አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ዕርዳታ ለመከልከል እያሰበች ነው በአባይ ግድብ ጉዳይ ከጅምሩ ለግብፅ ወገንተኛ መሆኗን ስታሳይ የነበረችው አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የዕርዳታ ዕቀባ ለማድረግ እያሰበች መሆኑን ፎሪይን ፖሊሲ (Foreign Policy) ዛሬ (ረቡዕ) ባወጣው ዘገባ ገለጸ። ይህ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አቋም በአስተዳደራቸው ውስጥ ክፍፍል መፍጠሩ አብሮ ተዘግቧል። አባይን በተመለከተ “ማድረግ የምችለውን መንገድ ሁሉ እጠቀማለሁ” በማለት ስትናገር የነበረችው ግብፅ የፕሬዚዳንት ትራምፕን እጅ በመጠምዘዝ በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በርትታ እየሠራች ነው። ግብፅና አሜሪካ ለዘመናት የቆየ የጥቅም ተጋሪዎች ናቸው። እኤአ ከ1980ዓም ጀምሮ አሜሪካ ለግብፅ $40 ቢሊዮን ዶላር የሚሊታሪና $30 ቢሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ ዕርዳታ ማድረጓን የስቴት ዲፓርትመንት መረጃ … [Read more...] about የትራምፕ ለግብፅ መወገን የውስጥ ክፍፍል ፈጥሯል
Middle Column
ኦኤምኤን ሕጋዊ ክስ ተከፈተበት፤ ለጊዜውም ሊታገድ ይችላል
በአሜሪካ አገር በትርፍ አልባ ድርጅትነት የተቋቋመውና ለበርካታዎች ሕይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ተጠያቂ ነው የሚባለው ኦኤምኤን (የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ) ክስ ተመሥርቶበታል። ከሚዲያው ጋር ታደለ ኪታባ (የሚዲያው ሹም እንደመሆኑ)፤ እንዲሁም አያንቱ በከቾ በግል የክስ ተመሥርቶባቸዋል። ክሱን ያቀረቡት ጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅ እንደሚሉት ይህ ፋይል የማስከፈት ዓይነት ተግባር ነው እንጂ በትክክል በዐቃቤ ሕግ ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ ክስ አልተመሠረተባቸውም። የጉዳዩ ባቤት የሆኑት አቶ ጥበበ ሳሙኤል እንዲህ ይላሉ፤ ከበርካታ ሰዎች እና የሚድያ አውታሮች፤ 'OMN and its employees are Charged in District Court የሚል የዜና ዘገባ እየተራገበ መሆኑ እና እንዳብራራ ጥያቄ እየተጠየቅኩ ነው። በአጭሩ ለማብራራት "they are sued not … [Read more...] about ኦኤምኤን ሕጋዊ ክስ ተከፈተበት፤ ለጊዜውም ሊታገድ ይችላል
የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ከOMN እንዲነጠል ደጋፊዎች አሳሰቡ፤ መዋጮ ሊያቆሙ ነው
“ቴክኖሎጂ የአማራ አክቲቪስቶችን ማንነት አጋለጠ” በዋናነት ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግ) በሚል የተገንጣይ ወንበዴ ስም በሚጠራው ቡድን፣ አፍቃሪ ትህነግ በሆኑ በውጭ አገር የሚኖሩ ደጋፊዎቹና የትህነግን የሥውር ንግድ በሚያከናውኑ ኃይሎች የሚደጎመው የትግራይ ሚዲያ ሃውስ (TMH) አሁን በሕግ ጥላ ሥር በሆነው ጃዋር መሀመድ ከሚመራው ኦኤምኤን ሚዲያ እንዲለይ ተጠየቀ። ይህ ካልሆነ ድጋፍ ማድረግ ይቆማል። ይህ የተሰማው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ የተሰኘውና ጃዋር መሀመድ በሂደት የግሉ ንብረት ያደረገው ሚዲያ የሚያሰራጫቸውን ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ዘገባዎች የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ቃለ በቃል እየተረጎመ በማቅረብ መቀስቀሱ አደጋ እንደሚያስከትል ከታወቀ በኋላ ነው። የድምጻዊ ሃጫሉን ግድያ ተከትሎ በቅንጅት በተፈጸመ ጥቃት በኦሮሚያ ከፍተኛ ጉዳት መደረሱና … [Read more...] about የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ከOMN እንዲነጠል ደጋፊዎች አሳሰቡ፤ መዋጮ ሊያቆሙ ነው
የሃጫሉ ተኳሽ፣ አስተኳሾችና የአስከሬን ድራማ ጸሐፊ ተውኔቶች የግፍ ሥራ
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ጸጋ ቅዳሜ ሐምሌ 5፤ 2012 ከፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጋር በሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ የሃጫሉ ሁንዴሣ ግድያን አስመልክቶ የተቀናበረውን ድራማ አስረድተዋል። የድራማውን ጸሐፍትና የድራማ ትወናቸውንም በዝርዝር ተናግረዋል። ቃታ ሳቢው ጥላሁን (ተኳሽ) “የአርቲስቱ ግድያ ግብ ነበረው” ያሉት አቶ ፍቃዱ ጸጋ “አርቲስቱ የግድያ ዛቻ ይደርስበት እንደነበር ለጓደኞቹ ተናግሯል” ብለዋል። ወደ ግድያው አፈጻጸም ዝርዝር ትንታኔ በመግባትም ገዳዩ ጥላሁን ያሚ በሚኖርበት የገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ ሁለት የማያቃቸው ሰዎች ስሙን ጠርተው እንዳናገሩት ራሱ በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል አስረድቷል። ይህንን የእምነት ክህደት ቃል የሰጠውም ሕገመንግሥታዊና የወንጀል ሕግ በሚፈቅደው መሠረት መብትና ግዴታው … [Read more...] about የሃጫሉ ተኳሽ፣ አስተኳሾችና የአስከሬን ድራማ ጸሐፊ ተውኔቶች የግፍ ሥራ
ህወሓት ይፍረስ፤ ዕልቂት ሰባኪዎች ለፍርድ ይቅረቡ!
“ሃጫሉን የገደሉት ነፍጠኞች ናቸው፤ መላው የኦሮሞ ህዝብ የምኒሊክን ሃውልት አፍርሰህ ወደ ቤተመንግሥት ገስግስ!” ይህንን የዘር ዕልቂት የተናገረው የዶ/ር ዐቢይ የለውጥ ቡድን እነ ጃዋር መሃመድን በቁጥጥር ሥር ከማዋሉ በፊት በሕወሃት የደም ገንዘብ የሚቀለበው ሕዝቅኤል ጋቢሣ አሜሪካ ቁጭ ብሎ ሕወሃት ባደራጀው ዲጂታል ሚድያ በመጠቀም ሲያውጅ ነበር። “በደረሰን መረጃ መሠረት፤ የሃጫሉ ሁንዴሳ ገዳዮች ነፍጠኞ ሳይሆኑ ሥልጠናና ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የመጡ ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያን ናቸው፤ እኔ በደንብ አውቃለሁ እነማን እንደገደሉት፤ ምን ዓይነት ሚሊተሪ ፐርሶኔል እንደተሳተፈም አውቃለሁ፤ ኢትዮጵያውያን እንኳን አይደሉም፤ ኤርትራውያን ናቸው" ይህን የተናገረው ደግሞ በጎጥ አስተሳሰብ እጅግ የጠበበው መርዘኛው ፀጋዬ አራርሳ ነው። ፀጋዬ አራርሣ፤ ሃገር መምራት የማይችል ደካማ ነው፤ … [Read more...] about ህወሓት ይፍረስ፤ ዕልቂት ሰባኪዎች ለፍርድ ይቅረቡ!
የስብሃት ነጋ ወንድም በሌብነት ተያዘ
አቤሴሎም ነጋ የተባለውና ነዋሪነቱ በአውስትራሊያ የሆነው ስብሃት ነጋ ወንድም 4 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር (2.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር) በማጭበርበርና በመስረቅ መከሰሱን Herald Sun ዘገበ። እኤአ ከ2008 – 2019 ባሉት ዓመታት የ54 ዓመቱ አቤሴሎም ነጋ የተለያዩ የፋይናንስ ወንጀሎችን በመፈጸም ነው 4.2 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ወደ ግል የባንክ ሒሳቡና iEmpower በሚል ለሚመራው የግል ድርጅቱ ሒሳብ እንዲገባ ያደረገው። ወንጀሉ ስርቆት ብቻ ሳይሆን በኑሯቸው ዝቅተኛ ለሆኑ የሚሰጠውን (የዌልፌር) ገንዘብን አጭበርብሮ መውሰድም የሚጨምር ነው። አቤሴሎም ከዘረፈው ገንዘብ ውስጥ $25,300 የሚሆነውን ያጭበረበረው ከሕግ ጋር ችግር ያለባቸውን የአፍሪካ ወጣቶችን ለመርዳት ከተቋቋመ ድርጅት በመስረቅ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አቤሴሎም የቪክቶሪያ … [Read more...] about የስብሃት ነጋ ወንድም በሌብነት ተያዘ
ሕግን በሕግ እናስከብራለን!!
ጃዋር በአዲሱ “ዓለም” ሆኖ ከፍርድ ሒደት ይልቅ ሽምግልናን ጠየቀ
ሐሙስ ዕለት በተለያዩ ወንጀሎች ተከስሶ ፍርድ ቤት የቀረበው ጃዋር የባህላዊ ሽምግልና እና ዕርቅ ከመደበኛው ፍርድ ቤት በፊት እንዲሞከር ጥያቄ አቀረበ። እጅግ መረን ከለቀቀና ከተደንደላቀቀ የቅምጥል ኑሮው ወጥቶ ወደ አዲስ “ዓለም” የገባው ጃዋር መሐመድ ያቀረበውን ጥያቄና ተማጽንዖ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ አድርጎ ክሱ እንዲቀጥል ቀጠሮ ሰጥቶ አሰናብቶታል። ጃዋር በሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የሚያስጠረጥረውን በርካታ መረጃዎች ተከትሎ፤ በኔትወርክ ሊያደርግ ያሰበው የመንግሥት ለውጥ በመክሸፉ፤ በተለይም በአስከሬን ባለቤትነት የተፈጠረው ግብግብ ከፍተኛ ተቃውሞ ስላስነሳበት የሽምግልና አካሄድ እንደሚያዋጣው በመረዳት ጥያቄውን ሐሙስ ለዋለው ችሎት ማቅረቡን በቅርብ ሂደቱን የሚከታተሉ ለጎልጉል ተናግረዋል። ጎልጉል ቀደም ሲል የሽምግልና ሃሳብ እንዳይጨናገፍ በማለት ያላተመውን … [Read more...] about ጃዋር በአዲሱ “ዓለም” ሆኖ ከፍርድ ሒደት ይልቅ ሽምግልናን ጠየቀ
ሃጫሉ አምቦ እንዲቀበር የቤተሰብ ፍላጎት ነው – ሃብታሙ ሁንዴሳ
ዛሬ [ረቡዕ] በአምቦ ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ እና የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከሚፈጸምበት ቦታ ጋር ተያይዞ በተከሰቱ ግጭቶች የሟቹን ድምጻዊ አጎትን ጨምሮ 5 ሰዎች መገደላቸውን ከቤተሰብ፣ ከከተማው ነዋሪዎች እና ከሆስፒታል ምንጮች ቢቢሲ አረጋግጧል። ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም ከ10 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውም ተነግሯል። የሃጫሉ ታናሽ ወንድም የሆነው ሃብታሙ ሁንዴሳ ለቢቢሲ ሲናገር “አጎታችን ተገድሏል። በእድሜ ትልቅ ሰው ነው። ያሳደገን ነው። የአባታችን ወንድም ነበር” ብሏል። ከሟቾቹ መካከል የአንዱ የሃጫሉ አጎት መሆናቸውን የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ከሃጫሉ አጎት በተጨማሪ ሶስት የቤተሰብ አባላት በጥይት ተመተው የተለያየ ጉዳት እንደደረሰባቸው ሃብታሙ ሁንዴሳ ለቢቢሲ ተናግሯል። “የአጎታችን ሚስት እግሯን ተመታለች፣ … [Read more...] about ሃጫሉ አምቦ እንዲቀበር የቤተሰብ ፍላጎት ነው – ሃብታሙ ሁንዴሳ
ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት
(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን) ዛሬ ላይ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች በስፋት አየተዘገበ ስላለው የኮሮና መድሀኒት ተገኘ የተባለው ዴክሳሜታሶን መድሀኒት አዲስ የተገኘ ሳይሆን ከዚህ በፊት እኛም ሀገር ላይ በስፋት ስንጠቀምበት የነበረ መድሀኒት ነዉ። ዴክሳሜታሶን (Dexamethasone) የሚባለው ስቴሮይድስ (Steroids) ከሚባለው ቤተሰብ የሚመደብ የመድኃኒት ዓይነት እ.ኤ.አ ከ1960 ጀምሮ ለተለያዩ በሽታዎች ጥቅም ላይ ሲዉል የቆየ ነው። ዛሬ ቢቢሲ ላይ የተዘገበዉ መድሀኒት የመተንፈስ ችግር እና በጽኑ የኮሮና ቫይረስ ሕመም ላይ ያሉ ሰዎችን እንጂ መጠነኛ (Mild Symptoms) ምልክት ላላቸው እንደማይጠቅም በጥናቱ ላይ አስፍረዋል። በተጨማሪ ስቴሮይድስ (Steroids) ' በከፍተኛ ጥንቃቄ' የሚሰጡ መድኃኒቶች ሲሆኑ በርካታ 'የጎንዮሽ ጉዳት' እንዳላቸው … [Read more...] about ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት