ኢትዮጵያ የአየር ኃይሏን የመዋጋት አቅም በከፍተኛ ደረጃ ከሚያሳድጉ እና የቀጠናውን የኃይል ሚዛን ቀያሪ ከተባሉት ዘመናዊ የጦር ጀቶች በተጨማሪ 2 የኢሉሺን (Ilyushin Il-78) የአየር ላይ ነዳጅ መሙያ ጫኝ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከሩሲያ ጋር ስምምነት መፈራረሟን ወታደራዊ መረጃ ተንታኞች ገለጹ። ይህ ግዢ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋ ካደረጉት የ12 ሱኮይ (Sukhoi Su-35) ዘመናዊ የውጊያ ጄቶች ግዢ ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው። የመከላከያ ሚኒስቴር እና የጦር መሣሪያ ዝውውርን በቅርበት የሚከታተለው ሚሊተሪ ዋች መጽሔት (Military Watch Magazine) እንደዘገበው፥ ኢትዮጵያ እነዚህን የጦር መሳሪያዎች የገዛችው በሞስኮ በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ወቅት በተደረገ የቢሊዮን ዶላሮች ስምምነት ነው። … [Read more...] about ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው

