• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ውጭ ቁጭ ብለው መንገድ ዝጉ” የሚሉ “ከህወሃት በምንም አይሻሉም” የአርሲ ወጣት

August 6, 2020 09:26 pm by Editor Leave a Comment

* “በተማረ ጭንቅላት ብቻ ታግለን ማሸነፍ አለብን እንጂ መንገድ በመዝጋት (የለብንም)” የአርሲ ወጣት

ሃገርን ለማፈራረስ የሚሰሩ የጸረ-ሰላም ኃይሎችን ሴራ በማክሸፍ የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ የአርሲ ዞን ወጣቶች ገለጹ።

ከአርሲ ዞን 26 ወረዳዎችና የአሰላ ከተማን ጨምሮ ከሶስት የከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ወጣቶች የተሳተፉበት የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ ዛሬ በአሰላ ከተማ ተካሒዷል። 

ከኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች መካከል ወጣት ከማል ንጉሴ “ሀገሪቷን ለማስቀጠል እኛ ወጣቶች በአንድነት ሆነን የጥፋት ሃይሎችን እንታገላለን ” ብሏል።

“ወጣቶች በስሜት ተነሳስተን ጥፋት በማስከተል ሳይሆን በተማረ ጭንቅላት ብቻ ታግለን ማሸነፍ አለብን እንጂ መንገድ በመዝጋት፣ የዜጎችን ህይወት በማጥፋትና ንብረት በማውደም አንድም ለውጥ አይመጣም” ብሏል።

ለመንግስት የሚቀርብ ጥያቄ ቢኖር እንኳን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከርና በመወያየት መፍታት እንደሚቻል ገልጾ፤ በክልሉ የተፈፀመው ተግባር ቄሮንም ሆነ ኦሮሞን እንዲሁም ማንኛውንም የህብረተሰብ ክፍል የማይወክል መሆኑን ተናግሯል።

“ውጭ ቁጭ ብለው መንገድ ዝጉ፣ በገበያ ላይ አድማ አድርጉ፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አግቱ ብለው ትዕዛዝ የሚያስተላልፉ አካላት በተመቻቸ ኑሮ ላይ ሆነው የደሃ ልጆችን ያስቀጥፋሉ ከትናንትናው ህወሃት በምንም አይሻሉም” ብሏል።

“የኦሮሞ ህዝብ በባህሉ ሌላውን ብሔር በጉዲፈቻና ሞጋሳ ወደ ራሱ በማምጣት አቃፊነትን መቻቻልና አብሮነትን ያስተማረ ነው” ያለው ደግሞ ወጣት ሙሐመድ ተሲ ነው።

“እኛ የኦሮሞ ወጣቶች ሀገር ማፍረስ ሳይሆን ከአባቶቻችን በወረስነው ጀግንነትና አንድነት ሀገሪቷን ገንብተን ማለፍ ነው” ብሏል።

ሌላኛው አስተያያት ሰጪ ወጣት ድሪባ ንጉሴ በበኩሉ “በመንግስት መዋቅር ውስጥ ሆነው ከውጭ ጠላት ጋር የሚሰሩ፣ የጥፋት መመሪያ የሚያስተላልፉ አመራሮች በህግ መጠየቅ አለባቸው” ብሏል።

“የኦሮሞ ህዝብ መቻቻልና አብሮነትን ከገዳ ስርዓት ነው የተማረው” ያለው ወጣት ድሪባ “ወጣቶች በተደላደለ ህይወት ውስጥ ቁጭ ብለው ትዕዛዝ የሚሰጡትን ሃይሎች መስማት የለባቸውም” ብሏል።

የአሰላ ከተማ ከንቲባ አቶ ገብሬ ዑርጌሶ በበኩላቸው የከተማዋ ወጣቶች ንብረት እንዳይወድም ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ ወሳኝ ሚና መጫወታቸውን ተናግረዋል።

ጥቂት ሰዎች የጥፋት ተልእኮ ተቀብለው ሀገር የመበጥበጥ ዓላማ እንዳላቸው ወጣቶች የተረዱበት መድረክ መሆኑንም ጠቅሰው ወጣቶች ጥፋትን ከመከላከል ባለፈ የአፍራሽ ተልዕኮ አስፈፃሚ እንዳይሆኑ የእናትና አባታቸውን ንብረትና ባህል እንዲጠብቁ አሳስበዋል።

የአርሲ ዞን አስተዳደር አቶ ጀማል አሊይ እንደገለጹት የትራንስፖርት፣የንግድና የገበያ እንቅስቃሴ እንዳይኖር የሚያደርጉ የጥፋት ሃይሎች በወጣቱ ዘንድ ቦታ እንደሌላቸው ከመድረኩ መረዳታቸውን ገልጸዋል።

በዞኑ አስተማማኝ ሰላም በመስፈኑም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለሱንም ተናግረዋል።

ወጣቶች መንግስት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከጀመረው በጎ ተግባር ጎን እንደሚቆሙ ማረጋገጣቸውን የገለጹት አቶ ጀማል፤ ንብረት በማውደምና በማቃጠል የሚገኝ ውጤት ባለመኖሩ በሰላም ማስፈን ላይ አሁንም ተባብረው መስራት እንደሚገባቸው አስገዝበዋል።

መድረኩን የመሩት የመለስ ዜናዊ አካዳሚ ፕሬዘዳንት አቶ አወሉ አብዲ በበኩላቸው መንግስት የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥና አጥፊዎችን ለህግ ከማቅረብ ጎን ለጎን ንብረት የተጎዳባቸውን መልሶ ለማቋቋም እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

“በአሁኑ ወቅት የምግብ፣ አልባሳት፣ የዘርና የአፈር ማደባሪያ ጭምር ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው” ያሉት አቶ አወሉ የዞኑ ማህበረሰብ ተጎጂዎችን በራሱ መልሶ ለማቋቋምና ወደ ቀደመው ህይወት እንዲመለሱ ለማድረግ በየወረዳው ኮሚቴ ተደራጅቶ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።

በድርጊቱ የተሳተፉ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ውስጥና በህብረተሰቡ ዘንድም ያሉ የጥፋት ተልእኮ ፈፃሚዎችን ለህግ እንዲቀርቡ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

የአርቲስት ሃጫሉን ሞት ተከትሎ በአሰላ ከተማና በአርሲ ዞን በተፈጠረው ሁከትና ግርግር የሰው ህይወት በማጥፋትና ንብረት በማውደም የተጠረጠሩ ከ1ሺህ 300 በላይ ግለሰቦች ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። (ኢዜአ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Right Column Tagged With: arsi, jawar massacre

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule