• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሓት/ትህነግ በአጥር ላይ

November 27, 2019 06:14 am by Editor Leave a Comment

ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የተገንጣዮች ጥርቅም፤ አዲስ የተመሠረተውን ብልጽግና ፓርቲ አልቀላቀልም ብሎ ካፈነገጠ ወዲህ ሁኔታዎች መስመር እየለቀቁበት ነው። ላሁኑ አጥር ላይ መንጠልጠሉን አማራጭ አድርጓል።

እስካሁን በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኘው ትህነግ/ህወሓት መሪ የነበረው መለስ በሥልጣን በቆየበት ዘመን ሲዘልፋቸው የኖረውን ተቃዋሚዎች ባንድ ወቅት እንዲህ ብሏቸው ነበር፤ አጥር ላይ መሆንና አንድ እግር ከግቢ ውስጥ ሌላኛውን ከውጭ ማድረግ አይቻልም። በአሁኑ ወቅት ህወሓት ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ የመለስን አጽም ካላበት ቦታ እንዲላወስ ያደረገ ሆኗል። አንድ እግሯ መቀሌ፤ ሌላው እግሯ አዲስ አበባ ሆኗል።

ባለፈው ዓመት ሐዋሳ ላይ በተደረገው የኢህአዴግ ፲፩ኛ ስብሰባ የግምባሩን ውህደት አስመልክቶ ጠቅላላው ጉባዔ የኢህአዴግ ምክርቤት ውህደቱ እንዲያስፈጽም ውክልና ሰጥቶት ነበር። ይህ ሲወሰን ህወሓቶች እጃቸውን ሰቅለው ዶ/ር ዐቢይን በሊቀመንበርነት እንደመረጡት ይህንንም ውሳኔ በሙሉ ድምጽ ደግፈዋል።

ላለፉት በርካታ ወራት አገር በማተራመስና ሕዝብን በማጋደል ሥራ ተጠምደው የነበሩት ህወሓቶች የማይደርስ መስሏቸው የግምባሩ ውህደት ሲደርስ አዲስ ትርክት ጀመሩ። ውህደት ጠቅላይነት ነው፤ አሃዳዊነት ነው፤ መብት ገፋፊ ነው፤ በማለት ሙሾአቸውን አሰሙ። ለነጻነት እንታገላለን ሲሉ እና ሕዝብ ሲደግፋቸው የነበሩ፤ ሕዝብን ክደው ቶርቸር ሲያደርጋቸው ከነበረው ህወሓት ጋር በመሰለፍ ፌደራሊስት ነን አሉ። የሚያዋጣ መስሏቸው ገፉበት።

ውህደቱ ዕውን ሲሆን ሦስቱ እህት ፓርቲዎች በሙሉ ድምጽ ሲደግፉ ለስብሰባው አዲስ አበባ ከመጡት የህወሓት አባላት መካከል ፊት አልባው መቀሌ ሲቀር ስድስቱ ተቃወሙ፤ ሁለቱ ደግሞ ለሽንት ወጥተው ነበር ተባለላቸው። እነዚህ የወጡት ደብረጽዮንና ኬሪያ እንደነበሩ በአንዳንዶች ተዘግቧል።

የህወሓት ተወካዮች ከሥራ አስፈጻሚው የውህደት ስብሰባ በኋላ ከዶ/ር ዐቢይ ጋር ውይይት እንዳደረጉ ተሰምቷል። በውጤቱም ስምምነት ሳይደርሱ ተለያዩ ቢባልም ጥያቄያቸው ውድቅ ተደረገባቸው የሚለው በአሳማኝነት ለመቀበል የሚቀል ይመስላል። መቀሌም ከደረሱ በኋላ ከተለያየ አቅጣጫ ተቃውሞ ሲደርስባቸው ያለፈው እሁድ ውህደቱን የሚቃወም ሰልፍ ጠሩ። ጊዜው ሲደርስ ግን ሠልፉ የተፈለገውን ዓላማ ለማሳኪያ እንደማይሆን በተረዱበት ጊዜ ሰረዙት። ከዚህ ጋር ተያይዞ የትግራይ ሕዝብ ከአዲስ አበባ ይዘው የመጡትን ውሃ የማይቋጥር ወሬ አንቀበልም እያላቸው እንደሆነ አየተሰማ ነው ያለው።

ሁኔታው ያላማራቸው የህወሓት መሪዎች ባንድ በኩል ለመዋሃድ እንፈልጋለን በማለት አዲስ አበባ ሽማግሌ መላካቸው የተሰማ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ኢህአዴግ በውህደት ስም አዲስ ፓርቲ ነው የመሠረተው፤ የኢህአዴግን ውርስ በመውሰድ አዲስ ፓርቲ መመሥረት አይቻልም፤ ተሰብሰበን እንወስናለን በማለት በደብረጽዮን አማካኝነት መግለጫ ሰጥተዋል።

ይህ ማለት እንግዲህ አምና የኢህአዴግ አጠቃላይ ጉባዔ ሐዋሳ ላይ የግምባሩን ውህደት ምክርቤቱ እንዲፈጽመው በማለት ሲወስን በሙሉ ድምጽ የወሰኑትን በመካድ ነው። ለሚዲያ ፍጆታ ብዙ ማወናበጃ መጠቀም ይቻል ይሆናል፤ ማስረጃ በሚጠቀስበት የፓርቲ ስብሰባ ላይ ግን እንዲህ ዓይነት ቀልድ እንደማይቻል እነጌታቸው ረዳና ደብረጽዮን አሳምረው ያውቁታል። ለዚህም ነው በሽምግልና እና በአንዋሃድም መካከል ላይ የተንጠለጠሉት። እውነታው ግን “የአስገቡኝ” ልመና ላይ ያሉ ለመሆናቸው አመላካቾች አሉ።

ከሁለት ቀን በፊት በትግራይ ክልል መሪ ደብረጽዮን ፊርማ የሽሬ ነዋሪ ለስብሰባ ተጠርቶ ነበር። ዋናው አጀንዳ የነበረው ስለ ውህደቱና በቀጣይ ለማድረግ ስለታሰበው ለመወያየት የነበረ ሲሆን ስብሰባውን በመቃወም ተሰብሳቢው ጥሎ መውጣቱ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ተዘግቦበታል። ለስብሰባ የመጣው ሕዝብ ተቃውሞውን እያሰማ ወደ ከተማ ወጥቶ የነበረ ሲሆን በተቃውሞ ሰልፉ ላይም “አማራ ጠላታችን አይደለም፤ ወደ ጦርነት መግባት አንፈልግም” የሚሉ መፈክሮች መሰማታቸው ታውቋል። ውህደቱንም በተመለከተ ህወሓት ለመዋሃድ አለመፈለጉ አንድ ጉዳይ ሲሆን መዋሃድ ከመገንጠል ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም በማለት ሰልፈኞቹ በተቃውሟቸው አስረድተዋል።

ህወሓት ተስፋ ያደረጋቸው አጋር ፓርቲዎችም አፋር፣ ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ሐረሪ ውህደቱን እንቀበላለን ብለው ውሳኔ አስተላልፈዋል። ቀሪ አለኝ ብለው ተስፋ ያደረጉት ሶማሊም ዛሬ (ማክሰኞ) ውህደቱን እንደሚቀበል ወስኗል። ህወሓቶች በፌዴራሊስት ስም የሚሰበሰቧቸው ጥርቅምቃሚ ፓርቲዎች የአየለ ጫሚሶና የትዕግስቱ ዐወል ፓርቲዎች እንኳንስ ከህወሓት ጋር ወግነው ገና ከጅምሩ ሕዝብ አንቅሮ የተፋቸው በዘመነ ህወሓት የደኅንነቱ ተከፋዮች እንደነበሩ የሚታወቅ ነው።

መቀሌ ላይ “ኢትዮጵያን እናድን” በሚል ስብሰባ ጠርታ የነበረችው ህወሓት ስብሰባው እንደታሰበው ሳይሆን በመቅረቱ በቀጣይ ምን ማድረግ አለብን የሚለውን በለመደችው ድርጅታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አሠራር በደብረጽዮን አማካኝነት በጠራችው ስብሰባ በቅርቡ ታስወስናለች።

በአሁኑ ጊዜ ከብዙ አቅጣጫ አጣብቂኝ ውስጥ የገባችው ህወሓት የመሪዋን መለስ ውለታ በልታ፤ በመቃብር ያለውን መሪዋን አሳፍራ ባጥር ላይ ተንጠልጥላ ትገኛለች። ሰሞኑን በጠራችው ስብሰባ ደግሞ ወይ እንዋሃድ ወይም አንጓጉል ብላ በመዋሃድ ስም መሠሪ ተግባሯን ትቀጥላለች ወይም ጓጉላ መጨረሻዋ መገለል ይሆናል። ለማንኛውም ህወሓቶች ተሰብስበው ሲጠያዩ (ሲገማገሙ) ቢያንስ አዲስ ህንፍሽፍሽ ወይም እርስበርስ ወደመጠፋፋት የሚወስድ መከፋፈል ሊከሰት ይችላል የሚለው ሌላው የሚጠበቅ ነው።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, meles zenawi, Middle Column, prosperity party, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule