አንድ ካሜሩናዊ እና አንድ ኮቲዲቫራዊ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አማዶ ፔንሲኦን ውስጥ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አዲስ ብራይት ፔንሲኦን ውስጥ ነዉ የኢትዮጵያና የተለያዪ ሀገራት የገንዘብ ኖቶችን በማዘጋጀት ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡
የግለሰቦቹን ህገወጥ እንቅስቃሴ ሲከታተል የነበረዉ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተጠርጣሪዎቹን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥቆማ በመስጠት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሲዉሉ 107,330 ትክክለኛ የኢትዮጵያ ብሮች ፣ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ባለ 200 በርካታ ፎርጅድ የኢትዮጵያ ብሮች፣ ዱቄት መሳይ ኬሚካል፣ ፈሳሽ ኬሚካሎች፣ ከተር ወይም የወረቀት መቁረጫ፣ በርካታ ቾክ፣በርካታ ወረቀት፣ 9 ሞባይል ስልኮች እና ሌሎች ቁሳቁሶች መያዛቸዉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመገናኛ ብዙሃን በላከዉ መረጃ አመልክቷል። (አዲስ ሚዲያ)
ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply