• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እነ እስክንድር፥ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት

September 13, 2020 08:10 am by Editor Leave a Comment

እነ አቶ እስክንድር ነጋ የአስተዳደሩን ሥልጣን በኃይል ለመያዝና ለሽብር ወንጀል መሰናዳት ወንጀሎች ተከሰሱ

ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ውለው የቆዩት እነ አቶ እስክንድር ነጋ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀና ለ)፣ 35፣ 38፣ 240(1ለ) እና የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 6(2) ድንጋጌዎችን በመተላለፍ መንግሥትን ሰላም በመንሳትና እንዳይረጋጋ በማድረግ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥልጣንን ኃይልና አመፅ ተጠቅመው ለመያዝ በመንቀሳቀስና ለሽብር ወንጀል በመሰናዳት ወንጀሎች ክስ ተመሠረተባቸው።

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጳጉሜን 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕገ መንግሥትና የሽብር ወንጀሎች አንደኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት፤

  • በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋ፣
  • የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣
  • የፓርቲው አመራር ወ/ሮ ቀለብ ሥዩም፣
  • አስካለ ደምሌ ደሳለኝ፣
  • ጌትነት በቀለ፣
  • አሸናፊ አወቀና
  • ፍታዊ ገብረ መድኅን ላይ ክሱን አቅርቧል።

በተለይ አቶ እስክንድር፣ አቶ ስንታየሁ፣ ወ/ሮ ቀለብ፣ አስካለና ጌትነት የተባሉት ለተከሳሾች፤

  • ብሔርንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ የእርስ በርስ ጦርነት ለማነሳሳት፣
  • መንግሥት በማዳከም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ሥልጣንን ለመያዝ መሥራት የጀመሩት በነሐሴ ወር 2011 ዓ.ም. ጀምሮ መሆኑን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል።

በወቅቱ ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው “የአዲስ አበባ ባላደራ” በሚል ስያሜ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና የተለያዩ እምነት ተከታዮች የሚኖሩበትን አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪን እንወክላለን በማለት ሲንቀሳቀሱ ቆይተው፣ ሕገወጥ የነበረውን ድርጅት “ባልደራስ” በሚል የፖለቲካ ፓርቲ አቋቁመው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ ዕውቅና ማግኘታቸውንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሷል።

ፓርቲው ሕጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መንቀሳቀስና ዓላማውን ማራመድ ሲገባው፣

  • በተቃራኒው በፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ውስጥ “የኦሮሞና ትግራይ ተወላጆች እንዳይካተቱ፣
  • የእስልምና እምነት ተከታዮች በተቻለ መጠን እንዳይኖሩ ወይም የእስልምና እምነት ተከታዮች ከተካተቱም ተፅዕኖ መፍጠር የማይችሉ መሆን እንዳለባቸው በመወሰን፣
  • ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ያገለለ እንዳይመስል ፓርቲው በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች ላይ የሚሳተፉ ሙስሊሞችን ፎቶ ጎላ አድርገው በማንሳት በማኅበራዊ ሚዲያ ያሠራጩ እንደነበር ገልጿል።

በፖለቲካ ፓርቲ ሽፋን ሕገወጥ በሆነ ድርጊት በመሰማራት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የነበሩት ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ወደ ሥልጣን የመጡት በሕገወጥ መንገድ መሆኑን በመግለጽ፣ ብሔርና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስና የአዲስ አበባ ነዋሪን በማሳመፅ ከሥልጣን ለማስወገድ ይንቀሳቀሱ እንደነበር ዓቃቤ ሕግ አብራርቷል።

ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ ብሔርና እምነት ተኮርት ጉዳዮችን በመምረጥ ግጭት በመቀስቀስ መንግሥትን ሰላም በመንሳትና እንዳይረጋጋ በማድረግ፣ የጥላቻ ዘመቻ በመክፈትና የጥላቻ ዘመቻ የሚካሄድባቸውን የተለያዩ ዘዴዎችን በመንደፍ የፓርቲውን ደጋፊዎችና አባሎቻቸውን ሲያንቀሳቅሱ እንደነበርም ገልጿል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩንና የምክትል ከንቲባውን ስም ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች፣ በትራንስፖርትና በተለያዩ አጋጣሚዎች በአካል ለሚያገኟቸው ሰዎች ጥላቻቸውን በመግለጽና ሐሰተኛ የፌስቡክ ማኅበራዊ ድረ ገጾችና ማናቸውን ዓይነት የመገናኛ ዘዴዎች ተጠቅመው ስም በማጥፋት ጥላቻን ያሰርፁ እንደነበርም ዓቃቤ ሕግ ገልጿል።

ሕገወጥ ግንባታዎች በአስተዳደሩ እንዲፈርሱ ሲደረጉ “አስተዳደሩ ቅርስ አፈረሰ፣ ዜጎችን አፈናቀለ” በማለት ፎቶ በማንሳትና ቪዲዮ በመቅረፅ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲያሠራጩ እንደነበርና የኦሮሞና የአማራ ብሔር ተቆርቋሪ መስለው አንዱ ብሔር የሌላውን ብሔር እንዲዘልፍ፣ የኦርቶዶክስና የእስልምና ሃይማኖቶችን መሠረት ያደረጉ ግጭት የሚቀሰቅሱ መልዕክቶች እንዲሠራጩ ማድረጋቸውንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል።

ተከሳሾቹ መንግሥትን ለመጣል የተገኘውን አጋጣሚ ሁሉ እንደሚጠቀሙ በመግለጽ፣ መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም. መንግሥትን በኃይል ለመጣል የሚችሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉና ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከመስከረም 30 ቀን በኋላ በከተማ አስተዳደሩ የሚቆየው “በእኛ እሬሳ ላይ ተረማምዶ ነው” በማለት፣ ማንኛውንም መስዕዋትነት ለመክፈል ደጋፊዎቻቸውና የፓርቲው አባላት እንዲዘጋጁ ሲቀሰቅሱ እንደነበር ዓቃቤ ሕግ አብራርቷል።

ተከሳሾቹ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ በቦሌ፣ በአራዳ፣ በጉለሌና በየካ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የእርስ በርስ ግጭት ለማስነሳት ሲንቀሳቀሱ እንደነበር፣ “መንግሥት ከሃይማኖት ላይ እጁን ያንሳ” የሚልና ሌሎች አንዱን ብሔር ከሌላኛው ብሔር ጋር የሚያጋጩ አፀያፊ ስድቦችን የያዙ መፈክሮችን በማራገብ፣ ሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ በማድረግ የጥላቻ ንግግር ሲዘሩ እንደነበር ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል።

ተከሳሾቹ የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም በተለያዩ ክፍላተ ከተማ ለሚገኙ አባሎቻቸው “ቄሮዎች ለሐዘን ወደ አዲስ አበባ ስለሚመጡ፣ የተደራጀውን ኃይል በመጠቀምና ለሁለት በመክፈል ቀጥቅጣችሁ እንዲመለሱ አድርጉ” የሚል ተልዕኮ መስጠታቸውንም ዓቃቤ ሕግ በዝርዝር ጠቁሟል።

ተከሳሾቹ የኦሮሞና የትግራይ ተወላጆች መኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ መደብሮችና ሕንፃዎች ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድ መንቀሳቀሳቸውንም አክሏል። ተልዕኮ ለተሰጣቸው 1,500 ብር አበል በመክፈል ሰኔ 23 እና 24 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተከስቶ የነበረውን የእርስ በርስ ግጭት መምራታቸውንም በክሱ ዘርዝሯል።

በአጠቃላይ ተከሳሾቹ ማናቸውንም አጋጣሚ በመጠቀም ሃይማኖትና ብሔርን መሠረት ያደረገ ግጭት በማስነሳት የድምፃዊ ሃጫሉ ግድያን እንደ አጋጣሚ በመጠቀምና ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት፣ በተለይ ሰኔ 23 እና 24 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደ አጋጣሚ በመጠቀም በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች እንዲፈጠር ባደረጉት የእርስ በርስ ግጭት የ14 ሰዎች ሕይወት እንደጠፋና 187,258,459 ብር ንብረት እንዲወድም በማድረጋቸው፣ አንዱ ወገን በሌላኛው ወገን ላይ የጦር መሣሪያ እንዲያነሳና በመንግሥት ላይ የማሳነሳሳት ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።

በሌላ በኩል ፓርቲውን እንደ ሽፋን በመጠቀም አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ መስጊዶችንና አቢያተ ክርስቲያናትን የሚያቃጥል፣ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) እና ሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናትንና የፖለቲካ አመራሮችን በግድያ የሚያስወግድ ገዳይ የሽብር ቡድን መመልመላቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል።

የሽብር ቡድኑ የተመለመለው ከአዲስ አበባና ከአማራ ክልል መሆኑንና ባልደራስ ሥልጣን ሲይዝ ቦታ እንደሚሰጣቸው ቃል በመግባት ወደ ክልል ተልከው ምልመላ እንዲፈጽሙ ተሰማርተው እንደነበር ዓቃቤ ሕግ በዝርዝር አስረድቷል። ተከሳሾቹ ሥልጣን በኃይል ለመያዝ የሽብር ቡድን በመምራት በማሠልጠንና ለመሠልጠን ሲንቀሳቀሱ እንደነበር በመግለጽ፣ የሽብር ወንጀል ለመፈጸም የመሰናዳት ወንጀል ክስ መሥርቶባቸዋል።

ተከሳሾቹ የክስ ቻርጁ ደርሷቸው መቃወሚያና የመብት ጥያቄ ማንሳት የሚፈልጉ ስለመሆናቸው ፍርድ ቤቱ ጠይቋቸው የተጠቀሱባቸው ክሶች እነሱን እንደማይመለከቱ፣ የታሰሩበትና የተከሰሱት የፖለቲካ ልዩነት ስላላቸው መሆኑን ተናግረው በሌሉባቸው የወንጀል ተሳትፎ ከመከሰሳቸው አንፃር ዳኞች በሕጉና በኅሊናቸው ብቻ ገለልተኛ ሆነው እንዲዳኟቸው ጠይቀዋል። ከጠበቆቻቸው ጋር በመመካር በክሱ ላይ ምላሽ እንደሚሰጡ ተናግረው ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም ምላሻቸውንና የሚያቀርቡትን የመብት ጥያቄ ለመስማት ለመስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል።

(ታምሩ ጽጌ፤ ሪፖርተር)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Law, Left Column Tagged With: chilot, eskinder, jawar massacre, ችሎት

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule