ዓለምአቀፉ የፖሊስ መሥሪያ ቤት (ኢንተርፖል) እንደሚለው ከሆነ አሸባሪዎችን የማድረቂያው አንዱ መንገድ የገንዘብ እንቅስቃሴያቸውን መከታተል ነው። መ/ቤቱ አሸባሪዎችን በገንዘብ የመርጃ መንገዶች ብሎ የሚከተሉትን አስፍሯ፤ ዕርዳታ ከደጋፊዎች በማሰባሰብ፣ በማጭበርበር፣ ትርፍ አልባ ድርጅት በመመሥረትና አለአግባብ በድርጅቱ ስም መበልጸግ (OMN በአሜሪካ አገር በትርፍ አልባ ድርጅትነት የተመዘገበ መሆኑን ልብ ይሏል)፣ ሰዎችን አፍኖ በመውሰድና በምላሹ ካሣ በመጠየቅ፣ በሕገወጥ ንግድ በመሠማራት (ይህም በነዳጅ፣ በከሰል፣ በአልማዝ፣ በወርቅና በአደንዛዥ ዕጽ የሚጠቀልል ነው)። ይህንን የገንዘብ (የዕርዳታ ድጋፍ) ማሰብሰብና ማዘዋወር ለመቆጣጠር በአገራት መካከል መረጃ የሚለዋወጥና ደረጃ የሚያወጣ Financial Action Taskforce (FATF) የሚባል ግብረኃይል ኢንተርፖል አለው። … [Read more...] about የጃዋር ፋይናንስ በክትትል ራዳር ውስጥ – ዳያስፖራ ደጋፊዎች ስለ ነገ አያውቁም!