በማናቸውም የአገሪቱ ባለስልጣናትና ተቋማት ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ ይፋ የማያደርጉት የአገር ውስጥ የጫት ፍጆታና ገቢ በውስጡ ከፍተኛ ዝርፊያ ይከናወንበታል። ከዝርፊያው ጋር በተያያዘ አቶ መለስን ጨምሮ ከፍተኛ ሹማምንትና ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን በቅድሚያ ስማቸው ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው። የጎልጉል የኦህዴድ ምንጮች የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትርና የንግድና ኢንዱስትሪ ምክትል ሚኒስትሩ በጫት ንግድ ዙሪያ የሚጫወቱትን ሚና አጋልጠዋል። ያገኘነውን መረጃ ለንባብ ያመች ዘንድ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
የጫት ንግድ ዝምድና – ወ/ሮ ሱራ
በደርግ የአገዛዝ ዘመን ወደ ጅቡቲ ኤክስፖርት መደረግ የጀመረው ጫት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የወያኔ አባላትን ቀልብ አልሳበም ነበር። ባለስልጣናቱና የቀድሞው ታጋዮች ጫት ተጠቃሚ ስላልነበሩ ስለ ጫት ንግድና ከፍተኛ ፍጆታ እንዳለው መረጃው የላቸውም። እንደውም ጫት “የሚበሉ” ሲመለከቱ ይገረሙ ነበር።
ወ/ሮ ሱራ ጅጅጋ ይኖሩ የነበሩ የሶማሌ ተወላጅ ናቸው። በቅርበት የሚያውቋቸው የሃርጌሳ ሶማሌ ጎሳ አባል የሆኑ ሙሉ የሶማሌ ዜግነት ያላቸው ሴት እንደሆኑ ይናገራሉ። ወይዘሮዋ የጫት ንግድ ስራ የጀመሩት ጅጅጋ ሲሆን ከቀን ወደ ቀን ገቢያቸውን በማሳደግ ወደ ሶማሌ ማጓጓዝ ጀመሩ።
የኦጋዴንን በረሃ በሌሊትና በቀን እያቆራረጡ ሶማሌ የሚገቡትን ላንድ ክሩዘር መኪኖች በመጠቀም ሱራ የጫት ንግዳቸውን አስፋፉ። ሲሉም ጅጅጋ የሚመጣላቸውን ጫት ከመረከብ ይልቅ ራሳቸው ከሐረር ዙሪያና ከአወዳይ አካባቢ በቀጥታ ከገበሬዎች በመግዛት ወደ ጅጅጋና ወደ ሶማሌ በበረሃ በማስረግ ሃብት ሰበሰቡ።
በኋላም ህጋዊ ፈቃድ አውጥተው ወደ ሶማሊያ ሃርጌሳ ጫት ላኪ ሆኑ። ከድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያ ዘወትር ጫት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በማመላለስ የተወለዱበትን አገር የጫት ኮታና ንግድ ለብቻቸው ተቆጣጠሩ። ሃብታቸው እየገዘፈ ሲመጣ የማጓጓዣ ወጪያቸውን ለመቀነስ የራሳቸውን አውሮፕላን ለመግዛት ፈቃድ ጠይቀው ተፈቀደላቸውና በራሳቸው አውሮፕላን ጫት ማጋዙን ተያያዙት። ሃብታቸው ገዘፈ። የጫት ማከፋፈያ መደብ ላይ ተቀምጠው አንድና ሁለት እስር ሲቸረችሩ የነበሩት ሱራ ከበሩ።
የጫት አቅርቦት ሞኖፖሊ
ሱራ የገንዘብ አቅማቸው ሲያድግ ወደ ምዕራብ ሐረርጌና ምስራቅ ሐረርጌ ክልላቸውን አሰፉ። አርሶ አደሩ ውስጥ በመግባት የጫት ማሳዎችን በኮንትራት በመግዛት በሞኖፖል ያዙት። የተሰበረ ጫት ከመግዛት ይልቅ ማሳውን በሞኖፖል በመያዝ በሚፈልጉት መጠን ማግበስበስ ያዙ። በየወረዳው ወኪሎቻቸውን አስቀምጠው ሥራውን ተቆጣጠሩት። የቀድሞውን የደርግ መንግስት የደህንነት ሰዎችና ኮማንዶዎች አደራጅተው የመንግስት ያህል ጡንቻቸውን አጎለበቱ። ሚዲያ እንኳን አጠገባቸው ሊደርስ ቀርቶ ፈራቸው። የሚታጀቡና ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርጉላቸው ባለሃብት ሆኑ። ጉልበታቸውን ተማምነው በሊዝ የያዙትን የጫት ማሳ ከገበሬ ማኅበራት አመራሮች ጋር በመሆን ወደፊት በሚከፈል እዳ ወደ ሶማሌና በቀን ሁለትና ከዛም በላይ በረራ በማድረግ ከበሩበት። የኦህዴድ የንግድ ድርጅት የሆነውን ቢፍቱ የጫት ንግድን ሳይቀር ጉሮሮው ላይ ቆመው አንገዳገዱት። በኋላ ላይ እንዳይሆን አድርገው በብር አሽመደመዱትና ሶማሌ ውስጥ ከጀመረው የጫት ንግድ አባረሩት። ኦሮሚያና አስተዳደሮቹ የህዝባቸውን ብሎም የፓርቲያቸውን ጥቅም እንኳን ማስከበር ሳይችሉ ቀሩ። አሁን ድረስም እንደዛው ነው።
እልህ ውስጥ የገቡት የኦህዴድ ሰዎች የፖለቲካ ስልጣናቸውን በመጠቀም ሱራን እጃቸውን ለመጠምዘዝና የሶማሌን የጫት ኤክስፖርት ለመጠቅለል ዘመቻ ጀመሩ። በኦሮሚያ የጫት መቆጣጠሪያ ኬላና በአርሶ አደሮች ማኅበራት አማካይነት ከአገር የሚወጣውን የጫት መጠን በማስላት ከጫት ኤክስፖርት የሚገባውን የውጪ ምንዛሬ መረጃ በማመሳከር ከፍተኛ ማጭበርበር እንደሚካሄድ ለፌደራል መንግስት አሳበቁ። ኦህዴድ ሶማሌ ጫት ንግድ ውስጥ ለመግባት ሞክሮ እንዴት ማጅራቱን እንደተመታና እንዴት ጅቡቲ ውስጥ ተወትፎ እንደቀረ በሌላ ዜና እንመለስበታለን።
ሱራ ከየአቅጣጫው የሚነሳባቸውን ተቃውሞና ቁጥጥር እንዴት እንደሚመክቱ ኦህዴድ ውስጥ መነጋገሪያ ሆነ። በከፍተኛ ደረጃ ያሉ የኦህዴድ አመራሮችና ባለስልጣናቱ ከጫት ንግዱ በስተጀርባ ያለውን አሻጥር ቢያውቁም ሊጋፉት የማይችል ስለሆነባቸው ቀረጥ ላይ አተኩረው በመስራት ክልሉ ከጫት በኪሎ ስድስት ብር ቀረጥ እየሰበሰበ እንዲቆይ ማሳሰቢያ ሰጡ። በዚህም ከሚመዘበረው የኬላ ገቢ ወጪ ቀሪ ክልሉ በዓመት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እየሰበሰበ ቆየ። በመካከሉ ሱራ በዘረጉት ሰንሰለት አማካይነት ኬላ እንዲነሳ የጀመሩት ዘመቻ በድል መጠናቀቁ ይፋ ሆነ። ኦሮሚያ ላለፉት አምስት ዓመታት በየዓመቱ ሲያገኝ የነበረውን ገቢ ተነጠቀ። በወቅቱ ውሳኔውን ተከትሎ የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ውሳኔውን ተቃወመ። በኦሮሚያ የቢሮው ሃላፊ በያዙት አቋምና በሼኽ መሐመድ አላሙዲ ድርጅቶች ላይ በያዙት አስገድዶ ግብር የማስከፈል ርምጃ ተዳምሮ መጨረሻቸው ወህኒ ሆነ።
ኬላ ተነሳ — ቀረጡን ሱራ መሰብሰብ ጀመሩ
የጫት ኬላ እንዲነሳ ቀደም ሲል በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትሩና በንግድና ኢንዱስትሪ ምክትል ሚኒስትሩ አማካይነት የውጪ ምንዛሪ ገቢ እንዲጨምር በሚል ሰበብ ሃሳብ ቀረበ። ያለ ቁጥጥር ጫት ቢወጣ የውጪ ምንዛሬ ገቢውን ይጨምራል ተብሎ ዓይን ያወጣ ክህደት ክልሉ ላይ ተበየነ። ክልሉ ሃሳቡን በመቃወሙና በክልሉ ቀረጥ የመሰብሰብ መብቱን ስለሚጋፋ ተግባራዊ ሊሆን አይገባም ቢባልም ከሱራ ጀርባ ያሉት ክፍሎች በኦሮሚያ በኩል የቀረበውን ቅሬታ ወግድ አሉት። ሱራም ባሰማሯቸው ጉዳይ አስፈጻሚዎች አማካይነት ኬላው እንደሚነሳ ሲያስነግሩ የነበረው እውን እንደሚሆን ፉከራው ቀጠለ። በመጨረሻም አቶ መለስ የጫት ኬላ እንዲነሳ የቀረበውን ሃሳብ አጸደቁትና ኦሮሚያ ከጫት ቀረጥ ሲያገኝ የነበረውን ብር ትቶ እጁን ታጥቦ የበይ ተመልካች ሆነ።
አስገራሚ ተብሎ በመረጃው ውስጥ የቀረበው ጉዳይ የጫት ኬላው ቢነሳም ጫት ለወ/ሮ ሱራ የሚያቀርቡት አርሶ አደሮች ሂሳብ ሲሰላላቸው በኪሎ ስድስት ብር “ቀረጥ” በሚል እንዲከፍሉ መደረጋቸው ነው። ቀረጡ የሚሰበሰበው ሱራ ባደራጁዋቸው ክፍሎች ሲሆን፣ ለሚሰበሰበው ብር ማስረጃ አይቀርብም። መረጃው እንደሚለው ኦሮሚያ እንዳይሰበስብ የተከለከለውን ቀረጥ ወ/ሮ ሱራ ሰብስበው የት ያደርሱታል ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል።
“ኬላ ከተነሳና ቀረጥ የምንከፍለው ለማን ነው?” በሚል አርሶ አደሮች ሲጠይቁ “ለባለስልጣኖች ይከፈላል” የሚል መልስ እንደተሰጣቸው የደደርና አካባቢውን አርሶ አደሮች በመጠቀስ አግራሞቱን የሚገልጸው ጥቆማ፣ በንግድ ትስስር ውስጥ አሉበት የተባሉትን ባለስልጣናት ይጠቁማል። መረጃው ለኦህዴዱ የንግድ ድርጅት ለቱምሳ ኢንዶውመንት የቦርድ ሊቀ መንበር አቶ ግርማ ብሩ ደርሷቸው እንደነበር አስረድተዋል። አቶ ግርማ ራሳቸው በከፍተኛ ንግድ ውስጥ ስለሚሳተፉ ዝምታን መምረጣቸውንም አመልክቷል።
የሱራ ኃይል
ሱራ የፈጠሩት ኃይል በቀላሉ የሚደፈር አይደለም። በቅርንጫፍ በተበጀ ድርጅት ይሁን በሽርክና በውል ባይታወቅም ሱራ የወ/ሮ አዜብ የቅርብ ወዳጅነት የመሰረቱት አሁን አይደለም። የጫት ንግድ ገቢ ጆሯቸው የዘለቀው ወ/ሮ አዜብ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትሩ ጋር ወዳጅነት የተጠናከረበት ዋና ምክንያት ይኸው ሱራ የዘረጉት መስመር እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርብ ነን የሚሉት የኦህዴድ ሰዎች ይናገራሉ።
የንግድና ኢንዱስትሪ ምክትል ሚኒሰትርና የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትሩ የተንቦጫረቁበት የጫት ንግድ በወ/ሮ አዜብ ሾፌርነት ታግዞ ከኦሮሚያ ጉሮሮ ላይ የቀረጥ ገቢውን ነጠቀው። የኦህዴድ ሰዎችም ሆኑ የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ትግል በነነ። ወ/ሮ አዜብ ዳር ሆነው በጫት ስራ ላይ ያሰመሯቸው የመከላከያ ሹማምንትና ከፍተኛ የጦር አመራር በገንዘብ እየተራጩ ነው። ኦሮሚያ የክልሉ ቢቀር የህዝቡን መብት ማስከበር አቅቶት እስካሁን በገባሪነት ይኖራል።
“ገንዘብ ያላቸው ከክልል በላይ ገዝፈው የሚዋጓቸውን ማባረርና ማሳሰር ችለዋል። የቀሩትም በስጋት ተወጥረዋል። ኦሮሚያን እየመራን ያለነው እንዲህ እንመስላለን” የሚል ሃረግ ያለበት መረጃ፣ ሱራ መንግስትና ውስን ገቢ በሌለበት አገር የሃርጌሳን ህዝብ ማስተዳደርና ስራ ማሰራት መቻላቸውን ያደንቃል። የኢትዮጵያ አየር መንገድን ገበያ ሳይቀር የተሻሙት ሱራ ካሉበት ቦታ ለዚህ ጽሁፍ ምላሽ እንዲሰጡ፣ መልስ ሲሰጡም በኪሎ ስድስት ብር ሂሳብ የሚቆረጠው የቀረጥ ብር ስሌቱና ክፍፍሉን በመቶኛ በማስቀመጥ እንዲጠቁሙ ይጠይቃል።
ከዝግጅት ክፍሉ
የኦህዴድ የንግድ ተቋም ቱምሳ ኢንዶውመንት ጫት እነግዳለሁ ብሎ ሃርጌሳ ገብቶ የደረሰበትን ኪሳራና፣ ፑንት ላንድ ብቸኛ ጫት አቅራቢ ለመሆን በረሃ ለበረሃ ተንከራቶ መጨረሻ ላይ ያፈሰውን ቅሌትና የቅሌት ድራማ እናስከትላለን። ለጊዜው አሁን በቀረበው በዚህ ጽሁፍ ላይ ማንኛውም ማስተባበያና የተቃውሞ ጽሁፍ ማቅረብ እንደሚቻል አስቀድመን ለመግለጽ እንወዳለን።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Oromo man says
This drama (collecting income to EPRDF’s member) is not only matters oromia,but also z mother land Ethiopia,my self,you….. Knowing z truth makes us to wakeup! Thanks to golgul,realy I apperciate golgul!
hootoo says
In spite of extremely limited resource as well as Woyanes closed door for free flow of information you are doing great job. I admire your clarity as well as investigative journalism. But what do you think the future of Chat industry during such volatile era of Mrs Zenawi’s marginalization?
Firdu Jemere says
Good job folks. Move on.
abebe says
thanks
Its a shame… i know the case closely. i have been to Awaday recently. For how do the Oromo People live in this way? I’m sure the time will come when an Oromo really administers itself… if you see the Harar Oromo living under abject poverty …
olad guled says
Where have you got the fact?
This article is completely wrapped with untrue story and I wonder how this website that I thought has a strong potential and capacity to become one of the best sources of reliable information and news ended up in becoming a mouth-piece of those who would never sleep a single second to depict false picture.
Had I not known suhura personally, I would have believed every word of the writing. However, having known suhura for a long period of time, I was completely surprised to read such false assertion in disbelief. It was not only me but anyone who lived in jijiga in the mid of 90s could be a living witness what this hard working Somali Ethiopia used to be, how she built a successful qat business. In fact, she is one of the most successful Ethiopian Somali business women. In a region where gender inequality is widespread, finding an accomplished Somali woman entrepreneur should have been taken as role model. Rather suhura’s hard work and entrepreneurship was taken wrongly and she was accused as a foreigner.
To my knowledge and as anyone from jijiga town could easily corroborate, She was born and brought up in jijiga. The statement which says she is a Somalian citizen is totally a false statement. Suhura has built here business from a scratch. Even I used to buy from her when she was one of those local Somali girls who were engaged as a street vendor qat business. Here meteoric raise was due to her strong personality and hard work she put on to it. In addition, in the past qat business was used to be dominated by Somali men. There was strong rivalry and it was hard for any Somali man to continue dominating qat business for more than a year. However, her gender has helped her to build a successful qat business because Somali society would rarely hassle a woman. When I was living in jijiga in 1994, suhura was a street vendor, at the same time she used to send a small amount of qat to Somaliland. However, she became famous and started to export in a bulk. During this time she even used to run open market a small stall in of jigjig town centre and sale qat to local people.
The Somali regional state and federal officials had once tried to take away the business from her. In this attempted these politicians attempted to open another qat export venture and instructed custom officers to delay taxing of her qat. The scheme to stop suhura from exporting qat, collapsed after the custom office in jijiga failed to collect tax. suhura approached one of the federal defence force based in jijiga and eloquently made him understand the ill-fated scheme of the officials. The next morning she was allowed to take her qat after the custom officers delayed her to tax her goods. The federal defence force commander gave order to the defence force on the check point to allow suhura to take her goods If the custom officers failed to collect tax within an hour. Suhura used to pay a lot of tax both for oromia and somali regional state. As you might understand qat trade to Somaliland comes under the federal jurisdiction. It was not a regional state mandate. As a result, it used to be taxed by export tax by the federal custom office known as gumuruk. Both oromia and somali regional state get a huge amount of annual budget from the federal government through the money collected from this taxation. Although the fact was as I state above, I do not understand how this respectable website print such kind of falsified report. As Ethiopia wanted to increase its foreign exchange, it enacted a law that exempt goods for export from internal tax. The hard currency Ethiopia get from qat export directly contribute to the overall country’s economic development. Suhura pays more than $ 34 million us dollar as a tax to federal government. In recognition of her huge contribution to the national coffer she was awarded the best woman trader in Ethiopia by the late prime minister of Ethiopia, Meles zenawi. I have no any vested interest to defend suhura or any other person. However, it is unfair to drag an innocent woman who has helped the Ethiopian to achieve huge foreign currency that used to be going directly to individuals and impacted on the country. As many people from this part of Ethiopia know suhura well, it would have been important if the editor had attempted to verify the truthfulness of the story before publishing in this website. I do not want to consider you as a useless website because you have just made this mistake. It would be surprising if you do not print this comment on your website to give the other version of the story. Many people have different motive behind giving such fabricated story to the website. If you want further info please do not hesitate to contact me.
If you want to interview suhura and other people who know her I would be cooperate with to make the connection you need. Please do not print a story that has an ulterior motive behind.
One of concerned Ethiopia
Olad Guled
Editor says
Dear olad guled – many thanks for taking your time and sending us this comment. Even though you commented in English, the thoroughness of your response has convinced us not doubt your brilliant understanding of Amharic. So we are replying back in Amharic, taking also into consideration that the article is originally written in Amharic.
1. የዜና ትንተናውን በተመለከተ መረጃውን ያገኘነው እጅግ ታማኝ ከሆነ ምንጭ መሆኑን ያለምንም ጥርጥር ልናሳውቅ እንወዳለን፡፡ እንደ እውነቱም ከሆነ የመረጃው አስተማማኝነትን በተመለከተ እርስዎ በጻፉት አስተያየት ላይ የተጠቆመ ነው፡፡ ከጻፍነው ዝርዝር ውስጥ በጣም በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ አስተያየት መስጠትዎ አብዛኛው የመረጃ ክፍል ተዓማኒ መሆኑን በራሱ ያረጋገጠ መሆኑን እርስዎ ምስክር ነዎት፡፡
2. የወ/ሮ ሱራን የጫት ንግድ በተመለከተ ካለን መረጃ አኳያ ሁሉንም አላወጣነውም – ወደፊት በዝርዝር የምንመለስበት ስለሆነ፡፡ ዓላማችን ስም ማጥፋት ወይም ዜጎችን በሃሰት መወንጀል ወይም ማስወንጀል እንዳልሆነ ሥራችን ምስክር ነው፡፡ የወ/ሮ ሱራን የጫት ንግድ በተመለከተ በጽሁፉ ላይ በዋንኛነት ያሰፈርነው ተገቢው ግብር አይከፈልም ነው እንጂ ወይዘሮዋ በድፍኑ ግብር አይከፍሉም አላልንም፡፡ በመሠረቱ ማንም ዜጋ ለሚያከናውነው የንግድ ተግባር ግብር መክፈል ግዴታው እንጂ ለብቻው ተነጥሎ የሚያስመሰግነው ተግባር አይደለም፡፡ ግብር መክፈልን አስመልክቶ ቤንጃሚን ፍራንክሊን ሲናገሩ ‹‹በህይወታችን እርግጠኛ የሆንባቸው ነገሮች ሞትና ግብር መክፈል ናቸው›› ብለው ነበር፡፡ የሰው ልጅ ሟችነት እንደማያስደንቀን ሁሉ ግብር መክፈልም እንዲሁ ነው፡፡ ስለሆነም የወ/ሮ ሱራን የጫት ንግድ በተመለከተ በኤርፖርት በኩል የሚላከውና በመኪና የሚወጣው የጫት መጠንና ዝርዝር መረጃ አለን – ያንን ወደፊት እንዳስፈላጊነቱ የምናወጣው ይሆናል፡፡ ላሁን አስፈላጊ ሆኖ ስላላገኘነው ነው በዚህ ጸሁፍ ላይ ያላካተትነው፡፡ ዋናው የመከራከሪያ አጀንዳችን በየብስና በአየር የሚወጣው ጫትና የሚከፈለው የቀረጥ መጠን በዶላር ተመጣጣኝ አይደለም – ብዙ ሙስና ይሰራበታል ነው፡፡
3. በአስተያየትዎ ወ/ሮ ሱራ ከችርቻሮ ንግድ ተነስተው እዚህ መድረሳቸውን ጠቁመዋል – እኛም እኮ በጽሁፋችን ይህንኑ ነው ያነሳነው – እንዲያውም አድንቀናል፡፡ ወይዘሮዋ በአቶ መለስ መመስገናቸውንና መሸለማቸውን በተመለከተ እንዲያውም አቶ መለስ ከማመስገንና ከመሸለም አልፈው ህጋዊው የኦሮሚያ ኬላ እንዲነሳ እና ለኦሮሚያ መግባት የነበረበት የቀረጥ ገቢ ወደ ወ/ሮ ሱራ እንዲገባ በፊርማቸው ጭምር አጽድቀውላቸዋል – ነፍሳቸውን ይማርና፡፡ በጽሑፉ ላይ እንዳመለከትነው የጫት ኬላዎች ተነስተዋል፤ ነገር ግን ኬላዎቹ ቢነሱም ገበሬው አሁንም ቀረጥ መክፈሉን አላቋረጠም፡፡ ጥያቄው ኬላ ከተነሳና ቀረጥ ከቆመ በኋላ ገበሬው ለምንድነው አሁንም ቀረጥ የሚከፍለው? ይሁንና ይከፈል ብንልም የሚከፈለው ገንዘብ የት ነው የሚሄደው? ስለጨዋነትና ታማኝነት ያነሱትን ሃሳብ ከልብ እናደንቃለን ሆኖም ግን በክልሉ ቀረጥ የመሰብሰብ ሕገመንግሥታዊ ሥልጣኑ ተገፍፎ ቀረጥ መሰብሰብ ስለተከለከለው ክልልና ስለ ኦሮሚያ ኬላዎች መነሳት አንዳችም ሃሳብ አልሰነዘሩም፡፡ ይህንን እንዴት ያዩታል? የጻፍነው ሃሰት ነው? ገበሬው አለአግባብ ስለሚከፍለው ቀረጥስ ምን ይላሉ?
4. የወ/ሮ ሱራን ትውልድ አስመልክቶ ያነሱት ሃሳብ እኛም ያልካድነው ነው፡፡ ክልሉ ከሱማሌ ጋር ካለው ኩታ ገጠምነት በአካባቢው ያሉት ነዋሪዎች የሁለቱንም አገሮች ነዋሪነት እንዳስፈላጊነቱ የሚጠቀሙበት ሁኔታ እስካለ ድረስ በልደት ሰርተፊኬት ያልተረጋገጠ የትውልድ ቦታ ይህ ነው ብሎ ለመጥቀስ አስቸጋሪ ስለሆነ እኛም በተወሰነ መልኩ ስንጽፍ ክፍተት ሰጥተን መጻፋችን ከዚሁ አኳያ እንደሆነ እርስዎም ሆኑ አንባቢ ሁሉ የሚያስተውለው ይመስለናል፡፡ በነገራችን ላይ የኢህአዴግ የዘር ፖለቲካ ‹‹የዚህ ክልል የዚያ ክልል፤ የዚህ ጎሣ የዚያ ጎሣ›› እያለ ሊከፋፍለን ሞከረ እንጂ የኢትዮጵያችን ልዩ ውበት በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች እንደዚህ ዓይነት ማንነት መላበሳቸው መሆኑን እርስዎም የሚዘነጉት አይመስለንም፡፡ ሆኖም በማስረጃ የተረጋገጠ ሰነድ ወይም መረጃ ካለዎት ለመቀበል ዝግጁ መሆናችንን ልንገልጽልዎት እንወዳለን፡፡
በመጨረሻም የወ/ሮ ሱራን የጫት ንግድ በተመለከተ እርስዎ ተገቢ መረጃ ሊሰጡን እንደሚችሉና ራሳቸውንም ወ/ሮ ሱራን ጨምሮ ሌሎችንም ሊያገናኙን እንደሚችሉ የገለጹትን ሃሳብ ከልብ እናደንቃለን፤ እናመሰግናለን፡፡ በኢሜይል አድራሻችን ዝርዝሩን እና እንዴት ግንኙነቱን ለማድረግ እንደምንችል፤ ቃለመጠይቅም እንደምናደርግ ይግለጹልንና ቀጣዩን ጽሁፍ ከማውጣታችን በፊት በቶሎ ቢከናወን መልካም ነው፡፡ የጻፉልንን አስተያየት እንዳለ ምንም ሳንቀንስና ሳንጨምር አውጥተነዋል፡፡ በድረገጻችን ‹‹ስለ እኛ›› በሚለው ክፍል በገለጽነው መሠረት አንባቢዎቻችን በጨዋነት የሚሰጡትን ማንኛውንም አስተያየት ያለአንዳች ገደብ እናወጣለን – በምንሠራው ሥራ እንተማመናለን፤ ስናጠፋ ደግሞ በግልጽ ይቅርታ ጠይቀን እንታረማለን እንጂ ምንም ዓይነት ልመና ወይም ማሳሰቢያ አያስፈልገንም፡፡
አርታኢ/Editor
ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
http://www.goolgule.com
editor@goolgule.com
Bekri S says
I really loved ur comment on zis post. I don’t think I know Surah very well but ur words are credible and it’s a polite way of disagreeing someone’s points. The topic have encouraged me to know more about this hard working wonderful lady.
Shukren!
dawit says
olad guled ወ/ሮ ሱራን አስመልክቶ ለላኩት አስተያየት የተሰጠውን መልስ አስመልክቶ አንድ ጥያቄ አለኝ። አስተያየት ሰጪው ወታደራዊ ባለስልጣናት በማለት ያነሱትና መንግስት ቢዝነሱን ለመውሰድ አስቦ እንዳልተሳካለት ጠቁመዋል። ጎልጉሎች ይህንን ነጥብ ለምን ዝም አለችሁት?ሌላው በየብስና በዓየር የሚጋዘው ጫት መጠኑ ከፍተኛ መሆኑንና የሚገባው ቀረጥ ተመጣጣጭ እንዳልሆነ የድሬደዋ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ መረጃ ቢሰጥበትስ?ተቀማጭነታቸው ጅጅጋና ድሬደዋ የሆነ የግል ባንኮችስ ለምን ማብራሪያ አይሰጡም?ከሁሉም በላይ የኦሮሚያ የንግድ ተቋም የሆነው ቱምሳ ኢንዶውመነት ቢካተትና ወ/ሮ ሱራ ቃለ ምልልስ ቢያደርጉ ትክክለኛ መረጃ እናገኛለን ብዬ አስባለሁ።
olad guled says
first of all thank you for your prompt reply. I would have preferred to write in amharic. However, my computer does not have amharic fonts and it would take me ages to reply in amharic. Anyway language is a means of communication and I do not consider this would be any issue in this regard.
Suhura got the opportunity to dominate qat business simply because she was doing the business at a time when the ethiopian government desperately wanted to increase its foreign currency earning. As you might have recalled the previous governments in ethiopia had not considered qat as a viable business and they did not attemped to regulated it. However, as you mentioned in your article EPRDF government looked at as a means to increase its foreign exchange not as a venture directly to control it. If you could easily understand qat business squarely fall under goods exmpted from export tax. Suhura was not given favourable treatment. Never the less, she benefited from the circumstances that prevailed at one point in ethiopia. The question now we have to ask is that oromia has not lost its tax income from qat. as I mentioned in my previous reply, Oromia is one of the region that get a huge amount direct subsidy from the federal government. Moreover, qat is a business that operate across more than one regional state. It would be impossible to tax qat export in many regional states. In order to bring fair trading the federal government completely eradicated double taxation which would have killed qat business. There are many taxes qat people engaged in qat pay to the federal or regional states. These taxes are income tax, sales tax, export tax, sur tax etc. The oromia farmers are paying taxes on the basis of their earning income tax as Suhura would have also does.
In my opinion Qat is not a good and ethical business and I prefer if it is completely banned. However, until our government understand the impact this mild substance has on health of the horn of africa people, it would be better if the business benefit both the supplier, in such case the oromia people and the consumers, the somalia people on both sides of the border.
you have asked me to provide evidence of nationality for Suhura whether she is ethiopian or not. I wonder if it should be you or me whom should produce this evidence. According to international standard of evidence production it is the one who contest something that must produce any evidence not the vice versa. Therefore, I do respectfully ask you to produce any evidence that clearly show suhura is not an ethiopia somali. This remind me a current american politic where President Obama’s americaness is doubted by a few bigot. Ethiopia is a wide country that could accommodate many people thank to our forefather who incoporated a huge junk of horn of africa in to present ethiopia. As somali inhabits both sides of the long border between djibouti, somalia and Kenya, Oromo people also resides in Kenya. I have never heard any time Kuma Demekassa was asked to produce his birth certificate to prove his nationality/citizenship. I am a fluent amharic speaker. I also speak Oromiffa. Oromo are my people and I have deep respect for them. I do not think would could wedge hatred among ethiopia people who have lived, intermarried, and existed for centuries together.
Editor says
Dear olad guled
Thanks for your reply. We think that we are entangled here with replies and re-replies and … We raised several issues with regard to your first reply but here you addressed only two of them.
We do not think the nationality of Suhura should cause such great length of analysis. We gave it ONLY two lines from the whole article. Here is what we said “ወ/ሮ ሱራ ጅጅጋ ይኖሩ የነበሩ የሶማሌ ተወላጅ ናቸው። በቅርበት የሚያውቋቸው የሃርጌሳ ሶማሌ ጎሳ አባል የሆኑ ሙሉ የሶማሌ ዜግነት ያላቸው ሴት እንደሆኑ ይናገራሉ።” We didn’t even definitively stated that she is non-Ethiopian or disavow her nationality one way or another. We just stated that as a matter of fact. The whole article is NOT written to verify or nullify her nationality. You know it and our readers understand it that the agenda is something else. As you have eloquently stated it and we have also mentioned that the beauty of Ethiopia emanates from those wonderful people in the boarder area. The Nuers and Anuaks have both South Sudanese and Ethiopian nationality. The Ethiopian Somalis also share the same and the list goes on. So as we have clearly stated in the article and our replies, the issue at stake is NOT about one’s nationality. And these back and forth replies are not taking us anywhere but distracting us from the stated agenda of the article.
We have been raising the issue and explicitly asking you in details about the taxes and how it is skewed and manipulated and … Your repeated reply is “Oromia is one of the region that get a huge amount direct subsidy from the federal government … “. With all due respect sir, we have found this argument of yours not only shallow but inconsequential as well. It is quite obvious that the federal government subsidizes regions. The custom also works in western countries, democracies, totalitarian regimes, …. but this subsidy DO NOT allow or dictate or instruct or disallow or … regions from collecting taxes that belong to their regions. Paying tax for the business you are owning or the operation that you are profiting is not something to be compromised or exchanged by other alternatives – it is YOUR DUTY! That duty may require you to pay your local authorities, weredas, region (ክልል), federal government, … As a person who is living in the Western world you know all about these and you also understand that this is NOT double taxation! You know it well.
Finally, we would like to inform you that we are going to call this discussion off at this moment. We are not going to be engaged in a back and forth replies here. Besides, you didn’t fully address the issues we raised. What we would like to inform you is that if you think we have mislead our readers by writing such article, you can formally write us back your opinion in an article form (could be an “op-ed”), not a comment, and we will gladly publish it. This is the decision of the editorial board and this is our final reply to your comment.
Thank you for your comments and engagement in this regard. We really appreciate it.
አርታኢ/Editor
ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
https://www.goolgule.com
editor@goolgule.com
olad guled says
sorry for some error. I was in hurry and did not got time to edit it. thanks