የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የወንጀል ችሎት የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ወደ አምቦ እንዳይሄድ ከእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ጋር በጋራ ተንቀሳቅሰዋል በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ለመጨረሻ ጊዜ በማለት 12 ቀናት ፈቀደ። ተጠርጣሪዎች አዲሱ ቶሎሳ፣ ደስታ ሽኩር ፣ጥላሁን ለታ፣ አበራ ሁንዴ፣ ሙስተዋሪድ አደም፣ አረፋት አቡበከር፣ አማን ቃሎ፣ ሱልጣን በድያ፣ ውቢ ቡርቃ፣ ሀቢቢ ሳፈው፣ ጉቱ ሙሊሳ፣ ሲሳይ በቀለ፣ ሮባ አዳነ እና ጉልማ ከፈና ናቸው። እንደ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ ሁሉም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት የሟች አስከሬን ወደ አምቦ ሳይደርስ አዲስ አበባ ተመልሶ ወደ ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ይዘው ሲገቡ የተገኙ ናቸው። ከእነ አቶ ጃዋር ጋር በመሆን አስከሬኑ ወደ … [Read more...] about የሀጫሉ አስከሬን ወደ አምቦ እንዳይሄድ አድርገዋል በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ ቀን ተፈቀደ
jawar massacre
የእስክንድር የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሆነ፤ የአስራት ቲቪ ሠራተኞችና በሃይማኖት በዳዳ ግድያ የተጠረጠሩ ፍርድቤት ቀረቡ
የፖሊስ ምርመራ ቡድን ፍርድ ቤቱ በሰጠው የምርመራ ጊዜ ያገኘውን የምርመራ ሥራ ለፍርድ ቤቱ አብራርቶ ለቀሪ የምርመራ ሥራዎችም የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል። በምርመራ ቡድኑ አፈፃፀም እና ቀጣይ ጥያቄ ዙሪያ የተጠርጣሪ ጠበቆች እና የምርመራ ቡድኑ ያደረጉትን ክርክር የመረመረው ችሎቱ፣ የፖሊስን የተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ጥያቄ አልተቀልኩም ብሏል። ጠበቆችም አቶ እስክንድር ነጋ የዋስትና መብቱ እንዲጠበቅ የጠየቁ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል። ምክንያቱ ደግሞ መርማሪ ቡድኑ አቶ እስክንድር የጠረጠረበት ወንጀል ሞት ያስከተለ በመሆኑ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ከ15 ዓመት በላይ ሊያስቀጣቸው ስለሚችል ነው ብሏል። በሌላ በኩል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአቶ እስክንድር ላይ የቀዳሚ ምርመራ ፋይል እንዲከፈት የወሰንኩ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ይስጠኝ በማለት … [Read more...] about የእስክንድር የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሆነ፤ የአስራት ቲቪ ሠራተኞችና በሃይማኖት በዳዳ ግድያ የተጠረጠሩ ፍርድቤት ቀረቡ
“ውጭ ቁጭ ብለው መንገድ ዝጉ” የሚሉ “ከህወሃት በምንም አይሻሉም” የአርሲ ወጣት
* “በተማረ ጭንቅላት ብቻ ታግለን ማሸነፍ አለብን እንጂ መንገድ በመዝጋት (የለብንም)” የአርሲ ወጣት ሃገርን ለማፈራረስ የሚሰሩ የጸረ-ሰላም ኃይሎችን ሴራ በማክሸፍ የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ የአርሲ ዞን ወጣቶች ገለጹ። ከአርሲ ዞን 26 ወረዳዎችና የአሰላ ከተማን ጨምሮ ከሶስት የከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ወጣቶች የተሳተፉበት የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ ዛሬ በአሰላ ከተማ ተካሒዷል። ከኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች መካከል ወጣት ከማል ንጉሴ “ሀገሪቷን ለማስቀጠል እኛ ወጣቶች በአንድነት ሆነን የጥፋት ሃይሎችን እንታገላለን ” ብሏል። “ወጣቶች በስሜት ተነሳስተን ጥፋት በማስከተል ሳይሆን በተማረ ጭንቅላት ብቻ ታግለን ማሸነፍ አለብን እንጂ መንገድ በመዝጋት፣ የዜጎችን ህይወት በማጥፋትና ንብረት በማውደም አንድም ለውጥ አይመጣም” ብሏል። ለመንግስት … [Read more...] about “ውጭ ቁጭ ብለው መንገድ ዝጉ” የሚሉ “ከህወሃት በምንም አይሻሉም” የአርሲ ወጣት
የእነ ጃዋር ጉዳይ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት እያመራ ነው
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቶ ጃዋር መሀመድና እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ የቅደመ ምርመራ ምስክሮችን እንዲያሰማ ብይን ሰጠ። አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች በዛሬው ዕለት (ሐሙስ) በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል። የዐቃቤ ሕግ ጥያቄ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋርን ጨምሮ አጠቃላይ 14 ተጠርጣሪዎች አቶ ጃዋር መሃመድ በሚል መዝገብ በመዝገብ ቁጥር 215585 ላይ የቅድመ ምርመራ መዝገብ የከፈተ ሲሆን፥ በዚህ መዝገብ ላይ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል የተጠረጠረ ጋዜጠኛም ተካቷል። አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 215585 የቀዳሚ ምርመራ እንዲደረግባቸው ጠይቋል። በተጨማሪም የፌደራል … [Read more...] about የእነ ጃዋር ጉዳይ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት እያመራ ነው
የበቀለ ገርባ የክስ ዝርዝር
ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ከወር በፊት በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ ላይ ያሉት አቶ በቀለ ገርባ፣ የእርስ በርስ ግጭት በማነሳሳትና ሌሎች ወንጀሎች እንደሚከሰሱ መወሰኑን ዓቃቤ ሕግ ረቡዕ ዕለት አስታወቀ። አቶ በቀለ በበኩላቸው እንደተናገሩት የሃጫሉ ሞትን ምክንያት በማድረግ የተቀሰቀሰው ሁከትና ግጭት፣ በራሱ በሕዝቡ የተመራ እንጂ እሳቸው ይህንን ማድረግ የሚያስችል ሠራዊት እንደሌላቸው ገልጸው፣ መንግሥት ፍርድ ቤትን በመጠቀም ተቀናቃኙን ለማጥፋት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቢያነ ሕግ ማክሰኞ ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ልደታ ማስቻያ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው እንደተናገሩት፣ ተጠርጣሪው አቶ በቀለ በምን እንደሚከሰሱ ተወስኗል ብለዋል። ክስ የሚመሠረትባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት … [Read more...] about የበቀለ ገርባ የክስ ዝርዝር
ፖሊስ፤ “(ጃዋር) የታዋቂ ሰዎችን ስልክ” ጠልፎ ነበር
የፌዴራል መርማሪ ፖሊስ በአቶ ጃዋር ሲራጅ መሃመድ ቤት በድጋሚ ባደረገው ፍተሻ በግለሰብ እጅ የማይገኙ ሳተላይቶችና ከውጭ በድብቅ የገቡ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ማግኘቱን ገለጸ። መርማሪ ፖሊስ በሃምሌ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. በፍርድቤቱ በተሰጠው የ13 ቀን ተጨማሪ ጊዜ የሠራውን አዳዲስ የምርመራ ሥራዎችን ይፋ አድርጓል። መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 13 ቀናት ሰራው ያለው አዲስ ሥራ፤ በአቶ ጃዋር ቤት በድጋሚ በተደረገው ፍተሻ የቴሌኮም መሳሪያዎች፣ በግለሰብ እጅ የማይገኙ የኤሌክትሮኒክስና የሳተላይት ዲሾችን ጨምሮ ሌሎችንም አግኝቷል። መሣሪያዎቹ ከውጭ በድብቅ መግባታቸውና ከውጭ ሀገር ባለሞያ አስመጥተው በድብቅ ማስገጠማቸውን ጠቅሷል። በመሣሪያው የታዋቂ ሰዎችን ስልክ በመጥለፍ ሚስጥራዊ ንግግራቸውን ያዳምጡ እንደነበር ማስረጃ ሰብስቢያለሁ ብሏል።አቶ ጃዋር ጋር የተገኙት … [Read more...] about ፖሊስ፤ “(ጃዋር) የታዋቂ ሰዎችን ስልክ” ጠልፎ ነበር
ፖሊስ፤ በቀለ ከጳውሎስ ሆ/ል እስከ ቡራዩ ኬላ የአመፅ ጥሪ በስልክና በአካል አስተላልፏል
በቀለ፤ የታሰርኩበት ቦታ ቴሌቪዥን ስለሌለ እንዲፈቀድልኝ ፍርድቤቱ ትዕዛዝ ይስጥልኝ “እንድታሰር የተደረገው ፖለቲከኛ በመሆኔ በምርጫ እንዳልወዳደር ነው” ተጠርጣሪ አቶ በቀለ ገርባ“መንግሥት የተፈጠረን ወንጀል ያጣራል እንጂ ወንጀል ፈጥሮ አያስርም” የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መርማሪ ቡድን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን አቶ በቀለ ገርባ በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ሽኝት ወቅት ከጳውሎስ ሆስፒታል እስከ ቡራዩ ኬላ ድረስ አብረው እንደነበሩ፣ የአመፅ ጥሪ በስልክና በአካል ሲያስተላልፉ እንደነበር በማስረጃ ማረጋገጡን ለፍርድ ቤት አስታወቀ። በሁከቱ በደረሰው የሰዎች ሞትና የንብረት ውድመት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኦፌኮ አመራር አቶ በቀለ ገርባ ግን፣ “መርማሪ ቡድኑ አንድ ጊዜ በስልክ ትዕዛዝ ሰጠ ይላል። በሌላ ጊዜ ደግሞ በአካልና በስልክ የአመፅ ጥሪ … [Read more...] about ፖሊስ፤ በቀለ ከጳውሎስ ሆ/ል እስከ ቡራዩ ኬላ የአመፅ ጥሪ በስልክና በአካል አስተላልፏል
ችሎት! ሃምዛ፣ የህወሓት አመራሮች፣ ይልቃልና እስክንድር
በወንጀል ተጠርጣሪ ሃምዛ ቦረና በአቶ ሃምዛ ቦረና መዝገብ የተካተቱ 9 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። መርማሪ ፖሊስ የሰራውን ተጨማሪ የምርመራ ስራ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከዘጠኙ ተጠርጣሪዎች መካከል ስምንቱ የአቶ ጃዋር መሃመድ ጠባቂዎች ሲሆኑ በፖሊስ ምርመራ ላይ መቃወሚያ አቅርበዋል። መርማሪ ፖሊስ ሌሎች በርካታ የሰዎች እና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሳብ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ ብሎ ጠይቋል። ፍርድ ቤት ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን ጊዜ ውስጥ 8 ቀን ፈቅዶ ተለዋጭ ቀጠሮ ለሃምሌ 29/2012 ዓ/ም ሰጥቷል። መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 11 ቀናት፤ በተጠርጣሪዎች ላይ የተያዙ መሳሪያዎችን ምርመራ አድርጓል፤ 10 የተከሳሽ ፤ 20 የምስክር ቃል ተቀብሏል።አንደኛ ተጠርጣሪ አቶ ሃምዛ ቦረና የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ብሄርን ከብሄርና የሃይማኖት ግጭት … [Read more...] about ችሎት! ሃምዛ፣ የህወሓት አመራሮች፣ ይልቃልና እስክንድር
ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚና አብዲ አለማየሁ ፍርድ ቤት ቀረቡ
አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በከሰአት በኋላ በነበረው ችሎትም የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በቡራዩና አዲስ አበባ በተፈጠረ አመጽና ሁከት በደረሰ የሰውና የንብረት ጉዳት የተጠረጠሩ 8 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በጠዋቱ ችሎት በቀዳሚነት የቀረቡት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ላይ መርማሪ ፖሊስ የሰራውን የምርመራ ስራ ይፋ አድርጓል። በዚህም የምስክር ቃል መቀበሉን፣ ወንጀሉ የተፈጸመበት ስፍራን በቴክኒክ ማስረጃ ማረጋገጡን፣ ግብረ አበሮቻቸውን በቁጠጥር ስር አውሎ ምርመራ እየሰራ መሆኑን፣ አርቲስት ሃጫሉ የተገደለበትን ሽጉጥ ከተጠርጣሪዎች ቤት ከተቀበረበት ጓሮ ማውጣቱን እና በምርመራ ማረጋገጡን አስረድቷል፡፡ ከዚህ ባለፈም በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ስልካቸውን … [Read more...] about ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚና አብዲ አለማየሁ ፍርድ ቤት ቀረቡ
በሁለት ሪዞርቶች ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ውድመት
ሐይሌ ሪዞርት በዝዋይ እና በሻሸመኔ ከተሞች ለወደመበት ኢንቨስትመንት መንግስት ድጋፍ ካደረገ ወደ ስራው እንደሚመለስ አስታውቋል። የድርጅቱ ባለቤት አትሌት ሃይሌገብረስላሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አንዳለው የድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞትን ተከትሎ በዝዋይ እና ሻሸመኔ ከተሞች በስራ ላይ የነበሩት ሆቴሎች ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል። አትሌት ሃይሌ ከዚህ በፊት በነዚህ ከተሞች የነበረውን ኢንቨስትመንት ማቋረጡን ያስታወቀ ቢሆንም አሁን ግን መንግስት ለወደመበት ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንት ድጋፍ ካደረገለት ወደ ስራ እንደሚመለስ ገልጿል። የዝዋዩን ሪዞርት ወደ ስራ ለመመለስ ከአንድ ዓመት በላይ የጥገና ጊዜ የሚፈጅ ሲሆን የሻሸመኔው ሀይሌ ሪዞርት ቅርንጫፍ ግን የግድ እንደ አዲስ መገንባት ስለሚጠይቅ ወደ ስራ ለመመለስ በትንሹ ሶስት አመታትን እንሚፈጅ አትሌት ሀይሌ … [Read more...] about በሁለት ሪዞርቶች ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ውድመት