኹለት ብቻ የቀሩ ሲሆን፣ በዋናነት ግንባታውን የሚያካሂደው እና በተጠባባቂነት ያለው ድርጅት ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

ከእነዚህ ኹለቱ ድርጅቶች ጋር ለመፈራረም በድርድር ላይ መሆናቸውን የጠቆሙት ነዚፍ በቅርቡ አሸናፊውን ድርጅት ተለይቶ የሚታወቅ ይሆናል ብለዋል።

በፈረንጆቹ 2022 ስራውን ለመጀመር ያቀደው የሀይል ማመንጫው ግንባታ የስራውን ኮንትራት ውል በ2021 ለመጨረስ እቅድ መያዙን አስታውቀዋል።

የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ሃይል ለማመንጨት ይረዳል የተባለው ይህ ግንባታ፣ ከመሬት ውስጥ የሚገኘውን የእንፋሎት ሃይል ወደ ኤሌክትሪክ ሃይል በመቀየር ወደ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል መስመር ማስገባት የሚችል ነው።

ቱሉ ሞዬ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ጦሳ ወረዳ ኢተያ አካባቢ የሚገነባ ፕሮጀክት ሲሆን፣ በሀገሪቷ ያለ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት ከሚገነቡ ትልልቅ ግንባታዎች ውስጥ አንዱ ነው።

የጂኦተርማል ኢነርጂ ወደ ስራ ለማስገባት ከ10 ዓመት በላይ ጥናት የተካሄደበት ሲሆን፣ ከኹለት ዓመት በፊት ቁፋሮ በመጀመር ወደ ስራ የገባ የሀይል ማመንጫ ነው።

በፈረንጆች 2020 የተጀመረው የሀይል ማመንጫው የጉድጓድ ቁፋሮ በአሁኑ ሰዓት ኹለት ቁፋሮዎችን በማጠናቀቅ ሶስተኛው ጉድጓድ ቁፋሮ ተጀምሮ ኹለት ሺሕ ሜትር በላይ መሰራቱን ነዚፍ ጠቁመዋል።

የመጀመሪያው ቁፋሮ የተደረገበት እንፋሎት እየወጣ መሆኑንም ነዚፍ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

ይህን እንፋሎት ምን ያህል ማመንጨት እንደሚችል በውጭ ሀገራት ባለሙያዎች ተጠንቶ፣ መረጃዎች ተሰብስበው ውጤት እየተጠበቀ ይገኛል ብለዋል። ይህ ጉድጓድ ያመነጨው እንፋሎት ላይ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የሚረዳ ጥናት ሲሆን፣ ጥናቱ ላይ እንፋሎቱ ሳይቋረጥ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቀጥል፣ ስንት ሜጋዋት ኤሌክትሪክ ሊያመነጭ ይችላል የሚል ነው።

ለመጀመሪያው የሚጠናው ጥናት አጠቃላይ ለሚቆፈሩት ማመንጫ ሀይል መረጃ ለማግኘት ያስችላልም ተብሏል።

ቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል የመንገድ ግንባታ፣ የውሃ ቁፋሮ እና ሌሎች የድጋፍ ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን ከ150 በላይ የስራ እድል የፈጠረ ድርጅት ነው።

ተቋሙ እንደ ድርጅት የተቋቋመው በፈረንጆቹ ታህሳስ 2017 ሲሆን፣ ሳይንሳዊው ጥናት መካሄድ ከጀመረ አስር ዓመታት አስቆጥሯል።

የቱሉ ሞዬ ሃይል ማመንጫ ለመገንባት 850 ሚሊየን ዶላር የሚፈጅ ሲሆን፣ በእንፋሎት ሃይል ማመንጨት የሚያስችሉ 12 ቁፋሮዎች የሚያካሄድበት ነው።

ቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል የሃይል ማመንጫ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል የከርሰ ምድርን እንፋሎት በመጠቀም ሀይል የሚያመነጭ ድርጅት ሲሆን፣ በ2017 ሀይል ለማመንጨት እና ለሀገር ወስጥ ጥቅም ለማዋል እቅድ ይዞ በመስራት ላይ ይገኛል።

የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኃይል ጣቢያ፣ በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለ 150 ሜጋ ዋት ማመንጨት የሚችል ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ ተገንብቶ ወደ ስራ ሲገባ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ በታቀደው በሁለተኛው ምዕራፍ ወደ 150 ሜጋ ዋት እንዲያመነጭ አቅሙን ለማስፋፋት ያስችላል ተብሏል። (ለአዲስ ማለዳ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: geothermal, tulu moye

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule