የሚዲያ አውታሮች ከውስጥም ከውጭም፣ የመንግሥትም ሆኑ የግል፣ የተገዙም ሆኑ በሊዝ የተያዙ፣ በደመ ነፍስ የሚጓዙትን ጨምሮ ሆን ብለው አስበውበትም ሆነ ሳያውቁት የጃዋር ሰለባና አንደበት ሆነዋል። አንዳንዶቹ በሳል የሚባሉት የሚዲያ አውታሮች ተቆጣጣሪ ኤዲቶር ያላቸውም አይመስሉም። “በድንገት በጃዋር ላይ በለሊት ከበባ መደረጉን ተከትሎ” እያሉ እሳቱ ላይ ነዳጅ ያርከፈክፋሉ። የዘገቡ መስሏቸው የጃዋር አፈቀላጤ በመሆን በትጋት ያገለግላሉ። ጃዋር “ተከበበ ” የተባለው በማን ነው? ማን ከበበው? እንዴት ተከበበ? ስንት ሠራዊት ከበበው? ለምን ተከበበ? በሚል ማጣራቱ ቢቀር እሱ ያለውን ጠቅሶ መዘገብ እንዴት ለአንድ ሚዲያ ይከብዳል? ከደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋና ቁሳዊ ጥፋት ለማምለጥ እየዋለ ሲያድር ከሚባለው ውጪ “በሌሊት ጠባቂዎቼ እንዲነሱ ታዘዘ” የሚለውን ጠቅሶ ለመዘገብ ያልተቻለበት … [Read more...] about የጃዋር ሰለባዎች በሱ መመሪያ የተጨፈጨፉት ብቻ ሳይሆኑ ሚዲያውም ጭምር ነው
jawar massacre
ያበደውን አድረን ማወቃችን አይቀርም!
“በብዙ እብዶች መካከል ጤነኛ ያብዳል” ይባላል ይህን እውነታ ኡመር ሱሌማን ነው ከ18 አመት በፊት የተናገረው። ብዙ ሰዎች የወደዱት እምቢ ካለ ወይም እነሱ የጠሉትን ከወደደ “እብድ” ወይም “ከሃዲ መባሉ አይቀርም። በዚህ ውስጥ አልፈን ነው የመጣነው እኔ ጤንነቴን በደንብ አውቀዋለሁ የሰውም ማረጋገጫ አልፈልግም ለሰውም እንደዛው ትልቅና አስቀያሚ በሽታ ነው ያለው። ይህን ለማከምና ለማስተካከል መታገል ትክክል ነው ግን ደግሞ ትግሉ አገር በሚያፈርስ መልኩ መሆን የለበትም። የፈለገ ችግር ቢኖር ከየመን ከሊቢያና ከሶሪያ ኢትዮጵያ ትሻላለች! የመንን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት እንጂ ኢትዮጵያን ወደ የመን መውሰድ ጤንነት አይደለም። ሩዋንዳን የዘነጋ ሰው በራሱ በሽታ ነው። ተቀምጠው የሰቀሉትን ቆመው ማውረድ ይቸግር ይሆናል። ያጣነውን ብቻ ሳይሆን ያለንንም ማስታወስ ተገቢ ነው … [Read more...] about ያበደውን አድረን ማወቃችን አይቀርም!
እንግዲህ ቢመርም እውነት ሊነገር ግድ ይላል!!!
በመጀመሪያ "የለውጡን (ሥሌት) የሰራሁት እኔ ነኝ" አለ - በዝምታ "አዎ ነህ" ተባለ ቀጠለና "እዚህ ሀገር ሁለት መንግሥት ነው ያለው የአብይ እና የቄሮ [የኔ]" አለ አሁንም በዝምታ "አዎ ልክ ነህ" ተባለ መንግሥት በዝምታ ያገነነው ኢመደበኛው የጃዋር መንግሥት በንግግር ብቻ ሳይገታ ውሳኔዎችን መሻር ማሳለፍ ጀመረ - በዝምታ መንግሥትነቱ ተረጋገጠለት እነሆ አሁን ደግሞ ለውጡ በመጣባቸው ጥቅመኛ የመንግሥት ሰዎች፣ አኩራፊዎች እና ጥገኛ ባለሀብቶች በተቀነባበረ ሴራ "ኢመደበኛው መንግሥታችሁ ሊገረሰስ ነው" ተብሎ (“የመግደል ሙከራ” በሚል ፈጠራ) 67 ንፁሃን ምስኪኖች ያልተገራው ኢመደበኛ ስልጣኑ ይፀና፤ ምሽጉም ይጠነክር ዘንድ መስዋዕት ሆነው ቀረቡለት። ይሄን ጊዜ በዝምታ አያልፉም ስንል - ተናገሩ! ምን አሉ "አንተ ዐይን ነህ - እንደ ብሌናችን … [Read more...] about እንግዲህ ቢመርም እውነት ሊነገር ግድ ይላል!!!
“የህወሓት ባለሥልጣናትንና አጋሮቻቸውን” መረጃ እየተረከክን ነው – ባለሙያዎቹ
ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ ወዳጆች! የኢትዮጵያን ሕዝብ በአፈና፣ ዝርፊያና ሰብዓዊ ጥሰት ሲገዛ በነበረው ህወሓት እና በሌሎች ጽንፈኛ ብሄረተኞች ትብብርና ቅንጅት የታየውን የለውጥ ተስፋና እየተካሄዱ ያሉ ለውጦችን ለማደናቀፍ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ቡድኖች በገዥነት ዘመናቸው ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን ሀብትና ንብረት በመጠቀም የተለያዩ ቡድኖችን በገንዘብ በመደለል አገርን ከማተራመስ በላይ ወደ ማፍረስ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ተረድተናል። በተለይም አሁን አገሪቱን እያስተዳደረ ያለው በጠ/ሚ/ር ዐቢይ የሚመራው ኢህአዴግ ሌሎች አጋር ፓርቲዎችን ጨምሮ በቅርቡ የሚያደርገው ውህደት ያልተዋጠላቸው የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ይኼን የውህደት እንቅስቃሴ በሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ከማጣጣል ጀምሮ፣ የተለያዩ የትርምስ እና የሽብር እንቅስቃሴዎችን … [Read more...] about “የህወሓት ባለሥልጣናትንና አጋሮቻቸውን” መረጃ እየተረከክን ነው – ባለሙያዎቹ