የሚዲያ አውታሮች ከውስጥም ከውጭም፣ የመንግሥትም ሆኑ የግል፣ የተገዙም ሆኑ በሊዝ የተያዙ፣ በደመ ነፍስ የሚጓዙትን ጨምሮ ሆን ብለው አስበውበትም ሆነ ሳያውቁት የጃዋር ሰለባና አንደበት ሆነዋል። አንዳንዶቹ በሳል የሚባሉት የሚዲያ አውታሮች ተቆጣጣሪ ኤዲቶር ያላቸውም አይመስሉም። “በድንገት በጃዋር ላይ በለሊት ከበባ መደረጉን ተከትሎ” እያሉ እሳቱ ላይ ነዳጅ ያርከፈክፋሉ። የዘገቡ መስሏቸው የጃዋር አፈቀላጤ በመሆን በትጋት ያገለግላሉ። ጃዋር “ተከበበ ” የተባለው በማን ነው? ማን ከበበው? እንዴት ተከበበ? ስንት ሠራዊት ከበበው? ለምን ተከበበ? በሚል ማጣራቱ ቢቀር እሱ ያለውን ጠቅሶ መዘገብ እንዴት ለአንድ ሚዲያ ይከብዳል? ከደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋና ቁሳዊ ጥፋት ለማምለጥ እየዋለ ሲያድር ከሚባለው ውጪ “በሌሊት ጠባቂዎቼ እንዲነሱ ታዘዘ” የሚለውን ጠቅሶ ለመዘገብ ያልተቻለበት … [Read more...] about የጃዋር ሰለባዎች በሱ መመሪያ የተጨፈጨፉት ብቻ ሳይሆኑ ሚዲያውም ጭምር ነው