አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የ14 ተጠርጣሪ ጠበቆች ለቅድመ ምርመራ የተሰየመው ዳኛ ገለልተኛ ሆኖ ጉዳያችንን ሊመለከትልን ስለማይችል ይነሣልን ሲሉ ማመልከታቸው ተገለጸ።
አሥራ አንዱም የተጠርጣሪ ጠበቆች በሰባት ገጽ ባቀረቡት አቤቱታቸው ሕግ ጠቅሰው ዳኛው ገለልተኛ ሆኖ ጉዳያችንን መመልከት አይችልም በማለት ነው ያመለከቱት።
የምርመራ መዝገቡን ሲመለከቱ የቆዩት የዕለቱ ዳኛ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ 25/88 አንቀጽን በመጥቀስ የቀረበው አቤቱታ ተጨባጭነት የሌለው፣ በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ ልነሣ አይገባም በማለት ወስነዋል።
ይሁን እንጂ በአዋጁ መሠረት መዝገቡ በሬጅስትራር በኩል ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ በተመሳሳይ ሌላ ዳኛ አይቶ ውሳኔ እስኪሰጥበት እና መጥሪያ እስከሚደርሳቸው ድረስ ተጠርጣሪዎቹ ባሉበት በፖሊስ ማረፊያ እንዲቆዩ የፌዴራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ትእዛዝ ሰጥቷል።
በዚህ መሠረት ለዛሬ ዐቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎች ላይ በቅድመ ምርመራ ችሎት ሊያሰማው የነበረው የምስክሮች ማሰማት ሒደት ሳይካሔድ ቀርቷል። (ምንጭ፤ ኢብኮ)
Leave a Reply