ባለፈው ሰኞ በዋለው ችሎት እነ ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት የክስ ፋይላቸው መቀየሩ ተዘግቦ ነበር። የዚያን ዕለት የቀረበባቸውም ክስ ሃይማኖትና ብሔርን መሠረት በማድረግ፣ በተለይም በአማራ ብሔር ተወላጆችና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም የተለያዩ መገናኛ ብዙኃንና የትስስር ድረ ገጾችን በመጠቀምና በአካል በመገኘት፣ በተገለጸው አግባብ ባስነሱት የእርስ በርስ ግጭት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የ13 ሰው ሕይወት እንዲያልፍና 48,026,526 ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም አድርገዋል፣ በኦሮሚያ በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች የ167 ሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ፣ 360 ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸውና 4,673,031,142 ብር ግምት ያለው ንብረት እንዲወድም ማድረጋቸውን በመጥቀስ ነበር ዐቃቤ ሕግ ክሱን … [Read more...] about ተከሳሾቹ እነ ጃዋር ወደ እስር ቤት እንዲዛወሩ ታዘዘ
jawar massacre
“በርቱ አገሪቱ የቄሮ በመሆኗ እንደፈለጋችሁ አድርጉ” ጃዋርና ግብረአበሮቹ
የእርስ በርስ ጦርነት በማስነሳት፣ የሽብር ወንጀል ለመፈጸም በማቀድና በመዘጋጀት፣ እንዲሁም የፀና ፈቃድ የሌለው የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ከተመሠረተባቸው 24 ተከሳሾች አንዱ ጃዋር መሐመድ፣ እሱን ጨምሮ እስክንድር ነጋና ልደቱ አያሌው የተከሰሱት መንግሥት በምርጫ ያሸንፋሉ የሚል ሥጋት ስላለው እንጂ ወንጀል ፈጽመው አለመሆኑን ለፍርድ ቤት ተናገረ። ጃዋር ይኼንን የተናገረው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በመዝገብ ቁጥር 260215 መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም. የከፈተውን ክስ፣ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ለተከሳሾች ሲሰጣቸው ነው። በሽብርተኝነት ሲከሰስ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን በማስታወስ የመጀመርያው በኢሕአዴግ ሥርዓት ውስጥ የቀረበበት ክስ ሲሆን፣ ሁለተኛው አሁን የተከሰሰበት መሆኑን ጠቁሞ፣ በዚህም ኩራት እንደሚሰማው … [Read more...] about “በርቱ አገሪቱ የቄሮ በመሆኗ እንደፈለጋችሁ አድርጉ” ጃዋርና ግብረአበሮቹ
የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮችን በእስር እንዲቆዩ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጠ
የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ የቀድሞ የወላይታ ዞን አመራሮች የነበሩ ግለሰቦችን ጨምሮ 20 ተጠርጣሪዎች በወላይታ ሶዶ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ፤ ለተጠርጣሪዎች ተፈቅዶ በነበረው ዋስትና ላይ ፖሊስ የመልስ መልስ ይዞ እንዲቀርብ ለመጪው ሳምንት ማክሰኞ መስከረም 19 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃ ተመስገን ዋጃና ለ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የተጠርጣሪዎችን አቆያየት በተመለከተ በትላንትናው ዕለት ከሰዓት ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም በጠዋት ችሎት ቀርበው የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች አልተገኙም በሚል ብይኑን ለዛሬ ማሳደሩን ጠበቃው ገልጸዋል። እስከ ምሽት አንድ ሰዓት ድረስ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሲጠብቁ የቆዩ ሰባት ተጠርጣሪዎችም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሐዋሳ ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ … [Read more...] about የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮችን በእስር እንዲቆዩ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጠ
የእነ እስክንድር ክስ እንዲሻሻል ተጠየቀ
ዓቃቤ ሕግ በመሠረተባቸው ክስ የሕዝብ ሰላምንና የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል፣ ሥልጣንን በኃይል ለመያዝና የሽብር ተግባር ለመፈጸም ተዘጋጅተዋል በማለት የዋስትና መብታቸው እንዳይፈቀድላቸው መከራከሩን በመቃወም ለፍርድ ቤቱ ምላሽ የሰጡት እነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ መንግሥት ወይም ዓቃቤ ሕግ ለሕዝብ ሰላምና ለአገር ደኅንነት የሚያስብ ከሆነ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆላቸው፣ በመጪው አገራዊ ምርጫ እንዲሳተፉ መደረግ እንዳለበት ለፍርድ ቤት ተናገሩ። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ዋስትና እንዲከበርላቸው የጠየቁት፣ የተመሠረተባቸውን ክስ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሽብር ተግባራትና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች አንደኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ካነበበላቸው በኋላ፣ ስለመብት … [Read more...] about የእነ እስክንድር ክስ እንዲሻሻል ተጠየቀ
“ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” የተባሉበት ክስ ዝርዝር
በተደጋጋሚ የክስ ቻርጅ እንዳይሰጠው ጥረት ሲያደርግ የነበረው ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ከግብርአበሮቹ ጋር “ተከሳሽ” የሚለውን መጠሪያ ትላንት ሰኞ መስከረም 11/2013 ተቀብለዋል፤ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በይፋ ክስ መስርቷል። ዐቃቤ ህግ በጃዋር መሐመድ እና ሌሎች 23 ተከሳሾች ላይ ክሱን በመሠረተበት ወቅት፤ ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች አንደኛ ወንጀል ችሎት፤ በውሎው የክስ ሰነዶቹ ለተከሳሾችና ጠበቆቻቸው እንዲከፋፈል አድርጓል። በመሆኑም እነ ጃዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባና ሀምዛ አዳነን ጨምሮ 18 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ተመስርቶባቸዋል። ተከሳሾቹ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ህገ መንግስትና ጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሱ ደርሷቸዋል። ዐቃቤ ህግ በክስ ሰነዱ ላይ 10 ክሶችን … [Read more...] about “ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” የተባሉበት ክስ ዝርዝር
ጃዋርና ግብረአበሮቹ 10 ተደራራቢ ክሶች ተከፈተባቸው
አቃቤ ሕግ በእነ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ ላይ ክስ የሚመሰርትበት ቀን አርብ መስከረም 8፤ 2013ዓም ነበር። ሆኖም በዚህ ክስ ይመሰረታል ተብሎ በሚጠበቅበት የመጨረሻው ቀን ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። በዚህም አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ ለፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡ የነ ጃዋር መሐመድ ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ተናግረው ነበር። ሆኖም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ መሠረት ጃዋርና ሲራጅ መሐመድና ግብረአበሮቹ በ10 ተደራራቢ ክሶች ፋይል እንደከፈተባቸውና የክስ ቻርጁም መስከረም 11፤2013ዓም ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እንደሚደርሳቸው አስታውቋል። ዐቃቤ ሕግ ያወጣው ጽሁፍ ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል፤ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድ፤አቶ በቀለ ገርባ፤አቶ ሀምዛ አድናን እንዲሁም በሌሉበት የተከሰሱትን የኦሮሚያ ሜዲያ … [Read more...] about ጃዋርና ግብረአበሮቹ 10 ተደራራቢ ክሶች ተከፈተባቸው
እነ ጃዋር ይከሰሳሉ – ዐቃቤ ሕግ
በእነ ጃዋር ሲራጅ መሃመድ ላይ ተከፍቷል ከተባለው የክስ መዝገብ ጋር በተያያዘ በመጪው ሳምንት መግለጫ እንደሚሰጥ ዐቃቤሕግ አስታወቀ። ጃዋር ሲራጅ መሀመድን ጨምሮ በአጠቃላይ በ24 ሰዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 260215 በ10 ተደራራቢ ክሶች ማስከፈቱን ያስታወቀው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩን በማስመልከት በመጪው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት መግለጫ እንደሚሰጥ ተገለፀ። “ክስ መመሥረት ባለበት ጊዜ ውስጥ ባለመመሥረቱ ተከሳሾቹ ከሰኞ ጀምሮ ከእሥር ሊለቀቁ ነው የሚል ወሬ በሕዝብ ዘንድ ተሰራጭቷል” መግለጫው ዐቃቤ ሕግ ተቋሙ እየሰራ ያለውን ሥራ ማኅበረሰቡ እንዲያውቀው ለማድረግ የሚሰጥ ነው ብለዋል። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ መከፈቱን በተመለከተ ዛሬ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አጭር ጥቅል መረጃን ሰበር በሚል ርዕስ ሰጥቷል። “ፍርድ ቤት ራሱ ክሱ በዝርዝር … [Read more...] about እነ ጃዋር ይከሰሳሉ – ዐቃቤ ሕግ
እነ እስክንድር፥ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት
እነ አቶ እስክንድር ነጋ የአስተዳደሩን ሥልጣን በኃይል ለመያዝና ለሽብር ወንጀል መሰናዳት ወንጀሎች ተከሰሱ ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ውለው የቆዩት እነ አቶ እስክንድር ነጋ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀና ለ)፣ 35፣ 38፣ 240(1ለ) እና የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 6(2) ድንጋጌዎችን በመተላለፍ መንግሥትን ሰላም በመንሳትና እንዳይረጋጋ በማድረግ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥልጣንን ኃይልና አመፅ ተጠቅመው ለመያዝ በመንቀሳቀስና ለሽብር ወንጀል በመሰናዳት ወንጀሎች ክስ ተመሠረተባቸው። የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጳጉሜን 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕገ መንግሥትና የሽብር ወንጀሎች አንደኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት፤ በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ … [Read more...] about እነ እስክንድር፥ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት
“ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” ሊባሉ ነው
እነ ጃዋር መሐመድ መንግሥትን ኮንነው የፍትሕ ተቋማትንና ፍርድ ቤትን አመሠገኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠ በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግሥት ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 71 ቀናት በእስር ላይ ያሉት እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የጊዜ ቀጠሮና የቅድመ ምርመራ የፍርድ ቤት ሒደቶች መጠናቀቃቸውንና የምርመራ መዝገቡ መዘጋቱን አስመልክቶ፣ “ያለ ጥፋታችን እንድንታሰር አድርጎናል” ያሉትን መንግሥትን ኮንነው የፍትሕ ተቋማትንና ፍርድ ቤትን አመሠገኑ። ተጠርጣሪዎቹ ቅሬታቸውንና ምሥጋናቸውን የገለጹት ከሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱን ሒደት ሲያይ የነበረው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት፣ ሰኞ ጳጉሜን 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በምርመራ መዝገቡ ላይ የተለያዩ ትዕዛዞችን ሰጥቶ ሲዘጋ በሰጡት … [Read more...] about “ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” ሊባሉ ነው
በጽንፈኞች ጉዳት ለደረሰባቸው 40 ሚሊዮን ድጋፍ ተደረገላቸው
የኦሮሚኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ የነበረው ሃጫሉ ሁንዴሣ በግፍ በተገደለ ጊዜ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የተነሳው ነውጥ የበርካታ ወገኖችን ሕይወት ቀጥፏል፤ ንብረት አውድሟል፤ አካለ ሥንኩል አድርጓል፤ ይህ ነው የማይባል የስነልቦና ችግር ፈጥሯል። አክራሪና ጽንፈኛ የሆኑ በደመ ነፍስ የሚመሩ ለፈጸሙት ግፍ መጠገኛ የሚሆን የተለያየ ድጋፍ ለተጎጂዎች ሲከፋፈል ቆይቷል። ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በኦሮሚያ ክልል በጽንፈኞች ንብረታቸው ለወደመባቸው፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸውና የቤተሰቦቻቸው ሕይወት በግፍ ለተነጠቀባቸው ልጆቿ የአርባ ሚሊዮን (40,000,000) ብር ድጋፍ አድርጋለች። ቤተክርስቲያኒቱ ለተጎጂዎች በየስማቸው የተዘጋጀውን የባንክ ሒሳብ ደብተር ያስረከበችው ዛሬ በጠቅላይ ቤተክህነት በተዘጋጀ ሥነሥርዓት ነው። (@ Dewol) ጎልጉል … [Read more...] about በጽንፈኞች ጉዳት ለደረሰባቸው 40 ሚሊዮን ድጋፍ ተደረገላቸው