• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኦብነግና ኢህአዴግ ንግግር አቆሙ!

October 19, 2012 12:52 am by Editor 2 Comments

የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አወጪ ግንባር /ኦብነግ/ እና ኢህአዴግ ጀምረው የነበሩት ድርድር መጨናገፉ ታወቀ። ድርድሩ የተጨናገፈው በኢህአዴግ በኩል በቀረበ ቅድመ ሁኔታ መሆኑ ተገልጿል። መግለጫው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስለተደረገው ንግግር በዝርዝር ሳያብራራ ህዝበ ውሳኔን በመፍትሄነት አስቀምጧል። 74 ንጹሃንን የገደሉት የኦብነግ ሰዎች ጉዳይ በድርድሩ ስለመካተቱ እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም።

ኦብነግ በድረገጹ ኦክቶበር 17 ቀን 2012 በይፋ እንዳስታወቀው የሰላም ድርድሩ የተጀመረው የኢትዮጵያ መንግሥት ለኬኒያ መንግስት ባቀረበው የአሸማግሉኝ ጥያቄ መሰረት ነበር። በዚሁ ጥያቄ መሰረት የኬንያ መንግስት አሸማጋዮች ለግንባሩ አመራሮች ጥያቄውን አቅርቦ ቀና ምላሽ በማግኘቱ የመጀመሪያ ደረጃ ንግግር ተደርጎ ነበር።

የግንባሩ አመራሮች በቀናነት የድርድር ሃሳቡን ተቀብለው እንደነበር ያስታወቀው መግለጫ የመጀመሪያው ንግግር በድርድሩ መርህ፣ ቅርጽና አጠቃላይ የመደራደሪያ አጀንዳዎች ዙሪያ መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር አስታውሷል። በዚሁ መነሻ ኦክቶበር 15 እስከ 17 በተደረገው ሁለተኛ ንግግር ላይ ቀደም ሲል ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ለማካሄድ የተደረሰውን ስምምነት ኢህአዴግ ጥሶታል።

በመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑካን “ኦብነግ በቅድሚያ ህገ መንግስቱን መቀበል አለበት” በማለት ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡ በመግለጫው ተወስቷል። ድርድር ለማካሄድ ያመች ዘንድ በተደረገው የመጀመሪያ ንግግር ሁለቱም ወገኖች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ የሰላም ድርድሩን የሚያሰናክሉ ጉዳዮችን ወደ ጎን በመተው ለመነጋገር ተስማምተው ሳለ ከኢትዮጵያ ወገን በቀረበ አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ ሳቢያ የሰላም ድርድር ለማካሄድ የተጀመረው ጥረት መቋረጡን አስታውቋል። በማያያዝም አቋሙን ይፋ አድርጓል። ግምባሩ በጥቅል በቀረበለት ቅድመ ሁኔታ ሳቢያ የሰላም ድርድሩን መጨናገፍ ሲያስታውቅ ሰነድ ሰንቆ ማሰረጃ አደራጅቶ ለሁለት ቀናት በናይሮቢ ስለተካሄደው ድርድር ዝርዝር ጉዳይ ዝምታን መምረጡ ለድርድሩ መቋረጥ ተጨማሪ ምክንያቶች እንዳሉ አመላካች ነው ተብሏል።

“በእኛ እምነት” ሲል የግንባሩን አቋም ያስታወቀው መግለጫው በኦብነግ እምነት በኦጋዴን ውስጥ ያለው ግጭት መፍትሄ ሊያገኝ የሚችለው የክልሉ ህዝብ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታና ገደብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብታቸውን እንዲጠቀሙ ሲደረግ ብቻ ነው። ግንባሩ በዚህ መሰረታዊ እምነቱ ሳቢያ ለድርድር የቀረበለትን አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ አለመቀበሉን ይፋ አድርጓል። በመጀመሪያው ንግግር መሰረት ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ የሰላም ድርድሩ ቢቀጥል ፈቃደኛ እንደሆነም አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦክቶበር 17 ቀን 2012 ኦብነግ ድርድሩ መጨናገፉን ይፋ ሲያደርግ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለተወካዮች ምክር ቤት ስም ሳይጠቅሱ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር ድርድር በመደረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል። በማብራሪያቸው ተቃዋሚዎችን ያወገዙት አቶ ሃይለማርያም መንግስታቸው ለመቻቻልና ለሰላም ያለውን ቁርጠኛነት ባስታወቁበት የንግግራቸው ክፍል ከቶውንም የማይደራደሯቸው ክፍሎች እንዳሉ አስታውቀዋል። እርስ በርሱ በሚጋጨው ገለጻቸው ስለ ሰላምና ስለ ኃይል እርምጃ አይቀሬነት ከማስጠንቀቂያ ጋር መልዕክት ያስተላለፉት ጠ/ሚኒስትሩ በተለይ ስለ ኦብነግ በስም ጠቅሰው የተናገሩት ነገር የለም።

በኦጋዴን፣ ከደገሃቡር 19 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ኢቦሌ የነዳጅ ፍለጋ ስራ ላይ በተሰማሩ 68 የኢትዮጵያ፣ 9 የቻይና ዜጎች ላይ አፕሪል 24/2007 በድንገት ለደረሰው ጭፍጨፋ ኦብነግ ሃላፊነቱን መውሰዱ አይዘነጋም። በ74ቱ ያልታጠቁ ሲቪል ሰራተኞች ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ በተደረገ አሰሳ መንግስት ወንጀሉን በዋናነት በማስተባበር ፈጽመዋል ያላቸውን ዘጠኝ ሰዎች በቁጥጥር ስር በማዋል በሶማሌ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ በሞት ፍርድ እንዲቀጡ መወሰኑም አይዘነጋም። ይሁንና ኢህአዴግ ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት ከኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር አንድ ክንፍ ጋር ሰላም ማውረዱን ይፋ ባደረገበት ወቅት አቶ አባይ ጸሃዬ በሸራተን አዲስ መግለጫ ሲሰጡ “ … በስምምነቱ መሰረት የታሰሩና በህግ ለሚጠየቁ ምህረት ይደረጋል። የሚታየው የወደፊቱ ዘለቄታዊ ሰላም ነው” በማለት ሞት የተፈረደባቸው በድርድሩ አስገዳጅነት እንደሚፈቱ አስታውቀው ነበር። የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ፍርደኞች ከሶማሌ ክልል ወህኒ ቤት ወደ ዝዋይ ተዛውረው፣ ቤተሰቦቻቸውም ዝዋይ ከተማ ቤት ተከራይተው እየጎበኟቸው መሆኑን ከጎልጉል የኦሮሚያ ፖሊስ ምንጮች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።

ፍርደኞቹ ዝዋይ ማረሚያ ቤት ጨለማ ክፍል ውስጥ በልዩ ጥበቃ ለተወሰነ ጊዜ ከኖሩ በኋላ ቤተሰቦቻቸውን የሚያነጋግሩበት የተለየ ኮሪደር ተዘጋጅቶላቸው ከሁሉም በተሻለ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ መደረጉን የዓይን ምስክሮች ይናገራሉ። አዲስ ተጀምሮ የተሰናከለው ድርድር እነሱን ስለማካተቱ እስካሁን ከኦብነግ በኩል የተባለ ነገር የለም። ከመንግስት ጋር ስምምነት ላይ የደረሱትን ክፍሎች አስመልክቶ ኦብነግ ውስን ወታደር ያላቸው አነስተኛ አፈንጋጮች በሚል ግንባሩን እንደማይወክሉ በተደጋጋሚ መግለጹ አይዘነጋም።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. serbedin says

    October 23, 2012 10:01 am at 10:01 am

    it is sad news to learn about Ethiopia and this TPLF news specially about democracy those who started their struggle for independence it is real Story OGADEN is not the part of Ethiopia and Ethiopia is the christian part of the LAND that is our last choice our unity never brings democracy it brings domination against Islam and Muslims only so we have to struggle for our freedom until l the drop of our blood we considered as part of Ethiopian Somali but things are different on the ground so from today i will go to my motherland OGHADEN and fight for our independence as our constitution article 39 allows us to go for secession alhamdulillah we don’t need wuyyane at all if this government change only we can negotiate about living together

    Reply
    • Christian says

      October 24, 2012 07:32 am at 7:32 am

      You serbedin u’r the only idiot person among the ogaden people

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule