
የኦሮሚኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ የነበረው ሃጫሉ ሁንዴሣ በግፍ በተገደለ ጊዜ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የተነሳው ነውጥ የበርካታ ወገኖችን ሕይወት ቀጥፏል፤ ንብረት አውድሟል፤ አካለ ሥንኩል አድርጓል፤ ይህ ነው የማይባል የስነልቦና ችግር ፈጥሯል።
አክራሪና ጽንፈኛ የሆኑ በደመ ነፍስ የሚመሩ ለፈጸሙት ግፍ መጠገኛ የሚሆን የተለያየ ድጋፍ ለተጎጂዎች ሲከፋፈል ቆይቷል።
ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በኦሮሚያ ክልል በጽንፈኞች ንብረታቸው ለወደመባቸው፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸውና የቤተሰቦቻቸው ሕይወት በግፍ ለተነጠቀባቸው ልጆቿ የአርባ ሚሊዮን (40,000,000) ብር ድጋፍ አድርጋለች።
ቤተክርስቲያኒቱ ለተጎጂዎች በየስማቸው የተዘጋጀውን የባንክ ሒሳብ ደብተር ያስረከበችው ዛሬ በጠቅላይ ቤተክህነት በተዘጋጀ ሥነሥርዓት ነው። (@ Dewol)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
It is about time the church stepped up its assisstance. The church collects and brings in tons of money from the believers and building rentals. Majority of these properties are in Oromia.
Mr Baba yes the church has property all over the worled not only in Oromia region the main thing is she gives in difference for those eho are in need you better read about Orthodox Church before you comment Orthodox Church is beyond your hate imajination. your ambition to claim wat you didnt deserve will cost you better you work and be prosper instead of seating and dreaming wat belongs to others.