በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ምክንያት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ጨምሮ በርካታ ተጠርጣሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ለሕዝብ ተደራሽ እንዲደረግ ምክር ሐሳብ ቀረበ። የፍርድ ቤት ውሎ በቀጥታ ሥርጭት ለሕዝብ ተደራሽ እንዲሆንና ሌሎች አማራጮችን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው፣ የኢፌዴሪ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ነው። በተቋሙ ዋና እንባ ጠባቂ እንዳለ ኃይሌ (ዶ/ር) ተፈርሞ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ለዳኞችና ዓቃቢያነ ሕግ፣ ለተጠርጣሪዎችና ለችሎት ታዳሚዎች ደኅንነትና ጥበቃ አመቺ በሆነ ሰፊ አዳራሽ ችሎት ማስቻልን የመጀመርያ አማራጭ አድርጓል። የፍርድ ቤቱን ውሎ ሁሉም የመንግሥትና የግል፣ የሕትመትና የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ አካላት ብቻ እንዲዘግቡት ማድረግና በዘገባዎቻቸው የችሎቱን … [Read more...] about የፍርድ ቤት የችሎት ውሎ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት እንዲተላለፍ ምክረ ሐሳብ ቀረበ