የቴዎድሮስ ክፍል ጦር ጥሪውን ተቀበለ በሕግ ወጥ መልኩ በዘመን ትህነግ በየክልሉ ተቋቁመው የነበሩና ልዩ ኃይሎች ፈርሰው ወደ መከላከያ ወይም ፖሊስ እንዲገቡ በተወሰነው መሠረት የቴዎድሮስ ክፍለ ጦር ጥሪውን ተቀበሎ ወደ ካምፕ ገብቷል። መንግሥት ያቀረበውን የልዩ ኃይል ሪፎርም ተቀብለው ሰላምን መርጠው ወደ ሕጋዊ መንገድ የመጡ የቴዎድሮስ ክፍለ-ጦር የልዩ ኃይል አባላትን የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ደማቅ አቀባበል አደርጎላቸዋል። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደ ቤተሰቦቻቸው ተንጠባጥበው ለተበተኑ የልዩ ኃይል አባላትም በፈለጉት ማለትም የክልል ወይም የፌደራል ፖሊስ ወይም የመከላከያ ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ዶ/ር ወንደሰን የተባለ ግለሰብ ከመስከረም አበራ ጋር ሲያወራ የተቀዳ ተብሎ በተሰራጨው የድምጽ ቅጂ ላይ እንደሚሰማው በጎንደር ያለውን ልዩ ኃይል … [Read more...] about ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ
News
ዜና
ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል
ኢትዮጵያ ማር ለማምረት የሚያስችል ያላትን ከፍተኛ ጸጋ በሚገባ እየተጠቀመች እንዳልሆነ ተነግሯል፡፡ ሃገሪቱ በአመት 500 ሚሊዮን ቶን ማር የማምረት አቅም ቢኖራትም እያመረተች ያለችው ግን 10 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ሆኖ የምትመረተዋ አነስተኛ የማር ምርት በኮንትሮባንድ ወደ ውጭ እየወጣች መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡ በተለያዩ የሃገሪቷ አካባቢዎች ገበሬዎች የሚያመርቱት የማር ምርት በትክክለኛው መንገድ ወደ ገበያ እየቀረበ ባለመሆኑ እና በኮንትሮባንድ ወደ ውጭ ስለሚወጣ ሃገሪቷን ገቢ እያሳጣት ይገኛል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳሬክተር አቶ ታሪኩ ተካ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ደላሎች አዛዥ በሆኑበት የማር ምርት ሃገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ገቢ እንዳታገኝ አድርጓታል ብለዋል፡፡ የማር ምርት እና ግብይትን የሚመለከት … [Read more...] about ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል
መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ
ከ698,000 በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘Mereja TV’ የሚል ስያሜ ያለው የፌስቡክ ገጽ ከነገ ጀምሮ “በአማራ ክልል ለ10 ቀናት የሚቆይ ዘመቻ የኮቪድ ክትባት በሚል ምንነቱ ያልታወቀ ክትባት ሊሰጥ መሆኑ ተገልጿል” የሚል መረጃ ማሰራጨቱን ተመልክተናል። ገጹ በተጨማሪም ህብረተሰቡ ክትባቱን እንዳይወስድ የሚያሳስብ መልዕክት ማከሉን አስተውለናል። መረጃ ቲቪ የተባለው ይህ የፌስቡክ ገጽ ይህን ይበል እንጅ በአማራ ክልል እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ለ10 ቀናት ሊሰጥ ስለታቀደው ክትባት የአማራ ክልል ጤና ቢሮና የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ባለፉት ቀናት በተናጠል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራሪያ መስጠታቸውን ተመልክተናል። በመግለጫዎቹም የክትባቶቹ ምንነት የተገልጸ ሲሆን ዘመቻ አገር አቀፍ ስለመሆኑን ተብራርቷል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በትናትናው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ … [Read more...] about መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ
“ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን”
”ነገሮች ተበላሽተዋል” በሚል የፋኖ አሰባሳቢ ኮሚቴ ናቸው የሚባሉት ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ ከመስከረም ጋር በስልክ ያደረጉትን ንግግር ይፋ በሆነ ማግስት በሰሜን ወሎ ዞን አካባቢ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበልና ይፋዊ ይቅርታ በማቅረብ ወደ መደበኛ ህይወታቸው መመለሳቸውን የአማራ ክልል አስታወቀ። ክልሉን ጠቅሶ የአማራ ማስ ሚዲያ ይፋ እንዳደረገው በሰሜን ወሎ ዞን አካባቢ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበልና ይፋዊ ይቅርታ በማቅረብ ወደ መደበኛ ህይወታቸው ተመልሰዋል ብሏል። “ተታለን ነው” በሚል ሽማግሌ የላኩትን የሰሜን ወሎ ፋኖዎች ጥያቄ ለመቀበል የአገር መከላከያ ሰራዊት አመራሮች ከዚህ በኋላ ምንም አይነት መንገድ እንዳይዘጋ፣ምንም አይነት የታጠቀ አካል ከተማ ውስጥ እንዳናገኝ … [Read more...] about “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን”
በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው
ጦርነት ባሕላችን ነው፣ ተራራ ያንቀጠቀጠ ትውልድ፣ ወዘተ በሚሉ ባዶ ዲስኩሮችና ከንቱ ልፈፋዎች ትውልድን በስሁት ትርክት ሲነዳ የኖረው ትህነግ የሚፈራው ጥያቄ እየቀረበለት ነው። "ልጆቻችን የት ናቸው?" "ልጆቻችንን መልሰን ማግኘት እንፈልጋለን" ወዘተ የሚሉ የወላጆች ጥያቄ በትግራይ እየተሰማ ነው። አቶ ገብረመስቀል አበበ የተባሉት ሌላኛው ነዋሪም የአንድ ወንድ ልጅ አባት ሲሆኑ “ከአንድ ቤት አንድ ሰው ወደ ጦርነት መግባት አለበት፣ ካልሆነ እርዳታ አይሰጠውሙ” በተባለ ጊዜ አንዱ ልጃቸው በግዳጅ ወደ ውጊያ ማምራቱን በሀዘን ድባብ ውስጥ ሆነው ነግረውናል። አሁን በተደረሰው ስምምነት መሰረት “ልጄ ከዛሬ ነገ ይመጣል እያልኩ በሀዘንና በተስፋ እገኛለሁ” የሚሉት አቶ ገብረመስቀል ልብ በሚሰብር ሁኔታ እያለቀሱ ልጄ ካለ መንግስት ምላሽ ይስጠኝ ሲሉ … [Read more...] about በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው
በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ
የውጪና የውስጥ ደጋፊዎቹንና አይዞህ ባዮቹን፣ ለዘመናት ከኢትዮጵያ የዘረፈውን ገንዘብና የጦር መሣሪያ የተማመነው ት ህነግ በእብሪት ጦርነት ውስጥ በገባበት ወቅት የአክሱምን አየር ማረፊያ በግሬደር ማረሱ የቅርብ ጊዜ ፅታ ነው። ማሰብ የተሳነው ትህነግ ይህንን ያደረገው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና እና አየር ኃይል የአክሱምን ኤርፖርት ለጦርነቱ እንዳይጠቀሙበት በሚል የጨነገፈና ኋላቀር አስተሳሰብ ነበር። ጦርነቱ የተካሄደው ት ህነግ ፈጽሞ ባልጠበቀው፣ እነ ስዬ አብርሃ ባለቀሱበት የአየር የበላይነትና በድሮን ነበር። የአክሱም ኤርፖርት ግን ምንም ላይፈይድ ፈርሶ ቀረ፤ ሕዝቡ አሁን በውጤቱ እያማረረ ይገኛል። በከፍተኛ ደረጃ የከተማው የንግድ እንቅስቃሴ በቱሪዝም መስህቦች ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው በአጼ ዮሃንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የደረሰው ጉዳት የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ላይ … [Read more...] about በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ
“የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል
ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በችግር ውስጥ የሚገኙበት ደብረብርሃን ከተማ ከአዲስ አበባ ዙሪያና ከኦሮሚያ ክልል ተጨማሪ ተፈናቃዮችን በመቀበሉ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት አስታወቀ። በደብረብርሃን ከተማ ከ1 ዓመት በላይ በመጠለያ ጣብያ የቆዩ ተፈናቃዮች የሚገኙ ሲሆን እስከአሁን ድረስ የደብረብርሃን ከተማ ህዝብና ከአንዳንድ ድርጅቶች ውጭ መንግስት ተገቢውን ድጋፍ እያደረገላቸው ባለመሆኑ ለችግር በመጋለጣቸውን ተፈናቅዮች ቅሬታቸውን ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል። በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት የተፈናቃዮች አስተባባሪ አቶ አንተነህ ገብረእግዚአብሄር በተለይ ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፁት በከተማዋ ከሰዎች ተጠግተውና ቤት ተከራይተው የሚኖሩትን ሳይጨምር ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ በ6 መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች … [Read more...] about “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል
ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል
በጦር መሳሪያ በመታገዝ በተለያዩ ቦታዎች እየተንቀሳቀሱ የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 4 ግለሰቦች ከ20 ዓመት እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ተስፋዬ ጌታቸው፣ ተገኝ ሞቲ፣ ባይሳ ተስፋዬ እና አዱኛ ኦልጅራ የተባሉት ተከሳሾች በቡድን ተደራጅተው በለሊት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች እየተንቀሳቀሱ በጦር መሳሪያ የታገዘ የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ተከሳሾቹ በተደጋጋሚ ጊዜ በፈፀሙት በጦር መሳሪያ የታገዘ የዘረፋ ወንጀል መዝገብ ተደራጅቶባቸውና አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸው ጉዳያቸውን ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ጌታቸው በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት፣ 2ኛ ተከሳሽ ተገኝ ሞቲ በ23 አመት ፅኑ እስራት እንዲሁም … [Read more...] about ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል
የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ
የሀገሪቱ ም/ፕሬዝዳንትና ጠ/ሚኒስትርን ጨምሮ 10 ከፍተኛ ባለስልጣናት የተሰረቀውን ቆርቆሮ ወስደዋል ተብሏል። የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር ጎሬቲ ኪቱቱ ከቤት ክዳን ቆርቆሮ ዝርፊያ ቅሌት ጋር በተያያዘ ፋሲካን በእስር ቤት ያሳልፋሉ። ሚኒስትሯ ለእስር የተዳረጉት በሀገሪቱ የተፈፀመው የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች ዝርፊያ ላይ ተሳትፈዋል በሚል እንደሆነ ቢቢሲ አስነብቧል። የክልሎች ሚኒስትር ጎሬቲ ኪቱቱ በኡጋንዳ ሰሜን ምስራቅ ክልል ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች የተዘጋጀውን 14 ሺህ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል ነው የተጠረጠሩት። ሚኒስትሯ ባሳለፍነው አርብ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ እስካሁን የጥፋተኝነት ውሳኔ ባሳያልፍባቸውም የዋስትና መብት ግን ከልክሏቸዋል። 10 የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የተሰረቀውን የቤት ክዳን ቆርቆሮ … [Read more...] about የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ
ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው
በማዕድን ዘርፍ ለማልማት ፈቃድ ከወሰዱ 250 መካከል እየሠሩ ያሉት 8% ብቻ ናቸው ብዙ ሃሜታ የሚነሳበትን የመዐድን ሚኒስቴርን ሲመራ የነበረው ታከለ ዑማ በበርካታ የሌብነት ወንጀል ብዙ ሲባለበት ቢቆይም አገር ለቅቆ መውጣቱ ይታወቃል። የእርሱን ከአገር መልቀቅ ተከትሎ ከመዐድን ሚኒስቴር አካባቢ የሚሰሙት መረጃዎች መሥሪያ ቤቱ ምን ያህል ሲመዘበር እንደቆየ አመላካች ሆኗል። የተያዙት ግለሰቦችም ስለዚህ ጉዳይና እስከ መንግሥት መዋቅር ስለ ዘለቀውን የሌብነት መስተጋብርም የሚሉት ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል። በየቤኒሻንጉል ጉሙዝ በማዕድን ልማት ለመሰማራት ፈቃድ ከወሰዱ ከ250 በላይ አልሚዎች መካከል ወደ ሥራ የገቡት 20 ብቻ እንደሆኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ በሕገ ወጥ መንገድ ወርቅ ሲያዘዋውሩ የተገኙ 45 የውጭ አገራት ዜጎች … [Read more...] about ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው