በተደጋጋሚ የክስ ቻርጅ እንዳይሰጠው ጥረት ሲያደርግ የነበረው ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ከግብርአበሮቹ ጋር “ተከሳሽ” የሚለውን መጠሪያ ትላንት ሰኞ መስከረም 11/2013 ተቀብለዋል፤ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በይፋ ክስ መስርቷል። ዐቃቤ ህግ በጃዋር መሐመድ እና ሌሎች 23 ተከሳሾች ላይ ክሱን በመሠረተበት ወቅት፤ ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች አንደኛ ወንጀል ችሎት፤ በውሎው የክስ ሰነዶቹ ለተከሳሾችና ጠበቆቻቸው እንዲከፋፈል አድርጓል። በመሆኑም እነ ጃዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባና ሀምዛ አዳነን ጨምሮ 18 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ተመስርቶባቸዋል። ተከሳሾቹ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ህገ መንግስትና ጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሱ ደርሷቸዋል። ዐቃቤ ህግ በክስ ሰነዱ ላይ 10 ክሶችን … [Read more...] about “ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” የተባሉበት ክስ ዝርዝር
jawar massacre
ጃዋርና ግብረአበሮቹ 10 ተደራራቢ ክሶች ተከፈተባቸው
አቃቤ ሕግ በእነ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ ላይ ክስ የሚመሰርትበት ቀን አርብ መስከረም 8፤ 2013ዓም ነበር። ሆኖም በዚህ ክስ ይመሰረታል ተብሎ በሚጠበቅበት የመጨረሻው ቀን ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። በዚህም አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ ለፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡ የነ ጃዋር መሐመድ ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ተናግረው ነበር። ሆኖም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ መሠረት ጃዋርና ሲራጅ መሐመድና ግብረአበሮቹ በ10 ተደራራቢ ክሶች ፋይል እንደከፈተባቸውና የክስ ቻርጁም መስከረም 11፤2013ዓም ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እንደሚደርሳቸው አስታውቋል። ዐቃቤ ሕግ ያወጣው ጽሁፍ ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል፤ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድ፤አቶ በቀለ ገርባ፤አቶ ሀምዛ አድናን እንዲሁም በሌሉበት የተከሰሱትን የኦሮሚያ ሜዲያ … [Read more...] about ጃዋርና ግብረአበሮቹ 10 ተደራራቢ ክሶች ተከፈተባቸው
እነ ጃዋር ይከሰሳሉ – ዐቃቤ ሕግ
በእነ ጃዋር ሲራጅ መሃመድ ላይ ተከፍቷል ከተባለው የክስ መዝገብ ጋር በተያያዘ በመጪው ሳምንት መግለጫ እንደሚሰጥ ዐቃቤሕግ አስታወቀ። ጃዋር ሲራጅ መሀመድን ጨምሮ በአጠቃላይ በ24 ሰዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 260215 በ10 ተደራራቢ ክሶች ማስከፈቱን ያስታወቀው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩን በማስመልከት በመጪው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት መግለጫ እንደሚሰጥ ተገለፀ። “ክስ መመሥረት ባለበት ጊዜ ውስጥ ባለመመሥረቱ ተከሳሾቹ ከሰኞ ጀምሮ ከእሥር ሊለቀቁ ነው የሚል ወሬ በሕዝብ ዘንድ ተሰራጭቷል” መግለጫው ዐቃቤ ሕግ ተቋሙ እየሰራ ያለውን ሥራ ማኅበረሰቡ እንዲያውቀው ለማድረግ የሚሰጥ ነው ብለዋል። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ መከፈቱን በተመለከተ ዛሬ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አጭር ጥቅል መረጃን ሰበር በሚል ርዕስ ሰጥቷል። “ፍርድ ቤት ራሱ ክሱ በዝርዝር … [Read more...] about እነ ጃዋር ይከሰሳሉ – ዐቃቤ ሕግ
እነ እስክንድር፥ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት
እነ አቶ እስክንድር ነጋ የአስተዳደሩን ሥልጣን በኃይል ለመያዝና ለሽብር ወንጀል መሰናዳት ወንጀሎች ተከሰሱ ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ውለው የቆዩት እነ አቶ እስክንድር ነጋ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀና ለ)፣ 35፣ 38፣ 240(1ለ) እና የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 6(2) ድንጋጌዎችን በመተላለፍ መንግሥትን ሰላም በመንሳትና እንዳይረጋጋ በማድረግ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥልጣንን ኃይልና አመፅ ተጠቅመው ለመያዝ በመንቀሳቀስና ለሽብር ወንጀል በመሰናዳት ወንጀሎች ክስ ተመሠረተባቸው። የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጳጉሜን 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕገ መንግሥትና የሽብር ወንጀሎች አንደኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት፤ በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ … [Read more...] about እነ እስክንድር፥ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት
“ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” ሊባሉ ነው
እነ ጃዋር መሐመድ መንግሥትን ኮንነው የፍትሕ ተቋማትንና ፍርድ ቤትን አመሠገኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠ በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግሥት ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 71 ቀናት በእስር ላይ ያሉት እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የጊዜ ቀጠሮና የቅድመ ምርመራ የፍርድ ቤት ሒደቶች መጠናቀቃቸውንና የምርመራ መዝገቡ መዘጋቱን አስመልክቶ፣ “ያለ ጥፋታችን እንድንታሰር አድርጎናል” ያሉትን መንግሥትን ኮንነው የፍትሕ ተቋማትንና ፍርድ ቤትን አመሠገኑ። ተጠርጣሪዎቹ ቅሬታቸውንና ምሥጋናቸውን የገለጹት ከሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱን ሒደት ሲያይ የነበረው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት፣ ሰኞ ጳጉሜን 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በምርመራ መዝገቡ ላይ የተለያዩ ትዕዛዞችን ሰጥቶ ሲዘጋ በሰጡት … [Read more...] about “ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” ሊባሉ ነው
በጽንፈኞች ጉዳት ለደረሰባቸው 40 ሚሊዮን ድጋፍ ተደረገላቸው
የኦሮሚኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ የነበረው ሃጫሉ ሁንዴሣ በግፍ በተገደለ ጊዜ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የተነሳው ነውጥ የበርካታ ወገኖችን ሕይወት ቀጥፏል፤ ንብረት አውድሟል፤ አካለ ሥንኩል አድርጓል፤ ይህ ነው የማይባል የስነልቦና ችግር ፈጥሯል። አክራሪና ጽንፈኛ የሆኑ በደመ ነፍስ የሚመሩ ለፈጸሙት ግፍ መጠገኛ የሚሆን የተለያየ ድጋፍ ለተጎጂዎች ሲከፋፈል ቆይቷል። ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በኦሮሚያ ክልል በጽንፈኞች ንብረታቸው ለወደመባቸው፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸውና የቤተሰቦቻቸው ሕይወት በግፍ ለተነጠቀባቸው ልጆቿ የአርባ ሚሊዮን (40,000,000) ብር ድጋፍ አድርጋለች። ቤተክርስቲያኒቱ ለተጎጂዎች በየስማቸው የተዘጋጀውን የባንክ ሒሳብ ደብተር ያስረከበችው ዛሬ በጠቅላይ ቤተክህነት በተዘጋጀ ሥነሥርዓት ነው። (@ Dewol) ጎልጉል … [Read more...] about በጽንፈኞች ጉዳት ለደረሰባቸው 40 ሚሊዮን ድጋፍ ተደረገላቸው
ይቅርታና ምህረት አድራጊው ይወገዳል! የተደረገለትም ይሞታል!
መሃል ሰፋሪ አሊያም ገለልተኛ ይመስል የነበረው የኦሮሞ አክቲቪስቶች በሙሉ የጃዋር ግልገል መሆናቸው የምታውቀው፤ ልክ እንደ አይን-አፋር ሴት እየተቅለሰለሱ፣ እንደ ሽምግሌ ምሳሌ እያበዙ ከሄዱ በኋላ በማጠቃለያው ላይ “ጃዋር መሃመድ በይቅርታ ከእስር ቢፈታ ለሀገርና ህዝብ ይጠቅማል!” ሲሉ ነው። በእርግጥ በእስር ላይ ያለ ሰው እንዲፈታ ማሰብ፣ አማላጅ መላክ ወይም Lobby ማድረግ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሀገር ውስጥ የተለመደ ነው። በዚህ ረገድ በሰኔ15ቱ ግድያ ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች መፈታታቸው በተደጋጋሚ እንደ ማሳያ ተጠቅሷል። ነገር ግን በሰኔ 15ቱ ግድያ የተሳተፉ አካላት በስልጣን ሽኩቻና አለመግባባት ምክንያት የተፈጠረ ነው። በዚህ ምክንያት የተጎዱ ሰዎች መኖራቸው እርግጥ ነው። ነገር ግን በአማራ ክልል የሚገኙ አማራዎችን ወይም ሙስሊሞችን ለማጥፋት ታቅዶ የተፈፀመ … [Read more...] about ይቅርታና ምህረት አድራጊው ይወገዳል! የተደረገለትም ይሞታል!
ደጀኔ ጣፋ፥ ከ “ተጠርጣሪ” ወደ “ተከሳሽ”!
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ በሕገ መንግስት እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓት ላይ በሚፈጸም ወንጀል ተከሰሱ። አቶ ደጀኔ ክስ የቀረበባቸው ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 26፤ 2012 ባስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ነው። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በአቶ ደጀኔ እና አቶ መስተዋርድ ተማም በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ባቀረበው ክስ፤ ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ከሚገኙ እና ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን እንደነበር ጠቅሷል። ሁለቱ ተከሳሾች “በኃይል፣ በዛቻ፣ በአድማ ወይም ህገ ወጥ በማናቸውም መንገድ በሕገ መንግስቱ የተቋቋመውን ስርዓት ለማፍረስ በማሰብ ከሰኔ 2012 ዓ.ም. በኋላ መንግስት የስልጣን ዘመኑ የሚጠናቀቅ በመሆኑ መንግስት ሆኖ … [Read more...] about ደጀኔ ጣፋ፥ ከ “ተጠርጣሪ” ወደ “ተከሳሽ”!
ጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ በኦሮሚያ የተፈጸመው ኦርቶዶክሳውያንን የማጽዳት እንቅስቃሴ ነው
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጥያቄዎቿን እንዲቀበላት ጠየቀች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉ ተደጋጋሚ ጥቃቶች እንደሚነገረው “በሽግግር ወቅት የሚያጋጥሙ” ተብለው ብቻ የሚታለፉ ሳይሆኑ፣ የተሳሳቱ ርዕዮተ ዓለማዊ ትርክቶችንና ጂኦ ፖለቲካዊ ዳራዎችን መነሻ በማድረግ በተቀነባበረና በተደራጀ ሥልት የሚፈጸሙ ኦርቶዶክሳውያንን የማፅዳት እንቅስቃሴዎች መሆናቸውን ቤተ ክህነት ገለጸች። የኦሮምኛ ቋንቋ ድምፃዊው ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ምክንያት በማድረግ በኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች በስድስት ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ 25 ወረዳዎች በሚኖሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የገለጸችው ቤተ ክህነት፣ በጥቅምት ወርና በጥር ወር ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ እንዲሁም በሃጫሉ ሞት ምክንያት በአቢያተ ክርስቲያናትና … [Read more...] about ጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ በኦሮሚያ የተፈጸመው ኦርቶዶክሳውያንን የማጽዳት እንቅስቃሴ ነው
እነ ጃዋር መሐመድና ተቋማቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ፈጽመናል አልፈጸሙም” በሚል ተካካዱ
“በግል ሐኪሜ ካልሆነ አልታከምም ማለታቸው እንድንጠራጠር አድርጎናል” ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ “አዕምሮዬን ብስት እንኳን በማላውቀው ሐኪም መነካት አልፈልግም” ተጠርጣሪ አቶ ጃዋር መሐመድ “ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ የሚሰጠው ትዕዛዝ እየተከበረ አይደለም” ተጠርጣሪዎች “መርህ አክብረን ሁሉንም ነገር በአግባቡ እየፈጸምን ነው” የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በተጠረጠሩበት የአመፅ ጥሪ ማድረግ፣ የሰው ሕይወት ማጥፋት፣ የእርስ በርስ ግጭት መፍጠር፣ የንብረት ውድመትና ሌሎችም የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኘው እነ አቶ ጃዋር መሐመድና ሁለቱ የመንግሥት ተቋማት (ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ፌዴራል ፖሊስ) የፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ፈጽመናልና አልፈጸሙም” በሚል ተካካዱ። ሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች “ፈጽሜያለሁና አልፈጸሙም” በሚል … [Read more...] about እነ ጃዋር መሐመድና ተቋማቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ፈጽመናል አልፈጸሙም” በሚል ተካካዱ








