ከሁለት ጠቅላይ ግዛቶች የተውጣጡ አንድ ሺህ ወታደሮች ያካተተ “ግብረኃይል” ከአንድ ወር ተኩል በኋላ ወደ አፍሪካ ቀንድ እንደምታዘምት አሜሪካ አስታወቀች። ግብረኃይሉ "ቀዩ ዘንዶ" በሚል ስያሜ የሚጠራ ሲሆን በዜናው ጦሩ "ወደ ኢትዮጵያ ይሄዳል" በሚል የተነሳ ጉዳይ የለም። የተሰጠውም ተልዕኮ ለአፍሪቃ ቀንድ ግብረኃይል ተጨማሪ ድጋፍ ለመስጠት ነው ተብሏል። ቅዳሜ ኅዳር 18፤ 2014 ዓም (ኖቬምበር 28፤ 2021) በተካሄደ ሥነሥርዓት ከ800 በላይ የሚሆኑ የቨርጂኒያ ግዛት ብሔራዊ አባላት ዘብ የተሸኙ ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ የኬንታኪ ግዛት ብሔራዊ ዘብ አባላት እንዲሁ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡ ይህ ከአሜሪካ የተላከው ግብረኃይል በምስራቅ አፍሪካዊቷ ጅቡቲ ከተቀመጠው የአፍሪካ ቀንድ ጥምር ግብረኃይል ጋር የሚቀላቀል … [Read more...] about በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ “ቀዩ ዘንዶ ግብረኃይል” ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅቡቲ ይጓዛል
Archives for November 2021
የተለያዩ ሀገራትን የገንዘብ ኖቶች ለማባዛት በዝግጅት ላይ የነበሩ የዉጭ ሀገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አንድ ካሜሩናዊ እና አንድ ኮቲዲቫራዊ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አማዶ ፔንሲኦን ውስጥ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አዲስ ብራይት ፔንሲኦን ውስጥ ነዉ የኢትዮጵያና የተለያዪ ሀገራት የገንዘብ ኖቶችን በማዘጋጀት ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡ የግለሰቦቹን ህገወጥ እንቅስቃሴ ሲከታተል የነበረዉ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተጠርጣሪዎቹን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥቆማ በመስጠት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሲዉሉ 107,330 ትክክለኛ የኢትዮጵያ ብሮች ፣ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ባለ 200 በርካታ ፎርጅድ የኢትዮጵያ ብሮች፣ ዱቄት መሳይ ኬሚካል፣ ፈሳሽ ኬሚካሎች፣ ከተር ወይም የወረቀት መቁረጫ፣ … [Read more...] about የተለያዩ ሀገራትን የገንዘብ ኖቶች ለማባዛት በዝግጅት ላይ የነበሩ የዉጭ ሀገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
“ሀገርን ማክበር የሚለው ሀሳብ የሚጀምረው የሀገርን ህግ ከማክበር ነው” – ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ያወጣውን ክልከላ የሚተላለፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ መንግስት አሳሰበ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ከቀናት በፊት፦ "ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችን እና ውጤቶችን በተመለከተ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ፣ በየትኛውም የመገናኛ አውታር መስጠትና ማሰራጨት ክልክል ነው። በየግንባሩ የሚገኙ የሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ከተሰጣቸው ሥምሪትና ተልእኮ ውጭ ማንኛውንም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችን እንዲሁም ውጤቶችን የሚመለከቱ መግለጫዎች መስጠት የተከለከለ ነው። የጸጥታ አካላትም ይሄን ተላልለፈው በሚገኙት ላይ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ታዟል። " የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል። በዛሬው ዕለት መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ መንግስት … [Read more...] about “ሀገርን ማክበር የሚለው ሀሳብ የሚጀምረው የሀገርን ህግ ከማክበር ነው” – ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ
“ምዕራባውያን መንግሥታት ዐቢይን በእነርሱ ቁጥጥር ሥር ማዋል ባለመቻላቸው ቀጠናውን ለማተራመስ እየሰሩ ነው” – ሎውረንስ ፍሪማን
ምዕራባውያንና አሜሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን በእነርሱ ይሁንታና ቁጥጥር ስር ማዋል ባለመቻላቸው፣ ኢትዮጵያንም ሆነ ቀጠናውን ማተራመስን መምረጣቸውን የአፍሪካ ፖለቲካ እና ምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑት ሎረንስ ፍሪማን ተናገሩ። አሜሪካ ዜጎችን ውጡ እያለች በምትወተውትበት ሰዓት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ሎረንስ ፍሪማን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት የአሜሪካና የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ላይ በውሸት ላይ የተመሰረተ የስነ-ልቦና ጦርነት ከፍተዋል፡፡ ይህንን የሚያደርጉት በሚስ-ኢንፎርሜሽን ሳይሆን ሆን ብለው፣ አቅደው ተከታዮቻቸውን ዲስ-ኢንፎርም ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡ ምዕራባውያንና አሜሪካ የሐሰት መረጃ የሚያሰራጩት ኢትዮጵያውያን በመሪያቸው አማካይነት የተደፈረውን ሉዓላዊነታቸውን ወደነበረበት ለመመለስ እየሰሩት ያለውን ስራ የፖለቲካ … [Read more...] about “ምዕራባውያን መንግሥታት ዐቢይን በእነርሱ ቁጥጥር ሥር ማዋል ባለመቻላቸው ቀጠናውን ለማተራመስ እየሰሩ ነው” – ሎውረንስ ፍሪማን
ትህነግ ሽንፈቱን አምኖ ያለ ቅድመ ሁኔታ ሽምግልና ለመነ
የትግራይ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለሃይማኖት ተቋማት “ሰላምን አስቀድመን እንስራ” ሲል ጥያቄ አቅረበ። ትህነግ መንግሥት ያቀረበውን ቅድመ ሁኔታ እንደሚቀበል ማሳወቁ ተሰማ። ሃይቅና ኮምቦልቻ በመከላከያ እጅ መግባታቸው እየተነገረ ነው። የትግራይ ቴሌቪዥን አማርኛ ላይ እንደተገለጸው “የትግራይ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፅ/ቤት ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰውን እና እየደረሰ ያለውን ግፍና ጭፍጨፋ በስልጣን ጥመኞች አማካኝነት በሌሎች ህዝቦችም ድርጊት ያለማቋረጥ እየተፈፀመ በመሆኑ ይህንን ግፍ እንዲያበቃም ሁሉም ህዝብና የሃይማኖት ተቋማት በሞላ ለሰላም ዘብ በመቆም የህዝባችንን ሰላም አስቀድመን እንስራ ሲል ጥሪ አቀረበ” ሲል ዜናውን በምስል አስደግፎ ይፋ አድርጓል። የአፍሪካ ህብረትን ምንጮችን የጠቀሰው … [Read more...] about ትህነግ ሽንፈቱን አምኖ ያለ ቅድመ ሁኔታ ሽምግልና ለመነ
በ2 ቀናት በተካሄደ ኦፕሬሽን 12 የትህነግ ከፍተኛ የጦር አመራሮች ተደምስሰዋል
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ዛሬ ምሽት በሰጠው መግለጫ ተደመሰሱ ካላቸው ውስጥ በፌዴራል መንግሥት በሀገር ክህደት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ጄነራሎችና ኮሎኔሎች ይገኙበታል። በመግለጫው ላይ ተደመሰሱ የተባሉት ጄነራሎችና ኮሎኔሎች ስም አልተገለፀም። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫ ይህን ነው ያሉት፦ "ባለፉት 2 ቀናት በባቲ ግንባር በተደረገ ልዩ ኦፕሬሽን 6 የአርሚና እና የኮር ከፍተኛ አመራሮቹ ተደምስሰዋል። እነዚህ አመራሮች በፌዴራል መንግሥት በሀገር ክህደት ወንጀል ሲፈጉ የነበሩ ከሃዲ ጄነራሎች እና ኮሎኔሎች ናቸው። በተጨማሪ በከሚሴ ግንባር በተለያዩ ቦታዎች በተደረጉ ልዩ ኦፕሬሽኖች የጠላትን ግንባር ጦር ሲመሩ የነበሩ 6 ከሃዲ ከፍተኛ የጦር አመራሮች ከነጠባቂዎቻቸው ተደምስሰዋል። በዛሬው ዕለት በባቲ ግንባር በተደረገው … [Read more...] about በ2 ቀናት በተካሄደ ኦፕሬሽን 12 የትህነግ ከፍተኛ የጦር አመራሮች ተደምስሰዋል
“ዐቢይ የዘመተው አማራን አስፈጅቶ ጦርነቱ ሲያልቅ ለራሱ ዝና/ኢጎ ነው” የ360 የማክሰኞ አጀንዳ
ከአሸባሪው ትህነግ ጋር የሚደረገውን የመጨረሻ ፍልሚያ አስመልክቶ ጠቅላዩ ይህንን ብለው ወደ ግምባር እንደሚዘምቱ አስታውቀዋል፤ “ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ”። ይህ በዘመናዊ አገላለጽ የተጻፈ ብዙ ጊዜ ሲነገር ከነበረው የአጼ ምኒልክ የክተት ጥሪ ጋር የሚመሳሰል ነው። ጠቅላዩ ቃላቸውን ጠብቀዋል። “አንገቴን እሰጣለሁ እንጂ ተላላኪ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ አይኖርም” ብለው ነበር። ምቾታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ወደ ሌላ አገር አልሄዱም። ወይም ደንዝዘው አዲስ አበባ በመቀመጥ እንደነ ጋዳፊ ለመሆን አልፈጉም። በዘመናዊ ታሪክ አገሩን … [Read more...] about “ዐቢይ የዘመተው አማራን አስፈጅቶ ጦርነቱ ሲያልቅ ለራሱ ዝና/ኢጎ ነው” የ360 የማክሰኞ አጀንዳ
TPLF dehumanized Olusegun Obasanjo as the “worst kind of chimpanzee”
A top confidant and an avid activist of the TPLF (Tigray People's Liberation Front) dehumanized the African Union’s High Representative for the Horn of Africa, Olusegun Obasanjo as “worst kind of chimpanzee”. In a Facebook post made in Tigrigna on Sunday, November 21, 2021, Gebremichael said, “this worst kind of chimpanzee called Obasanjo, following his trip from Mekelle (Tigray’s capital), it is now reported that Isayas (Eritrea’s president) (and) Prosperity (Party) conducted a drone attack … [Read more...] about TPLF dehumanized Olusegun Obasanjo as the “worst kind of chimpanzee”
ትህነግ ኤርትራውያንን ለመጨፍጨፍ ማቀዱን ትሮንቮል አረጋገጠ
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር - ትህነግ ስም ሳይጠራ “ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ትሠራላችሁ" በሚል የጠቀሳቸው ክፍሎች ኤርትራዊያንን እንደሆነ ጥርጥር እንደሌለው ተመለከተ። ዛቻው በኢትዮጵያ ያሉ የኤርትራ ተወላጆች ላይ እንደሆነም ተጠቁሟል። ትህነግ በመግለጫው በመከላከያ፣ በደኅንነትና ጸጥታ ተቋማት “ተሰግስጋችሁ” ሲል የፈረጃቸው ማስጠንቀቂያው እንዲደርሳቸው ደጋግሞ አመልክቷል። በዚሁ ስምና አገር ይፋ ባልተደረገበት የማስጠንቀቂያ መግለጫ የተጠቀሱት ተቋማት ውስጥ አሉ ያላቸው የውጭ ዜጎች “የአስካሁኑ በቃን” ብለው አገር ለቀው እንዲወጡ፣ አገራቸውም የተጠቀሱትን ወገኖች ከኢትዮጵያ እንዲያስወጡ ያሳሰባል። ይህ ካልሆነ “የትግራይ መንግሥትና ሰራዊት በትግራይ ህዝብ ጆኖሳይድ በፈፀሙ ወንጅሎኞች ላይ በሚወሰደዉ ማንኛዉም አፀፋዊ እርምጃ ተጠያቂ እንደማይሆን የዓለም አቀፍ … [Read more...] about ትህነግ ኤርትራውያንን ለመጨፍጨፍ ማቀዱን ትሮንቮል አረጋገጠ
የዛሬ ዓመት በማይካድራ በተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ
• አንድ ሺ 564 ሰዎች በጭካኔ ተገድለዋል። • 81 ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። • ድርጊቱን የፈጸመው አሸባሪው ሕወሓት ያደራጀው ሳምሪ የሚባል ገዳይ ቡድን ነው። የዛሬ ዓመት በማይካድራ በተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ አንድ ሺ 564 ሰዎች በጭካኔ መገደላቸውን፤ 81 ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ድርጊቱን የፈጸመው አሸባሪው ሕወሓት ያደራጀው ሳምሪ የሚባል ገዳይ ቡድን መሆኑን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህርና ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት የጥናት ቡድን መሪ ገለጹ። የጥናት ቡድኑ መሪ አቶ ጌታ አስራደ አለማየሁ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የዛሬ አመት በማይካድራ ጭፍጨፋውን ያካሄዱት ሳምሪ የተባለ አሸባሪው ሕወሓት ያደራጃቸው ገዳይ ቡድን ነው። ይህ ቡድን አንድ ሺ 564 ሰዎችን መጥረቢያ፣ ቆንጨራና፣ ቢለዋ፣ ማጭድና መሰል … [Read more...] about የዛሬ ዓመት በማይካድራ በተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ