በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር) “እንደቀልድ፣ ሳናውቀው አገራችን ወደ ፍርስራሽነት ተቀየረች” አለ፣ አንድ ታዋቂ የየመን ጋዜጠኛ፤ በአንድ ቃለመጠይቁ ላይ። ነገሮች የረዥም፣ ተከታታይ ሂደት ውጤት ወይም መጨረሻ ናቸው፤ የድንገቴ ክስተት አይደሉም። ጦርነት ያለመግባባትና የቅራኔ ሂደት ውጤት ነው። ሞት ከጤንነት ጀምሮ፣ እየጠነከረ የሚሄድ ህመም ሒደት ውጤት ነው። በሥርዓትና ደንብ የቆመ ሀገር መፍረስም እንዲሁ የረዥም ጊዜ፣ ተከታታይ ከሥርዓትና ደንብ ማፈንገጥ ሒደት ውጤት ነው። የሀገር መሪዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ፖለቲከኞች . . . ሁላችንም፣ “ኢትዮጵያ አትፈርስም” እያልን እንጮሀለን። ከጩኸቱ ጀርባ የቻሉትን እያደረጉ ያሉት ግን የሀይማኖት አባቶች ብቻ ናቸው፤ ዕንባቸውን ሽቅብ ወደ ፈጣሪ መንበር እየረጩ የመንፈስ ልጆቻቸውን ይለምናሉ፤ ምእመኑን በጸሎትና በጾም ያተጋሉ። ፖለቲከኞች … [Read more...] about ሰላምን ከጦርነት፣ መፍረስን ካለመፍረስ የሚለይ ቀይ መስመር የለም!