አሸባሪው ህወሓት ሀገርን የሚያፈርስበትና የኢትዮጵያን ህዝብ በመበቀል ለመከራ የሚዳርግበት አዲስ ሰነድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር ገብቷል። አሁን እያካሄደ ያለው ውጊያም የዚሁ አካል ነው። ፅሁፉ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ በማሳጠርና መታየት ያለባቸው ነጥቦች ብቻ ቀርቧል። ከሰነዱ የተወሰዱ ዋና ወና ሃሳቦች: ስለ ሰላም አማራጮች ያላቸው አቋም:- • የሰላም አማራጭ በሚል ስትራቴጂው፣ በአንድ በኩል ጊዜ ወስዶ ለአጠቃላይ ዘመቻ ለመዘጋጀት በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት ሰላም ፈላጊ አይደለም ብሎ ለዓለም ማህበረሰብ ጥላቻ ለማሰተጋባት እንዲያግዘው በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የጀመረው አካሄድ በፍፁም የማያዋጣና የትግራይ ህዝብን ጥቅም የማያስከብር መሆኑን ያስቀምጣል። • የውስጥ ትግላችን በማገዝ የሚንቀሳቀሱ እንደ ኦነግ የመሳሰሉ አጋሮቻችን እንዲሁም በተለያዬ የዓለም … [Read more...] about የህወሓት የሽብር ሰነድ ሲገለጥ…
Middle Column
WhatAboutism በመረጃ ‘ጦርነት’ ውስጥ
WhatAboutism ስትራቴጂው በሰዎች ባህሪ ውስጥ ብቻ ሳይወሰን በፖለቲካ እሰጣገባዎች ውስጥም የሚተገበር ሆኗል፤ ወቀሳ እና ትችት ሲሰነዘር የወቃሽ መሰል ወንጀል በአፃፋነት ማቅረብ…። Whataboutism እንደ ፖሮፓጋንዳ ስትራቴጂ ቆየት ቢልም በኮቪድ 19 ሰሞን ጡዘት ላይ የደረሰበት ነበር። የኮቪድ መነሻ ቻይና ነች የሚለው የምዕራባዊያን የሚዲያ ዘመቻ ከቻይና በተጨማሪ ሩሲያን ያካተተ ቅንጅታዊ የመልስ ምቶይ እንዲያይሉ ያደረገ ነበር። የቻይና እና ሩሲያ ባለስልጣናት አሜሪካ በቤተ ሙከራ ፈጥራ አሰራጨቻቸው የሚባሉትን የበሽታ ዝርዝሮች ቆየት ያሉ ፋይሎች እየፈለፈሉ ይጠቅሱ ነበር። የራሳቸው የምዕራባዊያን ተቋማት ቀደም ሲል ያወጧቸውን ጥናታዊ ማጋለጫዎች እንደማጠናከሪያ መጠቀማቸው ሞስኮ እና ሩሲያን በ whataboutism ፕሮፖጋንዳው በለስ ሆኖላቸዋል። “Whataboutism” … [Read more...] about WhatAboutism በመረጃ ‘ጦርነት’ ውስጥ
ምኒልክ የድል መንፈስ!
የዛሬዋ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ስበት ማዕከል የሆነው አፄ ምኒልክ ዘመን ተሻጋሪ ውርሶች ለዘመናዊት ኢትዮጵያ ጥሎ አልፏል። ዘመናዊት ኢትዮጵያ ስንል ከጨረቃ የመጣች እያልን ሳይሆን ግዛታዊ ቅርጿ ሲጠብና ሲሰፋ የነበረችው ኢትዮጵያ በአንጻራዊ ዝማኔ መመራት የጀመረችበት አስተዳደራዊ ዘመን መገለጫ ማለታችን ነው። የዛሬዋ ኢትዮጵያ መልከዓ ምድራዊ ቅርጽ ከሞላ ጎደል የአፄው የንግሥና ዘመን ውጤት ናት። ከምንም በላይ የጥቁር ዘር የነጻነት ምልክት የሆነው የአድዋ ድል በምኒልክ መሪነት የመጣ ነው። በርግጥ ድሉ የአባቶቻችን የመደማመጥና የመተባበር ውጤት ነው። ምኒልክን አልባ የአድዋን ድል ማስመዝገብ ይቻል (ይሆን) ነበር ብሎ ማመን ይቻላል። ይሁንና በታሪክ የምናውቀውን የአድዋን ድል ያለ ምኒልክ ማሰብ ክርስትናን ያለክርስቶስ፣ እስልምናን ያለነብዩ መሐመድ እንደማሰብ ያለ ቅዥት ነው። ይህ … [Read more...] about ምኒልክ የድል መንፈስ!
“አውሮፕላኑ ሳይመታ መቀሌ ቢገባ ደስታውን አልችለውም ነበር”
ጌታቸው ረዳ መሳሪያ ጭኖላቸው ሲገባ ስለተመታው አውሮፕላን በቁጭት ሲናገር “አውሮፕላኑ ሳይመታ መቀሌ ቢገባ ደስታውን አልችለውም ነበር፤ ግን መተውታል፣ ዛሬም ነገም ወደፊትም ሊመቱ ይችላሉ” ብሏል። ከሙሉው ንግግሩ ተቀንጭቦ የተወሰደውን ቪዲዮ ይመልከቱ። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about “አውሮፕላኑ ሳይመታ መቀሌ ቢገባ ደስታውን አልችለውም ነበር”
የትህነግ ፍቅር ያከነፈው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከኢትዮጵያ ጀርባ ከአሸባሪው ትህነግ ጋር በመደራደር የራሱን ህግ ጥሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከኢትዮጵያ ጀርባ ከአሸባሪው ትህነግ አመራር ጋር በቀጥታ በመደራደር የራሱን ሕግ መጣሱ ታውቋል። የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባለፈው ሳምንት ከአሸባሪው የህወሓት ቡድን ሊቀመንበር ከሆነው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። ዋና ጸሀፊው ይህንን ከአሸባሪው ድርጅት መሪ ጋር የመነጋገራቸው መረጃ የታወቀውም፤ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስታፌን ዱጃሪች ለተመድ ጉዳይ ዘጋቢ ጋዜጠኞች ጽፈውት ሾልኮ ከወጣው ኢሜይል ነው። የዋና ጸሀፊው ድርጊትን ተከትሎ በርካቶች ጉዳዩን በማንሳት ተገቢነት የጎደለው መሆኑን እየገለጹ ነው። ትህነግ በዓለም አቀፍ የሽብር መረጃ ቋት (Global Terrorism … [Read more...] about የትህነግ ፍቅር ያከነፈው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት
በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበሌ ነዋሪዎች በኦነግ ሸኔ ላይ ጀብዱ ፈፀሙ
ነገሩ እንዲህ ነው። በኦሮሚያ ክልል በሆሩ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጮማን ጉዱሩ ወረዳ ውስጥ ካሉት ቀበሌዎች መካከል በአንዲት ቀበሌ ውስጥ ታላቅ ጀብዱ ተፈፅሟል። ቀበሌዋ ጉደኔ ጫላ ሲበሬ ትባላለች። እንደወትሮው ሁሉ ህዝቡ ውስጥ ለመደበቅ የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ወደዚህች ቀበሌ ዘልቀው ይገባሉ። ነገር ግን የጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበሌ አሁን በቃችሁን በማለት 07 ወጣቶች ከታጠቁት ሸኔ ታጣቂዎች ጋር በጦርና በገጀራ ጦርነት ገጠሙ። ከ7ቱ ሶስቱ የዩኒቨሪሲቲ ተማሪዎች ሲሆኑ አራቱ ደግሞ አርሶ ከደር ናቸው። ጩሃቱን የሰማው የቀበሌው ህዝብ በሙሉ በነቂስ ወጥቶ ከታጠቁት ሸኔዎች ጋር በባህላዊ ጦርና ገጀራ ገጠሙ። ይህንኑ ያላሰቡትን የህዝብ ማዕበልና ቁጣ አይተው የተደናበሩት አሸባሪዎች እግር አውጪኝ ብለው እግራቸው ወደመራቸው አቅጣጫ መሸሽን መረጡ። ነገር ግን የህዝብ ማዕበሉ አንዱን በጦር … [Read more...] about በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበሌ ነዋሪዎች በኦነግ ሸኔ ላይ ጀብዱ ፈፀሙ
በኢትዮጵያ ግብርና ላይ ግብጽ ለዓመታት የፈጸመችው ሤራ
የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ "ኢህአዴግ ጣና በለስን ለምን አፈራረሰው?" በሚል ርዕስ አንድ ዘገባ አቅርበን ነበር። ያንን ተከትሎ ከሦስት ዓመት በኋላ አምባ – የአማራ ባለሙያዎች ህብረት የጣና በለስ ታሪካዊ የልማት ፕሮጀክት፤ ከመፈራረስና ውድመት እስከ መሸጥ በሚል ርዕስ ሌላ ዘለግ ያለ ዘገባ ለንባብ አብቅቷል። በአገራችን ያለው እና በዘመነ ት ህነግ ተስፋፍቶ መንግሥታዊ ቅርጽ የያዘው የዘር ፖለቲካና ምክን ያቱ አገራችን በነጻነት ራሷል እና ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ ለጥቁር ሕዝብ ኩራት ሆና የኖረችውን ያህል በኢኮኖሚውም መስክ ተመሳሳይ ፈር ቀዳጅ ድል እንዳትቀዳጅ ለማኮላሸት ነው። ከራሳችን በላይ ማንነታችንን እና እሴታችንን የሚያውቁት ጠላቶቻችን በቆፈሩልን ጉድጓድ ስንነጉድ ዓመታት አሳልፈናል። እስሌማን የዓባይ ልጅ በተለይ ከግብርና ጋር በተያያዘ ለዓመታት ሲፈጸምብን … [Read more...] about በኢትዮጵያ ግብርና ላይ ግብጽ ለዓመታት የፈጸመችው ሤራ
ገቢ የማያስገኙ የዜና ርዕሶች
የማኅበራዊ ሚዲያ ሰለባዎች ዓይነታቸው ብዙ ነው። ልጆቻቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ተግዳሮቶችን (ቻሌንጅ) በመውሰድ እልህ ውስጥ ገብተው የሞቱባቸው ጥቂቶች አይደሉም። “Blackout Challenge” የተሰኘው የቲክቶክ ተግዳሮት ፉክክር ውስጥ የገቡ ሕጻናትና ወጣቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሌሎች ጥቂት የማይባሉ ደግሞ የማኅበራዊ ሚዲያ ሱሰኛ ሆነው ሕይወታቸው የተበላሸ አሉ። የተጎጂው ቁጥር ሥፍር የለውም፤ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮቹን የሚከስሱ ወላጆች ቁጥርም እንዲሁ እጅግ በርካታዎች ናቸው። በማኅበራዊ ሚዲያ ዘገባ ምክንያት ሕይወታቸውን ከሚያጡት በተጓዳኝ አገራቸውንም እያጡ ያሉ ጥቂቶች አይደሉም። የዛሬ ስድስት ዓመት በቱርክ የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ሤራ የማክሸፍ ሥራ ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ ትልቅ አስተዋጽዖ አለው። አገር ወዳድ ቱርካውያን የወሬ ሰለባ አንሆንም ብለው አገራቸውን … [Read more...] about ገቢ የማያስገኙ የዜና ርዕሶች
የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እንዲያወግዙት አብን ጠየቀ
"የዘር ማጥፋት" ወንጀሎች የሚመረምር ልዩ አቃቤ ህግ እንዲቋቋም ጠየቀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅና የፌደራል የጸጥታ ኃይል እንዲሰማራም ጠይቋል ጥቃቱን "ዘር ማጥፋት ብሎታል። የአብን ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና የንቅናቄው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጣሂር መሐመድ ፤ በአማራ ተወላጆች ላይ በተፈጸመው “የዘር ማጥፋት” ዙሪያ ዛሬ በአዲስ አበባ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ አብን፤ በኦሮሚያ ክልል በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈፀሙ “የዘር ማጥፋት” ወንጀሎች የሚመረምር ልዩ አቃቤ ህግ በአዋጅ እንዲቋቋም ጠይቋል፡፡ ይህንን ተከትሎም የወንጀል ፈፃሚዎች በግልፅ ችሎት መዳኘት እንዳለባቸው ንቅናቄው ጠይቋል፡፡ የፓርቲው ሊቀ መንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ፤ በአማራ ሕዝብ ላይ ባለፉት ዓመታት የተሰራው የተሳሳተ ትርክት አሁን ለሚካሄደው “የዘር ማጥፋት ወንጀል” … [Read more...] about የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እንዲያወግዙት አብን ጠየቀ
“አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ
በወለጋ የንፁሃንን ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ያለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም ተናገሩ። አክለውም የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ጠ/ሚ አብይ አህመድን በይፋ በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭታቸው ጠይቀዋል። ከ 2 ቀናት በፊትም ጠባቂያቸው መገደሉን ተናግረዋል። አቶ ሀንጋሳ ትላንት ሁለት ሰዓት በፈጀውና ከ15 ሺህ በላይ ተመልካቾች በተከታተሉት የፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት በኦሮምኛ (የተወሰኑ ቁልፍ ነገሮችን ደግሞ በአማርኛ) አስተላልፈዋል፡፡ የሚከተሉት ዋነኛ ነጥቦች ነበሩ: አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና እቅድና ተግባር ነው፣ አብዲ ኢሌ ሲነሳ ሶማሊያ ሰላም እንደሆነው ሁሉ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ በክልሉ ያሉ ባለስልጣናትን እስር … [Read more...] about “አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ