“የኢትዮጵያ ችግር የዕርዳታ ስንዴ ነው” October 15, 2021 05:04 pm by Editor 1 Comment Share on FacebookTweetFollow us
Tesfa says October 18, 2021 01:38 pm at 1:38 pm የቢቢሲ ኦንላይነ ዜና የቀኑን የፈጠራ ዜናውን ሲያናፍስ የኢትዮጵያው መሪ የእርዳታ እህልን እንደ ጦር ሊጠቀምበት ነው ይላል። ጠ/ሚሩ ራሳችን ስለመቻል ነበር የተናገሩት። ሌሎች ደግሞ እንዴት ሃገሪቱ ጦርነት ላይ እያለች ማሳ ጉብኝት ይሄዳል በማለት ይወርፋሉ። እንዝፈን ሲሉ የሚያለቅ፤ እናልቅስ ሲሉት የሚዘፍን የደነዘዘ ትውልድ የኢትዮጵያ ችግር የእርዳታ ምግብ መሆኑን መረዳት ይከብደው ይሆናል። የጠ/ሚሩ አባባል ግን ሃቅ ነው። የስንት ሃገሮች ሃገር በቀል የእህል ዝሪያ በመጤው ተውጦ ቀርቷል። ስንቶች ናቸው ይህን ካልታዘዛችሁ እህል አንሰጥም የተባሉት? ሁቱና ቱትሲ በሩዋንዳ ሲተላለቁ ምንም አያገባንም በማለት ቆመው የተመለከቱት የነጭ ወታደሮች አፋቸውን ሞልተው ጥቁር በጥቁር ላይ ስላለው ጭካኔ ያወራሉ። ግን እንዲህ ያለ ከሰው ባህሪ ውጭ የሆነ ጭካኔን እንዲያረጉ መንገድ የከፈተላቸው ራሱ ነጩ ህዝብ ነው። ከአውራ ጣት አመልካች ጣት ትበልጣለች እያሉ አንድ ከሌላው ጋር እንዲላተም በማድረግ። ነገሩ ሲከፋ ደግሞ የዜና አውታሮችን በማምጣት የአለም ህዝብ የእኛን ገመና እያየ ከንፈሩን እንዲመጥና ብሎም የእርዳታው ስንዴ ሲሰፈርለት ሃገራቸው የእርዳታ እጇን መዘርጋቷን ሲመለከቱ የፓለቲካ አሻሮአቸውን ቅመው እርፍ ይላሉ። ውስጠ ሚስጢሩን ግን የሚረዳ የለም። ለዚያ ነው እኛም እነርሱ በያዙልኝ ጅራፍ እየተነዳን ሃገር የምናፈርሰው፤ የምንገዳደለው አልፎ ተርፎም በዘርና በቋንቋ ተጠልለን ሰላቢዎችን የሆነው። የነቃ የበቃ አርቆ የሚያስብ ጭንቅላት ያለው ማንም ቢሆን የዘር ፓለቲካ የቆሻሻ ክምር መሆኑ ሊገባው ይገባል። ግን የውስልትናው ፓለቲካ የነጻነት ጮራ አስመስሎ ጽልመት ሲያለብሰው ሰው የክልል ባንዲራ ይዞ በጅምላ አስተሳሰብ አብሮ ይነጉዳል። አሁን እንሆ ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር መባሉ ምን ያህል ወያኔ እየገፋ እንደመጣ ያመላክታል። አዲስ አበባ ላይ ተቀምጦ ዲስኩር መደስኮርና መለኮታዊ ሃይልን መማጸን ቅድመ አያቶቻችን በጣሊያ የጋዝ ጭስ ከመታፈን አላዳናቸውም። መቀሌ ላይ ቁጭ ብለው እየመከሩና እየዘከሩ ጦርነቱን አፋር ምድር አድርሰውት ዝም ብሎ መመልከት መደንዘዝ ነው። የሚፎክሩት መሪዎቻቸው የት ናቸው? እነርሱ ታድነው እንዲገደሉ ወይም እንዲያዙ የሚከለክለው ህግ የቱ ነው? ይመስለኛል ሰራዊቱ እዚህም እዚያም የያዛቸውን ስፍራዎች እየለቀቀ አንዴ የፓለቲካ ውሳኔ ነው ስንባል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ታክቲካዊ ማፈግፈግ ነው ሲሉን አዲስ አበባ ሲደርሱ ምን ሊሉን ፈልገው ይሆን? ግራ የሚያጋባ ነገር ነው እየሆነ ያለው። ይህ ጦርነት በረዘመ ቁጥር ህዝባችን አሁን ካለው በባሰ ሁኔታ ይራባል፤ ይፈናቀላል፤ ይሰደዳል፤ ይሞታል። አሁንም በቋፍ ላይ ያለ ህዝብ ነው። ኑሮ ጣራ ላይ ደርሷል። በጦርነቱ ቦታዎች ሰው የሚበላው የለም። ይህ መንግስ ነኝ ለሚለው የውድቀት ዋዜማ ይመስላል። የስንዴ ማሳው ማለፊያ ነው። ግን የኦሮሞ ጽንፈኞች እንደ ሽዋው የጤፍ ክምር እሳት እንዳሰድበት ጥንቃቄ ይደረግ። ጠ/ሚሩም ለምን የማሳ ጉብኝት አረጉ ብሎ የሚያጉረመርም ያው እሳቸውንም እንደ ስብሃት ነጋ እስረኛ ለማድረግ የፈለጉ ብቻ ናቸው። እየተዋጉም/እያዋጉም/እያቀድም/የተጀመሩ ፕሮጄክቶችንና የሰብል ማሳዎችን መጎብኘት ይቻላል። ችግሩ እሱ አይደለም። ችግሩ መቼ ነው የሰሜኑ ጦርነት የሚያከትመው ነው። በጻድቃንና በጌታቸው ረዳ ስሌት በሳምንታት ውስጥ ነው። ጠብቀን እናያለን። በቃኝ! Reply
የቢቢሲ ኦንላይነ ዜና የቀኑን የፈጠራ ዜናውን ሲያናፍስ የኢትዮጵያው መሪ የእርዳታ እህልን እንደ ጦር ሊጠቀምበት ነው ይላል። ጠ/ሚሩ ራሳችን ስለመቻል ነበር የተናገሩት። ሌሎች ደግሞ እንዴት ሃገሪቱ ጦርነት ላይ እያለች ማሳ ጉብኝት ይሄዳል በማለት ይወርፋሉ። እንዝፈን ሲሉ የሚያለቅ፤ እናልቅስ ሲሉት የሚዘፍን የደነዘዘ ትውልድ የኢትዮጵያ ችግር የእርዳታ ምግብ መሆኑን መረዳት ይከብደው ይሆናል። የጠ/ሚሩ አባባል ግን ሃቅ ነው። የስንት ሃገሮች ሃገር በቀል የእህል ዝሪያ በመጤው ተውጦ ቀርቷል። ስንቶች ናቸው ይህን ካልታዘዛችሁ እህል አንሰጥም የተባሉት? ሁቱና ቱትሲ በሩዋንዳ ሲተላለቁ ምንም አያገባንም በማለት ቆመው የተመለከቱት የነጭ ወታደሮች አፋቸውን ሞልተው ጥቁር በጥቁር ላይ ስላለው ጭካኔ ያወራሉ። ግን እንዲህ ያለ ከሰው ባህሪ ውጭ የሆነ ጭካኔን እንዲያረጉ መንገድ የከፈተላቸው ራሱ ነጩ ህዝብ ነው። ከአውራ ጣት አመልካች ጣት ትበልጣለች እያሉ አንድ ከሌላው ጋር እንዲላተም በማድረግ። ነገሩ ሲከፋ ደግሞ የዜና አውታሮችን በማምጣት የአለም ህዝብ የእኛን ገመና እያየ ከንፈሩን እንዲመጥና ብሎም የእርዳታው ስንዴ ሲሰፈርለት ሃገራቸው የእርዳታ እጇን መዘርጋቷን ሲመለከቱ የፓለቲካ አሻሮአቸውን ቅመው እርፍ ይላሉ። ውስጠ ሚስጢሩን ግን የሚረዳ የለም። ለዚያ ነው እኛም እነርሱ በያዙልኝ ጅራፍ እየተነዳን ሃገር የምናፈርሰው፤ የምንገዳደለው አልፎ ተርፎም በዘርና በቋንቋ ተጠልለን ሰላቢዎችን የሆነው። የነቃ የበቃ አርቆ የሚያስብ ጭንቅላት ያለው ማንም ቢሆን የዘር ፓለቲካ የቆሻሻ ክምር መሆኑ ሊገባው ይገባል። ግን የውስልትናው ፓለቲካ የነጻነት ጮራ አስመስሎ ጽልመት ሲያለብሰው ሰው የክልል ባንዲራ ይዞ በጅምላ አስተሳሰብ አብሮ ይነጉዳል።
አሁን እንሆ ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር መባሉ ምን ያህል ወያኔ እየገፋ እንደመጣ ያመላክታል። አዲስ አበባ ላይ ተቀምጦ ዲስኩር መደስኮርና መለኮታዊ ሃይልን መማጸን ቅድመ አያቶቻችን በጣሊያ የጋዝ ጭስ ከመታፈን አላዳናቸውም። መቀሌ ላይ ቁጭ ብለው እየመከሩና እየዘከሩ ጦርነቱን አፋር ምድር አድርሰውት ዝም ብሎ መመልከት መደንዘዝ ነው። የሚፎክሩት መሪዎቻቸው የት ናቸው? እነርሱ ታድነው እንዲገደሉ ወይም እንዲያዙ የሚከለክለው ህግ የቱ ነው? ይመስለኛል ሰራዊቱ እዚህም እዚያም የያዛቸውን ስፍራዎች እየለቀቀ አንዴ የፓለቲካ ውሳኔ ነው ስንባል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ታክቲካዊ ማፈግፈግ ነው ሲሉን አዲስ አበባ ሲደርሱ ምን ሊሉን ፈልገው ይሆን? ግራ የሚያጋባ ነገር ነው እየሆነ ያለው። ይህ ጦርነት በረዘመ ቁጥር ህዝባችን አሁን ካለው በባሰ ሁኔታ ይራባል፤ ይፈናቀላል፤ ይሰደዳል፤ ይሞታል። አሁንም በቋፍ ላይ ያለ ህዝብ ነው። ኑሮ ጣራ ላይ ደርሷል። በጦርነቱ ቦታዎች ሰው የሚበላው የለም። ይህ መንግስ ነኝ ለሚለው የውድቀት ዋዜማ ይመስላል። የስንዴ ማሳው ማለፊያ ነው። ግን የኦሮሞ ጽንፈኞች እንደ ሽዋው የጤፍ ክምር እሳት እንዳሰድበት ጥንቃቄ ይደረግ። ጠ/ሚሩም ለምን የማሳ ጉብኝት አረጉ ብሎ የሚያጉረመርም ያው እሳቸውንም እንደ ስብሃት ነጋ እስረኛ ለማድረግ የፈለጉ ብቻ ናቸው። እየተዋጉም/እያዋጉም/እያቀድም/የተጀመሩ ፕሮጄክቶችንና የሰብል ማሳዎችን መጎብኘት ይቻላል። ችግሩ እሱ አይደለም። ችግሩ መቼ ነው የሰሜኑ ጦርነት የሚያከትመው ነው። በጻድቃንና በጌታቸው ረዳ ስሌት በሳምንታት ውስጥ ነው። ጠብቀን እናያለን። በቃኝ!