• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጃዋር ፋይናንስ በክትትል ራዳር ውስጥ – ዳያስፖራ ደጋፊዎች ስለ ነገ አያውቁም!

November 29, 2019 01:21 am by Editor 5 Comments

ዓለምአቀፉ የፖሊስ መሥሪያ ቤት (ኢንተርፖል) እንደሚለው ከሆነ አሸባሪዎችን የማድረቂያው አንዱ መንገድ የገንዘብ እንቅስቃሴያቸውን መከታተል ነው። መ/ቤቱ አሸባሪዎችን በገንዘብ የመርጃ መንገዶች ብሎ የሚከተሉትን አስፍሯ፤ ዕርዳታ ከደጋፊዎች በማሰባሰብ፣ በማጭበርበር፣ ትርፍ አልባ ድርጅት በመመሥረትና አለአግባብ በድርጅቱ ስም መበልጸግ (OMN በአሜሪካ አገር በትርፍ አልባ ድርጅትነት የተመዘገበ መሆኑን ልብ ይሏል)፣ ሰዎችን አፍኖ በመውሰድና በምላሹ ካሣ በመጠየቅ፣ በሕገወጥ ንግድ በመሠማራት (ይህም በነዳጅ፣ በከሰል፣ በአልማዝ፣ በወርቅና በአደንዛዥ ዕጽ የሚጠቀልል ነው)።

ይህንን የገንዘብ (የዕርዳታ ድጋፍ) ማሰብሰብና ማዘዋወር ለመቆጣጠር በአገራት መካከል መረጃ የሚለዋወጥና ደረጃ የሚያወጣ Financial Action Taskforce (FATF) የሚባል ግብረኃይል ኢንተርፖል አለው። ከዚህ ግብረኃይል በተጨማሪ በዓለም ዙሪያ 164 የፋይናንስ ስለላ ዩኒት ያሉት Egmont Group የሚባል በመረጃ ልውውጥ የረቀቀ መስተጋብር (ኔትዎርክ) እንደሚጠቀም የኢንተርፖል ድረገጽ በግልጽ ያስረዳል። ይህ Egmont Group የተባለው ቡድን አሸባሪነትንና የገንዘብ ልውውጥን ለመከላከል የፋይናንስ ስለላ (financial intelligence) መረጃዎችን የሚያለዋውጥና የሙያ ዕገዛ የሚያደርግ መድረክ በማዘጋጀት የሚሠራ ቡድን ሲሆን ለአባል አገራት በአገራቸው ውስጥም ይሁን በአገራት መካከል በዓለምአቀፉ Anti Money Laundering and Counter Financing of Terrorism (AML/CFT) ውል መሠረት መረጃ በቀላሉ እንዲለዋወጡ የሚያደርግና የሚያስገድድም ነው።

በስምንት ቀጣናዎች በተደራጀው በዚህ የኢንተርፖል ቡድን በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ውስጥ ኢትዮጵያ ከረቡዕ July 3, 2019 (ሰኔ 26፤ 2011ዓም) ጀምሮ በአባልነት ተመዝግባ ትገኛለች።

ከዚህ በተጨማሪ ከመስከረም 1ዱ (ሴፕቴምበር 11) የአሸባሪዎች ጥቃት በኋላ የአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስቴር የአሸባሪዎችን መስተጋብር ለይቶ የሚያወጣ፣ ሥር መሠረቱን የሚመረምርና የሚከታተል Terrorist Finance Tracking Program (TFTP) የሚባል መርሃግብር ዘርግቷል። ይህ መርሃግብር የአሸባሪዎችን የገንዘብ ምንጭና ፍሰት በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገራት የሚከታተል ሲሆን በቤልጂየም ከሚገኘው ዓለምአቀፉ የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ ልውውጥ ማኅበር Society for Worldwide Interbank Financial Telecommunication (SWIFT) በተጠርጣሪ አሸባሪዎች ላይ የፋይናንስ መረጃ የመጠየቅና የመሰብሰብ ሙሉ ፈቃድ አለው።

አሸባሪዎች የሚፈልጉትን ዓላማ ለማስፈጸም ገንዘብ ዋንኛ መሠረታቸው እንደሆነ የሚናገረው የካናዳው የገንዘብ ልውውጥና የዘገባ ትንተና ማዕከል (Financial Transactions and Reports Analysis Centre of Canada – FINTRAC) አሸባሪዎች ሕጋዊና ሕገወጥ የሆኑ የገንዘብ ምንጮችን እንደሚጠቀሙ ይናገራል። ከደጋፊዎችና አባላት የገንዘብ ዕርዳታ መሰብሰብ፣ ከግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር አብሮ በመሥራት ገንዘብ ማስተላለፍ፣ በንግድ በመሠማራት ትርፍ በማግኘት ሕጋዊ የሚባሉትን መስመሮች የሚጠቀሙ ሲሆን በጦር መሣሪያ ዝውውር፣ በአደንዛዥ ዕጽ ዝውውር፣ በሕገወጥ የሰው ዝውውር፣ በግብር ማጭበርበር፣ ወዘተ ሕገወጥ የገንዘብ መሰብሰቢያ መንገዶች እንደሚጠቀሙ ማዕከሉ ያስረዳል።

በተለይ ከውጭ አገራት የሚሰበሰበው ገንዘብ ወደ አገር ውስጥ የሚገባበትን በተመለከተ አሸባሪዎች የተወሰነውን በህጋዊ የባንክ ዝውውር የሚጠቀሙ ሲሆን ሌላውን ግን በሐዋላ፣ በሁንዲ፣ በግለሰብ፣ በዕቃ ግዢ፣ በአካል በማዘዋወር፣ በወርቅና በመሳሰሉት በመቀየር፣ የተለያዩ ሕገወጥ ስልቶችን እንደሚጠቀሙ ማዕከሉ ይናገራል።

ይህንን መሰሉን የገንዘብ ዝውውር ከምንጩ፣ ከለጋሾቹ፣ ከተባባሪዎቹ ማንነት ጀምሮ እስከ መድረሻው ድረስ ለመከታተል የካናዳውም ሆነ የአሜሪካው እንዲሁም ኢንተርፖል ከየቤተእምነቱ፣ ከየስብሰባው አዳራሽና ሰልፍ የሚሰበሰቡ የምስል፣ የቪዲዮ ወዘተ መረጃዎችን እንዲሁም በየማኅበራዊ ሚዲያ የሚለጠፉ ፎቶዎችን፣ ቪዲዮዎችን፣ ጽሁፎችን ወዘተ በመሰብሰብ የሚጠቀሙ መሆናቸው የሚታወቅ ነው። የካናዳው ማዕከል እንደሚለው ከሆነ አሸባሪነት በዓመጽና በኃይል ማኅበራዊ ጉዳት የሚያደርስ፣ ግልጽ የሆነ ማኅበራዊ ግፍ በመፈጸም የተጎጂዎችን ቁጥር የሚበራክት በመሆኑ በቁጥጥር ሥር ሊውል የሚገባው ወንጀል ነው ብሏል።

በእምነታቸውና በማንነታቸው ምክንያት መንግሥት በይፋ ባመነው መሠረት ሰማንያ ስድስት ዜጎች ከተገደሉ፣ ቤተ እምነቶች በእሳት እንዲጋዩ ከተደረገ በኋላ በአሜሪካ ስለ ቀጣዩ የትግል አቅጣጫና ለዚሁ ዓላማ ገንዘብ ለማሰባሰብ ወደ አሜሪካ ብሎም ወደ አውሮጳ ያቀናው ጃዋር መሀመድ ከተከታዮቹ ጋር በዓለም አቀፍ ደረጃ ሸምቀቆ ውስጥ መግባቱ ተሰማ። በኖርዌይ በልዩ ሁኔታ ክትትል መደረጉ ተመለከተ። በጀርመንና በእንግሊዝ ተመሳሳይ ክትትል እንደሚደረግ ታውቋል።

የጎልጉል ዜና አቀባዮች እንዳሉት ጃዋር በአሜሪካ ቆይታ ያካሄዳቸው ማናቸውም ተግባራት ከክትትል ነጻ አልነበረም። በተመሳሳይ በኖርዌይም ከአሜሪካ ጋር በጥምረት ይሁን በተናጠል ጃዋርና ዙሪያውን የከበቡት ሲጠኑ ነበር።

የንጹሃን መታረድ፣ የእምነት ቤቶች መቃጠል፣ ሰዎች በማንነታቸው ተለይተው መገደላቸውና ጃዋር ግንኙነት የሚያደርጋቸው አገሮች ጉዳይ ፊትለፊት ከሚታየው የታጋይነት ተግባር ጋር የማይጣጣሙ መሆናቸው ጃዋርና ባልደረቦቹ እንዲጠኑና በቅርበት እንዲመረመሩ ምክንያት እንደሆነ ነው የዜናው ሰዎች በጥቅሉ የተናገሩት።

ጃዋር በአሜሪካ የደረሰበት ተቃውሞ ምንም እንኳን መሪ አልባ፣ ያልተቀናጀ፣ ስድብ የታከለበት ቢሆንም ከሽብር መለያ ዓለምአቀፍ ስሞች ጋር ተያይዞ መወገዙና የተገደሉ ንጹሃን ምስል አደባባይ መቅረቡ ድንጋጤን ፈጥሯል። ኢንተርፖልና ሌሎች የጸረ ሽብር መሥሪያቤቶች ባላቸው ዓለምአቀፍ የአሸባሪነት መለኪያ መስፈርትም ድርጊቱ ሚዛን የሚደፋ መሆኑ ትኩረትን የሳበ ሆኗል።

ዜግነት እንደሚቀይር ከመናገሩ ውጪ በተግባር የኢትዮጵያ ዜግነት ስለመያዙ ይፋ ያላደረገው ጃዋር፣ በፍጹም ራስ መተማመን በማኅበራዊ ገጹ ላይ ተቃውሞው ጫና እንዳላሰደረበት ቢገልጽም በዲሲ የሃይማኖት መሪዎችን በመያዘና አብሯቸው ፎቶ በመንሳት፣ ቤተሰቦቹ ቤተክርስቲያን እንደገነቡ በመናገር ራሱን ከጽንፈኛ አካላት ለይቶ ለማሳየት ያደረገው ጥረት የፍርሃቻው አመላካች ተደርጎ ተወስዷል።

“ማኅበራዊ ሚዲያ የፖሊስ ምርመራ ሥራችንን አቃሎልናል። ወንጀለኞችን ለመለየት ከምንፈልገው በላይ መረጃ ከማኅበራዊ ገጻቸው ላይ በቀላሉ እናገኛለን” ሲሉ ከዚህ በፊት አንድ የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ (ኤፍ.ቢ.አይ.) መርማሪ መናገራቸውን ያስታወሱት የዜናው ሰዎች፤ ጃዋር በሕግ የሚጠየቅበት አግባብ ከተጀመረ ስማቸውን እየቀየሩ ወይም እየደበቁ (anonymous እያሉ) ገንዘብ ሲሰጡና ይህንኑ ሲያስተባብሩ የነበሩ ሁሉ በምንም ዓይነት ሁኔታ እንደማያመልጡ አመልክተዋል። መረጃቸውን ከሕዝብ ዕይታ ቢያጠፉ ወይም ቢሰውሩ እንኳን በቀላሉ ወደኋላ ሄዶ ማግኘት እንደሚቻል የቴክኖሎጂው ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

በአሜሪካ የሚኖሶታ ጠቅላይ ግዛት በርካታ የሶማሌ ክልል ተወላጆችና የሶማሌ ዜግነት ያላቸው በጃዋር ስብሰባ እንዲገኙና የገንዘብ ዕርዳታ እንዲያደርጉ ቢጠየቁም ወደፊት ከአሸባሪ ጋር ተባባሪ የመሆናቸው መረጃ በማስረጃ እንደሚቀርብባቸው በውስጥ ለውስጥ ስለደረሳቸው በስብሰባው ላይ ሳይገኙ መቅረታቸውን ስለ ጉዳዩ በቅርብ የሚያውቁ የጎልጉል ምንጮች ተናግረዋል።

ጎፈንድሚ (gofundme) ላይ ዕርዳታ የሚሰጡ ወገኖች ስማቸውን ያለመሙላት (anonymous እያሉ ገንዘብ የመስጠት) መብት ቢኖራቸውም ከየት ሰፈር፣ ከየትኛው ሞባይልና ኮምፒውተር፣ ከየትኛው ባንክና ከየትኛው አድራሻ ገንዘብ እንደላኩ አሁን በሚሠራበት ዓለምአቀፍ የፋይናንስ ትብብር መሠረት መረጃቸው ስለሚገኝ የጃዋር አድሮም ቢሆን ወደ ሕግ መምጣት ከተከለከሉ የወንጀል ሕጎች (በተለይ አሸባሪነት) ጋር ተያይዞ በርካቶችን ሊያነካካ እንደሚችል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚገኙ የጎልጉል የዘወትር ተባባሪ ከፍተኛ ዲፕሎማት ገልጸዋል።

እርሳቸው እንዳሉት በአገራቸው (በአሜሪካ) የሕግ አካሄድና የምርመራ ሥራ በመጣደፍ የሚደረግ ባለመሆኑና መረጃ ፈርጥሞ እስኪደራጅ ድምጽ በማጥፋት ስለሚሠራ ቀኑ እስኪደርስ ጉዳዩ እንደ ቀለድ ይታያል፤ ምናልባትም ተባባሪ መስሎ የመታየት ሥራም ሊሠራ ይችላል። በሌላ አነጋገር “በረጅም ገመድ የታሰረች ዶሮ የተፈታች ይመስላታል” እንደሚባለው መሆኑ ነው።

የአሜሪካውን ጉዞ “አጠናቅቆ” ወደ ኖርዌይ ያቀናው ጃዋር፤ በኖርዌይ በተመሳሳይ አብረውት ካሉት ተባባሪዎቹ ጋር በድፍን ተጠንቷል፤ ግንዛቤም ተወስዷል። እንደ ታማኝ ዜና አቀባዮች ከሆነ ሁሉም ጉዳይ ተመዝግቧል፤ እርሱም በኖርዌይ ባደረገው ስብሰባ ባልተለመደ መልኩ በኦሮምኛ ለተጠየቀው በእንግሊዝኛ ሲሰጥ የነበረው “ከራሴው አንደበት ስሙኝ ንጹህ ሰው ነኝ” በማለት ራዳር ውስጥ ላስገቡት ሰዎች የተናገረው ተደርጎ ተወስዷል። በአሜሪካ የተጀመረው ፋይልን የማደራጀትና የማፈርጠሙ ሥራ ሲጠናቀቅ ጃዋር ወደ ህግ የሚቀርብ ከሆነ ከኖርዌይ፣ ከጀርመን፣ ከስዊድንና ከእንግሊዝ ወዘተ መረጃ የመለዋወጥ አሠራር አለ።

ጃዋር በተወለደበት አካባቢ አሁን በቅርቡ በርካታ ንጹሃን መታረዳቸው፣ ቤተ እምነቶችና አባቶች መገደላቸው አይዘነጋም። ጃዋር በቅድሚያ ኦሮሞ (ኦሮሞ ፈርስት) በሚለው ትግል ከመጠመዱ በፊት “እኔ በምኖርበት አካባቢ በሜንጫ ነው አንገቱን የምንለው” ሲል ባደባባይ መናገሩ አይዘነጋም።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Politics Tagged With: financial intelligence, Full Width Top, jawar massacre, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. yougonnadelete says

    November 30, 2019 12:52 am at 12:52 am

    የጎልጉል አርታኢ ሆይሻ!

    ይህንን ራሳችሁ እንዳላችሁት በምርመራያ ክትትል ላይ ያለውን ጃዋር የተባለ ዕብድ ውሻ ጉዳይ እንዲህ አድሮ ማቅረብ ማንን ነው የሚጠቅመው? ጃዋርና ተከታዮቹን ነው – ይበልጥ እንዲጠነቀቁና ሌላ ዘዴ እንዲፈልጉ ሳታውቁት እየመከራችሁ ነው፤ ምንድን ነው እኛ ነን የመጀመሪያዎቹ፤ አስተማማኝ ምንጮች አሉን ቅብጥርስዮ ለመለት ነው? ወይስ ለዝም ብሎ ጯሂ ዳያፖራዎች አስደሳች ዜና ማቅረባችሁ ነው? ኧረ እየተስተዋለ? በተለይ አገር ቤት ያሉ ገልቱ ጄኔራሎችና የኦሮሚያ ባለሥልጣኖች ጠቅላይ ሚንስትሩን ሳይቀር እንደሚተባበሩት እያወቃችሁ ስለሚደረግበት ክትትል ዝርዝር መረጃ ታቀርባላችሁ? ዜናም ሆነ የምርመራ ሂደትን በማንኛውም መልኩ የሚያደናቅፍ ወሬም ሆነ ማስረጃ ጊዜውን ጠብቆ አይደለም እንዴ መሰራጭት ያለበት?

    ያው አስተያዬቴን መሠረዛችሁ ወይም አልባሌ መልስ መሠንዘራችሁ አይቀርም ግን ቢሆንም አርታኢው ማየቱ/ቷ አይቀርም ብዬ ነው የምልከው

    Reply
  2. Ayalew Shebeshi says

    November 30, 2019 04:20 am at 4:20 am

    WILL YOU PLEASE PROVIDE ENGLISH LANGUAGE VERSION OF THIS ARTICL. WE CAN USE IT SUPPORTING OUR PETITION:

    https://www.change.org/p/peter-dutton-refuse-jawar-mohammed-entry-into-australia-3be00b01-6d00-4b56-9fff-fa771316e45a

    Reply
  3. delazu-arta-ee says

    November 30, 2019 10:00 am at 10:00 am

    እንዲህ ትላላችሁ

    ስለ እኛ!
    ህዝብ “የነጻ” ሚዲያ ረሃብ አለበት፡፡ ፖለቲከኞችም ከድጋፍና ከሙገሳ ባለፈ መልኩ ግልጽ የሕዝብ ትችትና የባለሙያ አስተያየት ያስፈልጋቸዋል፡፡ በሁሉም አቅጣጫ ግን ክፍተት አለ – ይህ ክፍተት ደግሞ የመረጃ አፈና በሚካሄድባት ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ነጻነት አለበት በሚባልበት የውጪው ዓለምም በተደጋጋሚ ሲከሰት ይስተዋላል፡፡ ይህንን ክፍተት መሙላት ባይቻልም የበኩላችንን ማበርከት እንዳለብን በማመናችን በተለያዩ አገራት የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ለመመስረት ወሰንን፡፡

    ወቸ ጉድ – ከመልካም ቃላት ጀርባ መደበቅ ማለት ይቺ ናት፡ እናንተ (ብዙ ከሆናችሁ) የሚደርስባችሁን ትችታ አስተያየትን ተከታትላችሁ እይደለዛችሁ ሌሎችን ትችት እንዲቀበሉ ታሳስባላችሁ? አርታኢው እየተከታታለ በመደለዝ ሥራ ተጠምዷል፤ ከቶ እኛን ማን ተችቶን የሚል አስተሳሰብ ስላወራችሁ ደጋግሞ ከማሳበድ ሌላ አማራጭ የለም፤ እናንት “በተለያዩ አገራት የምትገኙ ባላሙያዎች” ሆይ ለዚህ አምባገነናዊ ሥራ ነው የተሰባስባችሁትን?

    Reply
  4. ጎልጉላዊው ደላዥ says

    November 30, 2019 09:46 pm at 9:46 pm

    ጎልጉላዊው ደላዥ

    ይህ ጽሁፍ ዜናም አስተያየትም የግምት ወሬና ማስጠንቀቂያም ይዟል
    ጃዋርና ደንቆሮ ቄሮዋች ተጠንቀቁ፤ ክትትል እየተደረገባችሁ ነው፤ የገንዘብ ማሰባሰቢያና ማስተላለፊያ መንገዳችሁ እየተደረሰበት ነው፤ የሚል ማስጠንቀቂያ ነው፤
    ክትትሉ የትና በእነማን እየተደረገ እንድሆነ የግምት ወሬም ሰንቋል፤ ደግሞም “የጎልጉል ምንጮች” የሚባሉ እንደማማለያ ወይም ማጣፈጫ በተን ተደርገዋል፤ለነገሩ በትውውቅና በአጋጣሚ የተገኘን መረጃ ልክ የራስ የምርመራ ጋዜጠኝነት ሥራ አድርጎ ማቅረብ በተለይ በጎልጉል በተደጋጋሚ ይስተዋላል፤ ለወሬዋ ታኮ ለማስገባት ታስቦ ነው፤ ኧረ አንባቢ አትናቁ! ለላው ደግሞ ጎልጉል አስተመማኝ በመረጃ የተምርኮዘ ዜና የሚያቀርብ አካል አድርጎ “እኛ እኮ በጣም አሪፎች ነን፤ ማንም አያክለንም” የሚል መታበይም ነው፤ ባላፈው ዘሀበሻ የውሸት ዜና ሠራ ብላችሁ የፃፋችሁትና የዘለፋችሁበት የብዕሩ ቀለም ሳይደረቅ ዕውነት ሆኖ ሲገኝ ይቅርታም ለመጠየቅ ከበዳችሁና ዝም አላችሁ – አንባቢ ይታዘባል! አሚን አሚር የተባለ በምንም መለኪያ የሚኒስቴር ማዕረግ የምይገባውን እያዳነቃችሁ ተሸለመ እኮ ሽልማቱም ይኸውና ገለመሌ አላችሁ -ኧረ ተዉ የወያኔ አሽከርና ተላላኪ የነበሩና አሁንም እበላ ባይ ሆዳም ካድሬና ሹማንትን አንዱን ማድነቅ አንዱን ማንኳሰስ ያስተዛዝባል – ሁሉም ወያኔዎችና ሆዳም አሽከሮቻቸው ሊወገዙ እንጂ በምንም ሁኔታ ሊመሰገኑ አይገባም፤ አርታኢ ተብየው በሞደሬሽን ስም አስተያየት ከመደለዝ ፋታ ውሰድ – ሌሎችም አንባቢዎች አስተያየቱን እንዲያዩት ተው

    Reply
  5. Hager says

    December 2, 2019 09:59 am at 9:59 am

    Western Destruction Of Western Culture.Is Ethiopia as such immune from such demonic menace?Read it. http://www.realjewnews.com/?p=561

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule