የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያን አስመልክቶ የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፦ ኢትዮጵያ በትናንትናው ዕለት መንግሥት አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን አስመልክቶ የሰጠውን መግለጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻሉን ያስታውቃል። ከዛሬ ጀምሮ ሥራ ላይ የሚውስው ይህ ማሻሻያ ኢትዮጵያን ተወዳዳሪ ወደሆነና በገበያ ላይ ወደተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት እንደሚያሸጋግራትና በኢኮኖሚ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ተንሰራፍቶ የቆየውን የማክሮ ኢኮኖሚ አለመረጋጋትና መዛባት እንደሚያሻሽል ይታመናል። የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያው በአዲሱ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መሠረት የሚተገበር ይሆናል። ይህ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀ ግብር ላይ የተመሠረተና … [Read more...] about የዘመናት ማነቆዎችን የበጣጠሰውና ተስፋን የሰነቀው የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት ማሻሻያ
News
ዜና
ቆሻሻ የሚጥሉና ዘንባባ የሚገጩ ቅጣት አንሷል ተባለ
በአዲስ አበባ በየቦታው ቆሻሻ ለሚጥሉና በቅርቡ የተተከሉትን ዘንባባዎች ለሚገጩ የሚከፈለው ቅጣት ያነሰ መሆኑን በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ። ተግባሩን ለመከላከል የሌሎች አገራት ልምድ ተግባራዊ እንዲደረግና ጥፋቱን ለመቀነስ የቅጣት መጠኑ መጨመር እንዳለበት ነው ነዋሪዎች የተናገሩት። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለከተሞች የሚገኙ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጋር ባደረገው ኢመደበኛ ጥናት ሁሉም ተጠያቂዎች የሰጡት ምላሽ ጥፋቱን በሚፈጽሙ ላይ የተበየነው ቅጣት ከዚህ መጨመር እንዳለበት ነው። ሌላው የሰጡት ምላሽ የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በማጥናት በአገራችን ላይ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደ ጥንቃቄ የሰጡት ምላሽ ሁሉም ሰው አውቆ ዘንባባ ስለማይገጭ እንደ አገጫጩ ምክንያትና ዐውድ ቅጣቱም በዚያው መልኩ አጥፊዎችን ከአደጋ አድራሾች … [Read more...] about ቆሻሻ የሚጥሉና ዘንባባ የሚገጩ ቅጣት አንሷል ተባለ
በእስክንድርና በዘመነ ሽኩቻ ፋኖ አንድ መሆን የማይችል ሆኗል – ኮሎኔል አሰግድ
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰግድ መኮንን እጁን ሰጠ በአማራ ክልል በርካታ የታጣቂ ቡድን አባላት እና አመራሮች በመንግሥት የቀረበላቸውን የሰላም አማራጭ ተቀብለው ሰላማዊ ሕይወት እየመሩ መሆኑን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታውቋል፡፡ የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይሉ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩትን የፀጥታ ችግሮች በንግግርና በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በመንግሥት ለታጣቂ ቡድን አባላት እና አመራሮች በተደጋጋሚ የሰላም አማራጮች ሲቀርቡ ቆይተዋል፡፡ ይሁንና በክልሎችም ሆነ በፌዴራል መንግሥት እየቀረበ ያለው የሰላም አማራጭ እንዳይሳካ እና ወደ መሬት እንዳይወርድ በተለይም ደግሞ ውጭ ሆነው በትግሉ ስም ጥቅም የሚያግበሰብሱ አንዳንድ ጽንፈኛ … [Read more...] about በእስክንድርና በዘመነ ሽኩቻ ፋኖ አንድ መሆን የማይችል ሆኗል – ኮሎኔል አሰግድ
ሳይታገት ታግቻለሁ ብሎ ከባለቤቱ 500ሺ ብር የተቀበለው ግለሰብ ተያዘ
የ63 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ እና የ5 ልጆች አባት የሆነው አቶ ገብረ ተንሳኢ ተክላይ ከወይዘሮ ዘነበች በርሄ ጋር ለ14 አመታት በትዳር ተጣምረው በአሶሳ ከተማ የንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው 4 ልጆችን አፍርተዋል። በትዳር ህይወታቸው ውስጥ ምንም አይነት እንከን እንደሌለ የሚገልፀው አቶ ገብረተንሳኢ ተክላይ ወይዘሮ ዘነበችን ከማግባቱ በፊት አንዲት ሴት ልጅ እንዳለችውና እሷም ለብቻዋ አዲስ አበባ እንደምትኖር በመግለፅ ይህንን እኩይ ተግባር ለመፈፀም የተነሳሳውም የግል ልጁን ለመርዳት እንደሆነ ተናግሯል። ከሚኖርበት አሶሳ ከተማ ወደ ነቀምት ከተማ በመጓዝ "ኦጌቲ" በሚባል ሆቴል ውስጥ ለሁለት ቀናት አልጋ ይዞ በመተኛት ከሆቴሉ አስተናጋጆች የ21 ዓመት ልጅ የሆነውን ወጣት ገመቹ ዮናስን በመግባባት የአጋችና ታጋች ድራማውን አብሮት እንዲሰራና ለዚህም ታግቻለሁ ብሎ ከሚላክለት ብር … [Read more...] about ሳይታገት ታግቻለሁ ብሎ ከባለቤቱ 500ሺ ብር የተቀበለው ግለሰብ ተያዘ
ቱሪዝም በአማራ ክልል ሊቆም ነው
"... አሁን ቱሪስት የለም" የላሊበላ ነዋሪ እስከ 2 ቢሊዮን የሚጠጋ ብርም ከዘርፉ ይገኝ ነበር የአማራ ክልል ቱሪዝም በግጭቱ ምክንያት ሥራ ለማቆም መቃረቡን የክልሉ የባህልና የቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ‼️ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የዐማራ ክልልን ይጎበኛሉ ተብለው ከታቀዱት የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ቁጥር የመጡት 20 በመቶ ብቻ መኾናቸውን የገለጸው የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ፣ የክልሉ ቱሪዝም በእጅጉ በመዳከሙ ሥራ ለማቆም መቃረቡን አስታውቋል፡፡ የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር አየለ አናውጤ ትናንት ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በክልሉ ተለዋዋጭ ገጽታ እያሳየ የቀጠለው የትጥቅ ግጭት፣ “ዘርፉን ጨርሶ ለማስቆም እየተቃረበ ነው፤” ብለዋል፡፡ በቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶችም፣ በግጭቱ ሳቢያ ከሥራ ገበታ ውጭ መኾናቸውን አመልክተዋል፡፡ (VOA) ጥር 7 2016 የታተመው … [Read more...] about ቱሪዝም በአማራ ክልል ሊቆም ነው
“መፈንቅለ መንግሥት በጭራሽ አይሳካም”
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? "አጠቃላይ የሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች በዋና ዋና አመላካቾች በምን ደረጃ ላይ ናቸው ?በተለይ የኑሮ ውድነት እየከፋ ነው።የዋጋ ንረትን ደግሞ ማረጋጋት አልተቻለም።በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ማህበረሰብ እና የመንግሥት ሰራተኛው መኖር አቅቶታል።መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው።ስለሆነም እንደ መንግሥት በቀጣይ አመታት እነዚህን ተግዳሮቶች ለመወጣትና የህዝቡን ጥያቄ ለመፍታት በምን ደረጃ ታቅዷል።" (አቶ አቤነዘር በቀለ - የተ/ም/ቤት አባል) " ... ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል " - የም/ቤት አባል የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?አቶ አብርሃም በርታ (የተ/ም/ቤት አባል) ፦ "ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና አንዳንድ ዓለም … [Read more...] about “መፈንቅለ መንግሥት በጭራሽ አይሳካም”
ፖሊስ: የተሰረቁ ስልኮቻችሁን መጥታችሁ ውሰዱ
ፖሊስ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ባደረገው ክትትል ግምቱ 150 ሺህ ብር የሚያወጣን ሞባይል ስልክን ከሌባ ላይ የገዛችን ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ንብረቱን ማስመለሱን አስታወቀ፡፡ ግለሰቧ ከወንጀለኞች በተለያየ ጊዜ የገዛቻቸው ልዩ ልዩ ሞባይል ስልኮችን፣ ላፕቶፖችንና ታብሌት ይዞ ምርመራው መቀጠሉን አዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆል፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው አለምነሽ ፕላዛ አካባቢ አንድ ግለሰብ ግምቱ 150 ሺህ ብር የሚያወጣ አይነቱ አይፎን ፕሮ ማክስ ሞባይል ስልክ መቀማታቸውን በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለአደይ አበባ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታሉ። የግለሰቡን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ፖሊስ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በቴክኖሎጂ በመደገፍ ባደረገው ክትትል የተሰረቀው ስልክ አራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ከሚገኝ አንድ የሞባይል … [Read more...] about ፖሊስ: የተሰረቁ ስልኮቻችሁን መጥታችሁ ውሰዱ
አቡነ ሉቃስ 6 ዓመት ተፈረደባቸው፤ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላል
አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት የቅስቀሳ ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉበት ድንጋጌ በሥድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ። ከፈጸሙት ወንጀል አኳያ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ። የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ሕገ-መንግሥታዊና በሕገ-መንግሥት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች የሚመለከተው ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በአቡነ ሉቃስ ላይ ከሦስት ወራት በፊት÷ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258 (ሀ) ሥር እና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251 (ሐ) የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ተከሳሹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የምሥራቅ … [Read more...] about አቡነ ሉቃስ 6 ዓመት ተፈረደባቸው፤ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላል
ትሕነግ ሕጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶት ብልጽግናን ሊቀላቀል ይችላል ተባለ
ትሕነግ ሌላ ሕንፍሽፍሽ ይጠብቀዋል በጌታቸው አሰፋ የሚመራው ጽንፈኛ የክልል ፓርቲ ሆኖ ሊቀጥል ይችላል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህወሓት መልሶ ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኝ የሚያስችል የአዋጅ ማሻሻያ ወደ ፓርላማ መራ። ውሳኔው ትሕነግን ሕጋዊ ዕውቅና ሰጥቶ ወደ ብልጽግና ለመቀላቀል የታሰበ ነው የሚል ግምት ሲሰጠው በትሕነግ ውስጥ አንጃ ፈጥረው ፓርቲውን ቀውስ ውስጥ የከተቱት እነ ጌታቸው አሰፋና ሞንጆሪኖ በክልል የተወሰነ ጽንፈኛ ፓርቲ ይዘው ሊቀሩ ይችላሉ እየተባለ ነው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት “ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ” ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ቡድኖች መልሰው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ለመመዝገብ የሚያስችላቸውን ድንጋጌ የያዘ የአዋጅ ማሻሻያን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ። የሕጉ ዋና ዓላማ ትሕነግን ወደ ሕይወት ለማምጣት … [Read more...] about ትሕነግ ሕጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶት ብልጽግናን ሊቀላቀል ይችላል ተባለ
ድምጽ ዓልባ እና ናፍጣም ሆነ ቤንዚን የማይጠቀም ጄኔሬተር የሠራው ኢትዮጵያዊ ወጣት
ፈዴሳ ሹማ ይባላል። ተወልዶ ያደገው በቄለም ወለጋ ሲሆን በከተማው ውስጥ በኤሌክትሪክ ጥገና ሙያውም ብዙዎች ያውቁታል፡፡ ሥራው ጥገና እንደመሆኑ የመብራት መጥፋትና መቆራረጥ ሥራውን ብዙ ጊዜ ያስተጓጉልበታል። ችግር ብልሃትን ይወልዳል እንዲሉ ወጣቱ መላ በመዘየድ ከብዙ ጥረት በኋላ አንድ ግዜ ቻርጅ ተደርጎ እስከ አንድ ዓመት ድረስ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቴክኖሎጂ እውን አደረገ። ቴክኖሎጂውንም ይበልጥ አዘምኖ መሥራት ችሏል። ቴክኖሎጂው የመብራት አገልግሎት ከመስጠቱ ባለፈ ሞባይል፣ ለቴሌቭዥን፣ ፍሪጅና የትኛውንም ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ መጠቀሚያዎችን ቻርጅ የሚያደርግ፣ የሚያንቀሳቅስና በገመድና ገመድ ዓልባ ቴክኖሎጂ መጠቀም እንዲቻል ተደርጎ የተሠራ ነው። አንዴ የያዘውን ኃይል ሪሳይክል እያደረገ ራሱን ቻርጅ ከማድረግ አልፎ ለረዥም ጊዜ ኃይል ማመንጨት የሚችለው … [Read more...] about ድምጽ ዓልባ እና ናፍጣም ሆነ ቤንዚን የማይጠቀም ጄኔሬተር የሠራው ኢትዮጵያዊ ወጣት