• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሀጫሉ አስከሬን ወደ አምቦ እንዳይሄድ አድርገዋል በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ ቀን ተፈቀደ

August 7, 2020 06:40 pm by Editor Leave a Comment

የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የወንጀል ችሎት የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ወደ አምቦ እንዳይሄድ ከእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ጋር በጋራ ተንቀሳቅሰዋል በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ለመጨረሻ ጊዜ በማለት 12 ቀናት ፈቀደ። 

ተጠርጣሪዎች አዲሱ ቶሎሳ፣ ደስታ ሽኩር ፣ጥላሁን ለታ፣ አበራ ሁንዴ፣ ሙስተዋሪድ አደም፣ አረፋት አቡበከር፣ አማን ቃሎ፣ ሱልጣን በድያ፣ ውቢ ቡርቃ፣ ሀቢቢ ሳፈው፣ ጉቱ ሙሊሳ፣ ሲሳይ በቀለ፣ ሮባ አዳነ እና ጉልማ ከፈና ናቸው። 

እንደ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ ሁሉም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት የሟች አስከሬን ወደ አምቦ ሳይደርስ አዲስ አበባ ተመልሶ ወደ ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ይዘው ሲገቡ የተገኙ ናቸው። 

ከእነ አቶ ጃዋር ጋር በመሆን አስከሬኑ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ 10 ቀን ተለቅሶ የሚኒሊክ ሐውልትን በማፍረስ ቤተመንግስቱን መቆጣጠር የሚለውን ዓላማ ሲያራምዱ የተገኙ መሆናቸውንም ጠቅሷል ፖሊስ በምርመራ መዝገቡ። 

ከተጠርጣሪዎች  ሲሳይ በቀለ የተባለው፣ “ሟች ዘመዴ ነው ለቅሶ ልደርስ ሄጄ አስከሬኑ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ አብሬ ተመልሼ ከኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተያዝኩ እንጂ የፈፀምኩት ጥፋት የለም፤ የዋስትና መብቴ ይጠበቅልኝ” በማለት አመልክቷል። 

ሌላኛው ወቢ ቡርቃ የተባለው ተጠርጣሪ ያጠፋው ጥፋት እንደሌለ እና የዩኒቨርስቲ ተማሪ እንደመሆኑ መጠን “የነገ ተስፋዬን በማየት ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቴን ይጠብቅልኝ” ብሏል። 

በእስር ሆኖ በኮሮና ቫይረስ ተይዞ 15 ቀን በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሲታከም ሕመሙን ተገናዝቦ እንደ ታካሚ ሳይሆን እንደ እስረኛ ሆኖ 15 ቀኑን በመጥፎ ሁኔታ ማሳለፉንም ለችሎቱ ገልጿል። 

ጠበቆችም እንዲሁ የተጠርጣሪዎች የየግል ጥፋት ተለይቶ አልተቀመጠም፣ ያጠፉት ጥፋትም የለም፤ በዚህም የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ጠይቀዋል። 

የምርመራ ቡድን የሰጠውን ምላሽ ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ተፈፀመ ከተባለው ወንጀል ስፋት አንጻር የተጠየቀውን የዋስትና ጥያቄ አልተቀበለም። 

የፖሊስን የምርመራ መዝገብ እየተመለከተ መሆኑን በመጥቀስ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ 12 ቀናቱን ለመጨረሻ በማለት ፈቅዷል። 

ወቢ ቡርቃ የተባለው ተጠርጣሪ በኤካ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ሕመምተኛ ሁኖ የቆየበትን ሁኔታ ሆስፒታሉ በጽሁፍ እንዲያስረዳም አዝዟል። 

ውጤቱን ለመጠበቅ ፍርድ ቤቱ ለነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። (ምንጭ፤ ጥላሁን ካሳ፤ ኢብኮ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Law, Right Column, Uncategorized Tagged With: chilot, jawar massacre, ችሎት

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule