• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ

March 15, 2023 04:44 pm by Editor Leave a Comment

ከኬንያ ላሙ ወደብ በመነሳት በደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚደርሰውን የምስራቅ አፍሪካ የትራንስፖርት ኮሪደር ለመተግበር ደቡብ ሱዳን ስትራቴጂክ ፕላን ማዘጋጀቷ ተሰምቷል፡፡

ከኬንያ ላሙ ወደብ በመነሳት በደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚደርሰውን የምስራቅ አፍሪካ የትራንስፖርት ኮሪደር ለመተግበር ደቡብ ሱዳን ስትራቴጂክ ፕላን ማዘጋጀቷ ተሰምቷል፡፡ እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ መጻኢ ዕድል አነጋጋሪ እያደረገው ነው፡፡

ደቡብ ሱዳን ቅድማያ ከምትሰጣቸው 16 ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ እንደሆነ የተነገረው ከሪደሩ፣ ምስራቅ አፍሪካን ከከምዕራብ አፍሪካ የሚያገናኝ ነው፡፡ የዚህ ኮሪደር አካል የሆነው ከላሙ ወደብ እስከ ኢሲሎ ያለው 500 ኪሎ ሜትር የሚረዝም መንገድ እየተገነባ ሲሆን፣ ከኢሲሎ በሞያሌ ሀዋሳ የሚደርስ 500 ኪሎ ሜትር የሚደርስ መንገድ ግንባታው ተጠናቅቋል፡፡

ደቡብ ሱዳን ቅድሚያ የምትስጣቸውን 16 ፕሮጀክቶች አስመልክቶ ከአገሪቱ ሚንስትሮች ጋር እንደተወያዩ ያስታወቁት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የአፍሪካ ንግድ ማዕከል ዋና አማካሪ አዲይንካ አዲዬሚ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአገሪቱ ድጋፍ እንደሚደርግ አስታውቀዋል፡፡

ይሁንና የሚገነባው መንገድ ምን ያህል ርዝመት እንዳለውና ስለተመደበለት በጀት የተባለ ነገር የለም፡፡

ኹሉም ፕሮጀክቶች የኮሪደሩን እንቅስቃሴ የሚያሳልጡ ናቸው ያሉት አማካሪው፣ ዓለም ባንከ በተለይም በመንገድ፣ ኃይልና ግብርና ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱን ተናግረዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ሀዋሳ ድረስ እየተገነባ ያለው የፍጥነት መንገድ የትራንስፖርት ኮሪደሩን ውጤታማነት ከፍ ያደርጋል የተባለ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ኬንያና ደቡብ ሱዳን የሚዘረጉ መሰረተ ልማቶች ከኬንያው ላሙ ወደብ በመነሳት ምስራቅ አፍካን ከምዕራብ አፍሪካ በየብስ ያገናኛሉ፡፡ (አዲስ ማለዳ)

TEU Twenty-foot Equivalent Unit ማለት የመርከብ ጭነት ወይም ካርጎ ኮንቴይነር መለኪያ ሲሆን አንድ TEU ማለት ሃያ ኮንቴይነር ነው። በግራፉ ላይ እንደሚታየው የላሙ ወደብ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በወደቡ በኩል የሚተላለፈው ጭነት በምን ያህል እንደሚያድግ የሚያሳይ ነው።

ከጥቂት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአንድ ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ ማድረጋቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ከአገሪቱ መሪ ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር በአገራቱ መካከል ስላለው የኹለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መወያያታቸውና የሳልቫ ኪር ተቀናቃኝ ከሆኑት ሬክ ማቻር ጋር በመሆን ሁለቱን መሪዎች ወደ ስምምነት ማምጣታቸው ተዘግቧል።

የጠቅላዩ ጉብኝት ከወደቡ ግንባታ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ የተወሳ ነገር ባይኖርም በተለይ ከምዕራብ አፍሪካ የሚመጣውን የመንገድ ፕሮጀክት የምታገናኘው ደቡብ ሱዳን ጁባ በመሆኗ ፕሮጀክቱ የውይይታቸው አጀንዳ አልነበረም ለማለት አያስደፍርም የሚል አስተያየት ተሰጥቷል።

ይህ ምጽዋንና የአሰብ ወደቦችን ጥቅም ዐልባ የሚያደርግ ፕሮጀክት ኤርትራን የማያካትት ሲሆን ኤርትራ በዚህ ውስጥ መካተት የምትፈልግ ከሆነ የግድ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛትን መስመር መዘርጋት ይጠበቅባታል። ከመሠረተ ልማት ዝርጋታው ሌላ ኤርትራ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ለውጥ ማድረግ ሌላኛዋ የቤት ሥራዋ ይሆናል። በአንዳንድ የቀጣናው ባለሙያዎች ትንታኔ መሠረት ኤርትራ ፈጣን ለውጦችን የማታደርግ ከሆነ ነጻ ከወጣች ጥቂት ዓመታት ያስቆጠረችው ደቡብ ሱዳን ጋር ለመድረስ የሚያቅታት የቀጣናው ደካማ አገር ትሆናለች ይላሉ።

የሰሜኑ ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ የኢትዮጵያ ትኩረት ወደ ኢኮኖሚው በመሆኑና ለዚህም በኤርትራ ወደቦች ላይ ያላትን ፍላጎት ከጅቡቲ ሌላ ወደ በርበራ አሁን ደግሞ ወደ ላሙ ወደብ በከፍተኛ ሁኔታ ፊቷን ማዞሯ በአስመራ በኩል እጅግም ደስታን የፈጠረ አይመስልም። ጥቅም ዐልባ ከሆነው አሰብ ሌላ ምጽዋም ከኤርትራ በስተቀር የሚፈልገው የማይኖርበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

የላሙ ወደብ እና የመሠረተ ልማት ግንባታ ሲጠናቀቅ ከአዲስ አበባ አዋሳ እስከ ሞይሌ ባለው መሥመር ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ለውጥ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል። አዋሳ ላይ ያለው ኢንዱስትሪያል ፓርክ እና ወደ ደቡብ በሚወስደው መንገድ የሚመረቱ ፍራፍሬዎች ወደ ውጪ ምርት በቀላሉ የሚቀርቡ ሲሆን በተጓዳኝ በሚሠራው የነዳጅ ቧንቧ ኢትዮጵያ ያለ ወደብ በቀላሉ የነዳጅ ፍላጎቷን የምታሳካ ይሆናል።

ከዚህም ሌላ ኢትዮጵያ ምርቷን በምዕራብ አፍሪካ በኩል ወደ አውሮጳ፣ ሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም በምሥራቅ በላሙ የኬኒያ ወደብ በኩል ወደ ሕንድ፣ ቻይና፣ ሩቅ ምሥራቅ፣ አውስትራሊያና ኒው ዚላንድ የምታቀርብና የውጭ ምርቶችንም የምታስገባ ይሆናል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ የቻይና የምስራቅ አፍሪቃ ልዩ መልዕክተኛ ሰሞኑንን አዲስ አበባ ተገኝተው ከመንግስት ጋር መክረዋል። ምክክሩም ከጁባ መልስ እንደሆነ ይታወሳል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, Politics Tagged With: Lamu Port, LAPSSET, LAPSSET Corridor project

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule