
አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የዛሪማ መስጊድን በከባድ መሳሪያ ደብድቦ ማውደሙን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አረጋ ገጠ። አሸባሪ ቡድኑ የፈጸመው ድርጊትም የሰዎችን እምነት የሚጋፋ መሆኑን ምክር ቤቱ ገልጿል።
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ሀጂ ሙሀመድ ሀሰን፣ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፣ በሰሜን ጎንደር ውስጥ በሚገኘውና በቅርብ በተገነባው የዛሪማ መስጊድ ላይ በከባድ መሳሪያ ተኩሶ መስጊዱን በከፊል አውድሟል።
በአካባቢው አሸባሪው ቡድን ሸሽቶ ጫካ በመግባቱና ደብቆ ባከማቸው የከባድ መሳሪያ ከርቀት በማስወንጨፍ በዛሪማ መስጊድና በአካባቢው በሚገኙ ቤተ-እምነቶችና ንፁሀን ላይ ጉዳት እያደረሰ እንዳለ ገልጸዋል። አሸባሪ ቡድኑ የፈጸመው ተግባርም ለእምነት ክብር እንደማይሰጥ አንዱ ማሳያ መሆኑንም ተናግረዋል።

አሸባሪ ቡድኑ ባደረሰው ጥቃትም የመስ ጊዱን ሚናራ ማፍረሱን፣ ግድግዳው እና መስኮቶቹን ማውደሙን አረጋግጠናል ያሉት ሀጂ ሙሀመድ ሀሰን፣ ሰባብሮ ማውደሙን በቡድኑና የክልሉ ምክር ቤት መረጋገጡን የጠቆሙት ሀጂ ሙሀመድ ሀሰን ፣ በውስጡ በነበሩ ሰዎች ላይ የደረሰ የሞትና የአካል ጉዳት ለመኖሩና ላለመኖሩ እስካሁን እንዳልተረጋገጠ ተናግረዋል።
በመስጊዱ ውስጥ በነበሩ ሰዎች የደረሰ የሞትና የአካል ጉዳት ለመኖሩና ላለመኖሩ በቀጣይ ተጣርቶ እንደሚገልፅ ሀጂ ሙሀመድ ሀሰን ተናግረው፣አሸባሪ ቡድኑ ከዚህ ቀደምም በነጃሺ መስኪድ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መፈጸሙንና ድርጊቱም በርካታ አማኞችን ማሳዘኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል። (ኢብኮ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply