• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው” የመለስ ድራማ!!

October 20, 2012 02:11 am by Editor Leave a Comment

የኦጋዴን ጉዳይ ሲነሳ ኢህአዴግ ይደነግጣል። ስለ ኦጋዴን አንዳችም ጉዳይ እንዲነሳበት አይፈልግም። የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ በኦጋዴን ተፈጽሟል ያለውን ይፋ ሲያደርግ ኢህአዴግ በተለዩት መሪው፣ በህዝብ ግንኙነቱና እንግሊዝ አገር ባሉት አምባሳደሩ በኩል የማስተባበያ ዘመቻ ከፍቶ ነበር። በኬንያ ስደት ጣቢያ የሚገኙትን የክልሉ ነዋሪዎችን ያነጋገረው የቢቢሲው መርማሪ ጋዜጠኛ ሪፖርት ብቻ ሳይሆን ሂውማን ራይትስ ዎችም የከረረ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ከአገር በቀል የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች መካከል የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄም በተመሳሳይ የኦጋዴንን አጀንዳ በማንሳት ጥሪ በማስተላለፍ ቅድሚያ እንደነበረው መረጃዎች ያመለክታሉ።

ኢህአዴግ በሃሰት ላይ የተመረኮዘ መረጃ በማዘጋጀት የሚመራውን ህዝብና የዓለም ህብረተሰብን እንደሚያወናብድ የሚያጋልጡ መረጃዎች በየጊዜው ይፋ ይሆናሉ። “ታላቅ ስህተት ሰርተናል፣ስህተቱ ህይወታችንን ሊያሳጣ ይችል ነበር …” በማለት አዲስ አበባ ከርቸሌ ውስጥ ሆነው ይቅርታ የጠየቁት ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች፣ ሰሞኑን ይፋ ያደረጉት ነገር ቢኖር ይህንኑ ኢህአዴግ ሊከድነው የሚደክምበትን ሃቅ ነው።

የተቀነባበረ ድራማ  “እንደ ሆሊ ውድ” ፊልም ማዘጋጀት የዓለምን ህብረተሰብና የሚመራውን ህዝብ ያጭበረበረው ኢህአዴግ በሞት በተለዩት መሪው አማካይነት ሲምልና ሲገዘትበት የነበረውን ማጭበርበር ማርቲን ሺብዬና ዩሃን ፐርሸን አጋልጠዋል። አቶ መለስ “የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው” በማለት ለፈጠሩት ፓርላማ ሲፈላሰፉና በህግ የበላይነት እንደሚያምኑ እያስጨበጨቡ ሲናገሩ የነበሩትን ሁሉ እርቃኑን በማስቀረት ሁለቱ ጋዜጠኞች ህያው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።በኢትዮጵያ በተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ደጋፊዎች፣ በጋዜጠኞችና ስርዓቱን በሚቃወሙ ዜጎች ላይ የሚለጠፈው “የአሸባሪነት” ወንጀል የተቀነባበረ የፈጠራ ፊልም መሆኑን አረጋግጠዋል።

ቀደም ሲል መለስ፣ አሁን ደግሞ ሃይለማርያም እየማሉበት ያለው የህግ የበላይነት ቁማር መሆኑን፣ ፍርድ ቤቶቻቸው የቁማር መጫወቻ፣ ዳኞቻቸው ታላቁን ሙያ ያረከሱና ሙሉ በሙሉ በተቀናበረ ድራማ የሚፈርዱ መሆናቸውን ሁለቱ ጋዜጠኞች ላገራቸው ሚዲያዎች፣ ለቢቢሲ አፍሪካና ለአሜሪካ ሬዲዮ አስታውቀዋል። በዚህም ተግባራቸው ቀደም ሲል የበደኖና የወተር፣ በቀርቡ ደግሞ “አኬልዳማ” የተሰኘው የመወንጀያ ዶክመንተሪ ኢህአዴግ ቆርጦ እየቀጠለ፣ እያስፈራራና በቅድመ ሁኔታ እየተደራደረ የሚያመርተው የግፍ አገዛዙ ማስቀጠያ የማታለያ ሸቀጡ ስለመሆኑ አመላክተዋል።

በተለይም የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍለ ጊዜ በዝርዝር ያቀረበው የሁለቱ ጋዜጠኞች ቃለ ምልልስ አገር ቤት የተለያዩ ጉዳዮችን አስነስቷል። “በደኖ ኢንቁፍቱ /የማይጠግበው ዋሻ/፣ አርባ ጉጉ፣ ደደር፣ ወተር፣ ቆቦ … አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሟል። የጎሳ ፖለቲካ ጣጣ ሰለባ ያደረጋቸው የኢትዮጵያ ልጆች ከነ ህይወታቸው ጉድጓድ ውስጥ ተጥለዋል። በጅምላ እንደ ባዳ ተጨፍጭፈዋል።ኢህአዴግ ህዝቡን ከመጠበቅ ይልቅ ለተራ የፖለቲካ ትርፍ በተቀነባበረው ወንጀል ስር ፊልም ያቀናብራል። የፖለቲካ ቁማር ይቆምራል። ራሱ ገደል ከቶ በሃዘን ሙዚቃ ታጅቦ ራሱ ከገደል ሲያወጣ የሚያሳይ ዘግናኝ ፊልም ለህዝብ እያሳየ እንባ ያራጫል። በሃሰት ፊልም እያመረተ ያጭበረብራል። የሁለቱ ስዊድን ጋዜጠኞች ሰሞኑን ያረጋገጡት ነገር ቢኖር ይህንኑ ነው” የሚል አስተያየት ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ተልኳል።

መለስ ቀይ መስቀልን ጨምሮ በኦጋዴን የሚገኙ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችን ሙሉ በሙሉ ሲያስወጡ ምን አስበው ነበር? ለሚለው የብዙዎች ጥያቄ ምላሽ የተገኘ ይመስላል። “መለስም አረፉ፣ እኛም አረፍን የምንለው መቼ ነው” በማለት የሚጠይቀው ቀን 2004 ዓ ም የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ነጥቦችን በመዘርዘር ስለ ኦጋዴን ችግር ያወጣው መግለጫ:-

“… ለወራት ያህል በመለስ ታማኞች ትዕዛዝ ሰጪነት የተከበቡት ኦጋዴኖች በረሃብ ተጠበሱ። ችግሩ ሲጠናባቸው ሽማግሌ በመላክ “በረሃብ ማለቃችን ነው። እኛ ንፁሃን ዜጎች ነን። ህፃናት እየተጎዱ፣ ከብቶቻችን እያለቁ ነው’’ በማለት ከከበባው ለመውጣት  ጥያቄ ቢያቀርቡም ትእዛዝ ከተላለፈላቸው የጦር አዛዦች ያገኙት መልስ ጥይት ነበር። በተፈጥሯቸው አንድ ቀበሌ መኖር የማይችሉ ዘላኖች (አርብቶ አደሮች) ከቦታ ቦታ መዘዋወር ተከልክለው ለአራትና አምስት ዓመታት እንዴት ኖሩ? ምን ያህልስ ሰብዓዊ ቀውስ ደረሰ? ከአመታት የስቃይ ኑሮ በኋላ የመጨረሻው የፍርድ ቀን ደርሶ በኦጋዴን የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሄደ። ንፁሃን ጉድጓድ ተምሶ በጅምላ እንዲቀበሩ ተደረገ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መለስ ስለ ኦጋዴን ሲነሳ ያማቸው ጀመር። ከዋናው የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የሰላም ስምምነት አድርጌያለሁ ቢሉም አካባቢውን ገለልተኛ ወገኖች ገብተው እንዲመለከቱት ፈቅደው አያውቁም። ሰሞኑን  የስዊድን ጋዜጠኞች  ላይ የተወሰደው ርምጃም የዚሁ ‹ምስጢር ይወጣብኛል› ፍርሃቻ አካል ስለመሆኑ ጥርጥር የለንም … ”

“… ኦጋዴን በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ተድበስብሶ ቢከርምም ዛሬ በሶማሊያ የተከሰተውን አስፈሪ ርሃብ ተከትሎ ይፋ መሆን ጀምሯል። ድርጅታችን በጋምቤላ፣ በደቡብ፣ ክልል፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተፈፀሙትን ጭፍጨፋዎች በመቃወም እንዳደረገው ሁሉ በኦጋዴን የተፈፀመው ጭፍጨፋ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ ነው። የኦጋዴን ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በመሆኑ ይህ መግለጫ የሚደርሳችሁ አካላት በሙሉ ድርጊቱን በመቃወም አግባብ ያለው ተፅዕኖ በማድረግ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ መድረክ ትግላችሁን እንድትቀጥሉ አጥብቀን እናሳስባለን” ሲል ጥሪውን አስተላልፎ ነበር። (የመግለጫው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)

ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች ኦጋዴን ዘልቀው የተደበቀ ምስጢር ለማውጣት የተከለከለውን መስመር በማለፍ የወሰዱት ርምጃ አስደናቂ የሚደርገው በርካታ ምክንቶች አሉት። አሜሪካ ድምጽ አማርኛ ክፍለ ጊዜ በስፋት የተረከው ጉዳይ በዘርፉ ለተሰማራነው ሁሉ ትምህርት የሚሰጥ፣ ሙያው ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን የሚያስገነዘብ፣ በበረሃ መንከራተትን የሚጠይቅ፣ የተደበቀ እውነትን በማጋለጥ መረጃን መስጠት ምን ያህል ክቡር እንደሆነ የሚያመላክት ነው። (አሜሪካ ድምጽ ዘገባ እዚህ ላይ ይገኛል)

(ሐብታሙ ሂካ ያምቦ፤ Habtamu Hiikaa Yaamboo; habtamu@goolgule.com)

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule