ለኢትዮጵያ የሚያስፈልገው እውነተኛ “ትራንስፎርሜሽን” ከሁከት ይልቅ ውይይት፣ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር፣ ከብቀላ ይልቅ ይቅርታ መሆኑን በማስገንዘብ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በግል ደብዳቤ መላኩን አስታወቀ፡፡ ንቅናቄው በደብዳቤው መልካም ተግባር በመፈጸም በትውልድ ሁሉ “ታላቁና ደጉ መሪ” እንዲባሉ ምኞቱን ገልጿል። ንቅናቄው ለጻፈላቸው ደብዳቤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልስ ይሰጣሉ የሚል ሙሉ እምነት እንዳለው ለጎልጉል በእርግጠኝነት ተናግሯል። ኢትዮጵያ የሁሉም አገር እንደሆነች በማስታወቅ በአቶ ኦባንግ ሜቶ የአኢጋን ዋና ዳይሬክተር ፊርማ የተላከው ደብዳቤ አቶ መለስ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ጥሪ ሲቀርብላቸው ባለመቀበል ለህዝብ መንገድ ንቀት ሲያሳዩ ማለፋቸውን ያስታውሳል። የአንድ ጎሣ፣ ብሔር፣ … [Read more...] about ኦባንግ ለሃይለማርያም በግል ደብዳቤ ላኩ!
News
ዜና
ሶስት የህወሓት ሰላዮች ከዱ
ሶስት የብሔራዊ ስለላና የደህንነት ሰራተኞች አገር ለቀው መኮብላቸው ታወቀ። የኮበለሉት የህወሓት/ኢህአዴግ ሰዎች ስደት በጠየቁበት አንድ የአውሮፓ አገር አስቸኳይ ከለላ ማግኘታቸውም ታውቋል። በቅርቡ አገር እየለቀቁ ከሚኮበልሉት የህወሓት/ኢህአዴግ አባላትና ሰራተኞች መካከል የደኅንነት ሰራተኞች እንደሚገኙበት ያመለከተው የጎልጉል የአውሮፓ ሪፖርተር፤ ድርጊቱ አስቀድመው ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞችን አስደንግጧል። በህወሓትና አቶ መለስ በሾሙዋቸው በሻዕቢያ ሰዎች የበላይነት የሚመራውን የስለላ ተቋም ሲያገለግሉ የነበሩትና አሁን የኮበለሉት ሶስት የደህንነት ሰዎችን ስም ዝርዝር ለጊዜው ከመዘርዘር በመቆጠብ መረጃውን ለጎልጉል የአውሮፓ ዘጋቢ የሰጡት ከሰዎቹ ጋር በቅርብ ርቀት አብረዋቸው የሚኖሩ ስደተኞች ናቸው። ሪፖርተራችን ባጠናከረው መረጃ ሶስቱ የስለላ ሰራተኞች በመረጃ ትንተና ዲቪዥን … [Read more...] about ሶስት የህወሓት ሰላዮች ከዱ
“ለዚህ (መንግሥት) ታላቅ ክብር አለኝ”
“ለኢትዮጵያ የጥምር መንግስት ያስፈልጋታል” በማለት በ1997 ምርጫ አጥብቆ ሲከራከር የነበረውና በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ውስጥ የገባው ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበሩት መንግስታትና ትውልዶች ይልቅ አሁን ላለው ትውልድ ከበሬታ እንዳለው በመግለጽ አስተያየቱን ሰነዘረ። የክብር ሪኮርዶቹን በሙሉ ለቀነኒሳ ያስረከበው ሃይሌ በእጁ የሚገኘውን ብቸኛ ሃብቱን (የህዝብ ክብር) እያሟጠጠ መሆኑ እየተገለጸ ነው። ሃይሌ ይህንን የተናገረው መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ ም ከተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ጋር በመንግስት ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) አስተያየት በሰጠበት ወቅት ነበር። የቀድሞውን ስርዓትና ትውልድ “ድንጋይ ዳቦ በነበረበት፣ ፍራፍሬ ከጫካ ያለምንም ድካም ከሚሰበሰብበት” ዘመን ጋር ያወዳደረው ሃይሌ፣ “የአሁኑ ትውልድ” በማለት ያሞካሸውን ስርዓት ከተፈጥሮ ጋር … [Read more...] about “ለዚህ (መንግሥት) ታላቅ ክብር አለኝ”
ዶላር አዘዋዋሪዎቹ ደላሎች!!
ህወሓት የአጋር ፓርቲዎቹን የንግድ ተቋማትና ልማታዊ ባለሀብት እያለ የሚጠራቸውን አባላቱን በዋናነት አሰባስቦ ያቋቋመው የወጋገን ባንክ ውለታ ባስገባቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች አማካይነት በቀን እስከ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ ዶላር የመሰብሰብ አቅም መገንባቱ ተጠቆመ። የጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የአዲስ አበባ ዘጋቢ ባካሄደው ማጣራት ወጋገን ባንክ ከፖለቲካው አመራር ባለው ቀጥተኛ ድጋፍና ሽፋን በመታገዝ ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፈውን የውጪ ምንዛሪ መቆጣጠር ያስቻለውን አቅም የገነባው በአስገዳጅ ደንብ ነው። በሶማሌ ተወላጆችና በህወሓት ሰዎች አማካይነት በሽሪክነትና በተናጥል የተቋቋሙ የገንዘብ አዘዋዋሪ ተቋማት ስራውን መስራት የሚያስችላቸውን ፈቃድ ሲያወጡ ከወጋገን ባንክ ጋር ብቻ ለመስራት አስቀድመው ውል እንደሚፈጽሙ ያስታወቀው ዘጋቢያችን፤ በዚሁ መሰረት ውል ከገቡት የገንዘብ … [Read more...] about ዶላር አዘዋዋሪዎቹ ደላሎች!!
“ታላቅ ዕድል ነው!”
ዛሬ አርብ ልክ ከጠዋቱ 3፡38 ላይ 374 የኢህአዴግ ወኪሎችና ኢህአዴግን እንደሚደግፉ በግልጽ የሚናገሩት አንድ በግል ያሸነፉ የፓርላማ አባል የሚገኙበት የተወካዮች ምክር ቤት አጨበጨበ። ጭብጨባውን ተከትሎ ኢቲቪ የቦሎ ሶሬውን ሰው አመላከተ። ከሃያ አንድ ዓመት በኋላ በሟቹ አቶ መለስ የፓርላማ መቀመጫ ላይ የተሰየሙት አቶ ኃይለማርያም ፈገግታ አሳዩ። አስቀድሞ የተነገረው በትረ ሹመት ስርዓቱን አሟላ። አቶ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ታወጀ። ቀልጠፍ ቀልጠፍ እያደረጉ ስርዓቱን የመሩት አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶ ተገኔ ጌታነህን ጋበዙ። በሳቸው ትዕዛዝ ኃይለማርያም ቃለ መሃላ ለመፈጸም ቀኝ እጃቸውን አነሱ። ስማቸውን ጠርተው ማሉ።“…ከአገርና ከህዝብ የተጣለብኝን ሃላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት፣ እንዲሁም ህግንና … [Read more...] about “ታላቅ ዕድል ነው!”
“የመሬት ባላባቱ” ሚኒስትር!!
አቶ አባይ ጸሀዬ በዘመዶቻቸው ስም በርካታ መሬቶች መውስዳቸው፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ባስቀመጡት ሃላፊ አማካይነት በመሬት ንግድ ከፍተኛ ጥቅም ማግኘታቸው፣ ህጋዊ ሰነድና ካርታ ያለው ቁልፍ ቦታ ከባለቤቱ ተነጥቆ ለእርሳቸው ዘመድ መሰጠቱ ሲረጋገጥ ምርመራው እንዲቆም መታዘዙ ታወቀ። በየክልሉ ተመሳሳይ ንቅዘት አለ። በህዝብና በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች፣ እንዲሁም ለአብነት የተጠቀሱት ንብረታቸው የተወሰደባቸው ሴት ወ/ሮ ጉዳያቸውን የትኛውም ቦታ ሲወስዱ መጀመሪያ ቀጠሮ እንደሚሰጣቸው፣ በቀጠሮዋቸው ቀን ሲሄዱ ምን ምላሽ እንደማያገኙ ጠቅሰው ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የተጀመረው የምርመራ ስራ ይህንን ይመስላል። ቀደም ሲል ተጠሪነቱ ለአቶ መለስ የነበረው የፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎች አቶ አባይ ጸሃዬን “የመሬት ከበርቴው” የሚል ስም ሰጥተዋቸዋል። ስያሜውም … [Read more...] about “የመሬት ባላባቱ” ሚኒስትር!!
ህወሓት የደኅንነት ሞተሩን መሪው አደረገ!
ህወሓት የድርጅቱን መሪዎች መምረጡን ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሰረት አቶ አባይ ወልዱ ሊቀመንበር፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ወልደ ሚካኤል ምክትል አድርጎ ሰይሟል። ምርጫው የተከናወነው መቀሌ ሳይሆን አዲስ አበባ ነበር። ሴፕቴምበር 19 ይፋ የተደረገውን የህወሓት ምርጫ አስመልክቶ ህወሓት መግለጫ አሰራጭቷል። ህወሓት በምርጫው ያልተገመቱና አዲስ አመራር ወደ ሃላፊነት አምጥቷል። እርሳቸውም ዶ/ር ደብረጽዮን ወልደ ሚካኤል ናቸው። በሚኒስትር ማዕረግ የኢንፎርሜሽንና ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተርና የኢትዮ ቴሌኮም ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን በነባር ታጋዮች ዘንድ እይወደዱም። ደብረጽዮን ወልደ ሚካኤል በደኅንነቱ የሚከናወኑ ከፍተኛ ጉዳዮችን የሚመሩ፣ ከፍተኛ ውሳኔዎችን የሚወስኑ፣ የአገሪቱን የደኅንነት መዋቅር ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ጎን ለጎን የሚመሩ መሆናቸውን በቅርብ የሚያውቁ … [Read more...] about ህወሓት የደኅንነት ሞተሩን መሪው አደረገ!
ከ21 ዓመት በኋላ ህወሓት ተነፈሰ!!
የመከላከያውንና የደህንነቱን የስልጣን ርካብ ከቀድሞው ይልቅ ቆንጥጦ ለመያዝ እየተረባረበ ያለው ህወሓት በግልጽ ከሚታየው የፖለቲካ አመራር ወንበሩ ተነሳ። ለ21 ዓመታት የድርጅት፣ የጠ/ሚኒስትርነትና ቁልፍ የስልጣን መደቦችን ተቆጣጥሮ የኖረው ህወሓት ሁለቱን ግዙፍ ወንበሮች ለማስጠበቅ በድርጅትና በጎንዮሽ ትስስር ያካሄደው ዘመቻ አልተሳካለትም። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አቶ መለስን የሚተካ መሪ መሰየም አለመቻሉን አቶ በረከት ስምኦን ያሳበቁበት ህወሓት በቀጣዩ ምርጫም ወንበሩን እንደማያገኘው አቶ በረከት በግልጽ ተናግረዋል። ኢህአዴግ ቀጣዩን ምርጫ ካሸነፈ ሁለቱ አዲስ ተሿሚዎች በስልጣናቸው እንደሚቀጥሉ በይፋ ተናግረዋል። የኢህአዴግን የአመራር ወንበር ላለማጣት ያደረገው ሙከራ በየድርጅቶቹ በተካሄደ የተናጠል ስብሰባ ተሞክሮ ሊሳካ እንዳልቻለ ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ … [Read more...] about ከ21 ዓመት በኋላ ህወሓት ተነፈሰ!!
ኢትዮጵያ ወደ ወታደራዊ አስተዳደር?!
ሰሞኑን ይፋ የተደረገው የከፍተኛ ወታደራዊ ሹመት ህወሓት የፖለቲካ የበላይነቱ ለመመናመኑ ምልክት መሆኑ ተጠቆመ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የህግ ለውጥ ሳይደረግ በደህንነት ሹሞች የቅርብ ቁጥጥር ስር መዋሉም ተሰማ። የጎልጉል ምንጮች ያነጋገሩዋቸው ክፍሎች መለስ በህይወት እያሉ ሁሉንም ቁልፍ ይዘውት ስለነበር ህወሃት የፖለቲካ የበላይነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ ስለነበር የጦር ኃይሉ በፖለቲካው ዘርፍ ቀጥተኛ ተሳታፊ ሲሆን አይታይም ነበር። ኢትዮጵያን ወደ ፍጹም ወታደራዊ አስተዳደር ለማሸጋገር ደፋ ቀና ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ህልፈት ሲያስተባብል የቆየው ኢህአዴግ፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ለሰላሳ አራት ከፍተኛ መኮንኖች የብርጋዲዬር ጄኔራልነት፣ ለሶስት ብርጋዲየር ጄኔራሎች ደግሞ የሜጀር ጄኔራልነት ማዕረግ መስጠቱን ምንጮቹ ያስታውሳሉ። በተለይም ሃያ ሶስቱ ተሿሚ ጄኔራሎች የትግራይ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ወደ ወታደራዊ አስተዳደር?!
የመለስ ሞትና የኤርትራ ዝምታ
የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር የአቶ መለስን ሞት አስመልክቶ ሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራም (ሻዕቢያ) ሆነ መሪው አቶ ኢሳይያስ የሚያስተዳድሩዋቸው መገናኛዎች ዝምታን መምረጣቸው እያነጋገረ መሆኑ ተገለጸ። በአገር ውስጥና በውጪ ለሚኖሩ የተለያዩ ኅብረተሰብ ክፍሎች መጠይቅ በመበተን ባሰባሰብነው መረጃ የኤርትራ ዝምታ የአቶ መለሰንና የኤርትራን ቁርኝት አደባባይ ያወጣ እንደሆነ የሚስማሙት ቁጥር አብላጫ ነው። “አቶ መለስ ቀድሞውንም ለኤርትራና ለኤርትራ ተወላጆች ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ የነበሩ መሪ መሆናቸውን ለምንረዳ የሻእቢያ ዝምታ አያስገርምም” የሚሉት አስተያየት ሰጪ “አቶ መለስ ለኤርትራ ያሳዩትን ከልብ የመነጨ ፍቅርና የተቆርቋሪነት ስሜት ለሚመሩት ህዝብና አገር አሳይተው አያውቁም። የኤርትራ ተወላጆችም ሆኑ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ሃዘን ቢቀመጡ ከኢትዮጵያዊያን በላይ … [Read more...] about የመለስ ሞትና የኤርትራ ዝምታ










