የትግራይ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለሃይማኖት ተቋማት “ሰላምን አስቀድመን እንስራ” ሲል ጥያቄ አቅረበ። ትህነግ መንግሥት ያቀረበውን ቅድመ ሁኔታ እንደሚቀበል ማሳወቁ ተሰማ። ሃይቅና ኮምቦልቻ በመከላከያ እጅ መግባታቸው እየተነገረ ነው።
የትግራይ ቴሌቪዥን አማርኛ ላይ እንደተገለጸው “የትግራይ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፅ/ቤት ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰውን እና እየደረሰ ያለውን ግፍና ጭፍጨፋ በስልጣን ጥመኞች አማካኝነት በሌሎች ህዝቦችም ድርጊት ያለማቋረጥ እየተፈፀመ በመሆኑ ይህንን ግፍ እንዲያበቃም ሁሉም ህዝብና የሃይማኖት ተቋማት በሞላ ለሰላም ዘብ በመቆም የህዝባችንን ሰላም አስቀድመን እንስራ ሲል ጥሪ አቀረበ” ሲል ዜናውን በምስል አስደግፎ ይፋ አድርጓል።
የአፍሪካ ህብረትን ምንጮችን የጠቀሰው የአዲስ አበባ ተባባሪያችን እንዳለው ይህ የሃይማኖት ተቋማት ጥሪ ከመተላለፉ አንድ ቀን በፊት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ሽንፈቱ አምኖ ለአፍሪካ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ የሰላም አምባሳደር መንግሥት ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ እንደሚቀበል መናገሩን አስታውቋል።
ድፍን የአፋር ክልል ከትህነግ ወረራ ነጻ መውጣቱ ይፋ በሆነበትና ባቲና ኮምቦልቻ በአገር መከላከያና በአማራ ልዩ ሃይል እጅ መውደቃቸው በተሰማ ቅጽበት የትግራይ የሃይማኖት ጉባኤ ጽህፈት ቤት ላቀረበው ጥያቄ እስካሁን በገሃድ ምላሽ የሰጠ አካል የለም። ከዚህ ቀደም የትግራይ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ዋናውን ሲኖዶስ “አላውቅህም” ሲል በይፋ በመግለጫና በቃለ ምልልስ በተለየዩ መገናኛዎች ሲያወግዝ እንደነበር ይታወሳል።
ዛሬ ጉባኤው “… ሰላምን አስቀድመን እንስራ” በማለት ጥሪ ሲያደርግ እነ ደብረጽዮን “እኛ ክልል ነው ሰላም ያለው” በማለት ከዚህ በፊት የቀረበላቸውን የሰላም ሃሳብ ውድቅ ማድረጋቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነና እንዳልሆነ ምንም ያለው ነገር የለም።
ቀደም ሲል ጦርነት ከመከፈቱ በፊት የሰላም አባቶችና እናቶች በትግራይ በመገኘት የዕርቅ ጥያቄ ሲያቀርቡ የትግራይ የሃይማኖት ምክር ቤት አቋም ግልጽ አልነበረም። የሰላም አሳብ እጅግ የሚደገፍ ቢሆንም ጉባኤው ለምን ዛሬ ላይ ይህን ጥሪ እንዳቀረበ ማብራሪያ አለመስጠቱ ማብራሪያ አላስቻለም።
ማብራሪያ መስጠት ባይቻልም የአፍሪካ ሕዝብረት ምንጮቹን የጠቀሰው ተባባሪያችን እንዳለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መንግሥት ያስቀመጠውን ቅደም ሁኔታ በመቀበል ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑንን በሽምግልና መልዕክቱ አስታውቋል።
መንግሥት የትህነግን ጦር እንደሚያፈርስ፣ ትህነግ ትጥቅ እንደሚፈታና መንግሥትን እንደ መንግሥት ተቀብሎ ከወረራቸው ስፍራዎች በሙሉ በመልቀቅ ላደረሰው ውድመት በህግ አግባብ የሚጠየቁ ክፍሎችን ለህግ አሳልፎ እንዲሰጥ የሚሉ ቅድመ ሁኔታዎች እንደሆኑ የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
አዲስ አበባ ለመግባት ሰላሳና አርባ ኪሎሜትር እንደቀረው ሲገለጽለት የነበረው ትህነግ “ከተሞች እንዳይጠፉ የገጠር ትግል ጀምሬ ወደፊት እየገሰገስኩ ነው። የዐቢይ መንግሥት የሚሞት መንግሥት ነው …” በሚል ሲገልጸውና “እጅህን ስጥ” በሚል በተደጋጋሚ ጥሪና ማስጠንቀቂያ ሲያቀርብለት የነበረው ሠራዊት ሰሞኑንን ጋሸናንና ላሊበላን፣ ትናንት ካሳጊናን ዛሬ ደግሞ ባቱና ኮምቦልቻን ተቆጣጥሮ ወደ ደሴ እያመራ መሆኑ በሚገለጽበት ቅጽበት የትግራይ የሃይማኖት ጉባኤ ያቀረበው “ለሰላም አብረን እንሥራ” ጥያቄ በርግጥም ትህነግ በጦር ሜዳ ድል እንዳጣ አመላክች ሆኖ ተወስዷል።
ከፍጥረቱ ጀምሮ ትህነግ የሚያሸንፍ ሲመስለው በኃይል እንደሚሄድ፤ ወደ ሽንፈት ሲቃረብ ደግሞ ቀድሞ ያጣጣለውን ሽምግልና፣ ዕርቅ፣ ድርድር ወዘተ ከአፈር አንስቶ እግዚዖ እንደሚል ታሪኩ ያስረዳል። በምርጫ 97 ሲሸነፍ ዕርቅና ድርድር ያለው ትህነግ ነገሮች መስመር ሲይዙለት ተቃዋሚዎችን በማሰርና በመግደል ሥልጣኑን እንዳስቀጠለ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። በቅርቡም በተደጋጋሚ የቀረበለትን የሰላም ሃሳብ የኃይል ሚዛኑ ወደሱ ያጋደለ ሲመስል ሲያጣጥል፤ ስሉሱ ሲዞርበት ደግሞ ሲለማመጥ መቆየቱ ይታወሳል።
የአፍሪካ ህብረት ምንጮች እንዳሉት ትህነግ ላቀረበው ጥያቄ እስካሁን መልስ አልተሰጠውም። ዛሬ አቶ ዛዲግ ይፋ እንዳደረጉት ከሆነ መንግሥት ከሽብረተኛና አገር ለማፈራረስ ከተነሳ ድርጅት ጋር አይነጋገርም።
የኢትዮጵያ መከላከያ ከአማራና አፋር ልዩ ሃይል እንዲሁም ሚሊሻ ጋር በመሆን ማጥቃቱን እንደቀጠለ መንግሥት ማስታወቁ ይታወሳል። ፊልትስማንን የትህነግ የአዲስ አበባ ጉዞ የከሸፈ መሆኑንን ማስታወቃቸውና “ዛሬ 1983 አይደለም ብለን ነግረናቸዋል” ማለታቸው አይዘነጋም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጦር ሜዳ መሄዳቸውን ተከትሎ በርካታ ሕዝብና ታዋቂ ዜጎች ወደ ግንባር መዝመታቸውና የጦሩ የመዋጋት አቅም እጅግ እንደተነገነባ የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች እያስታወቁ ነው።(ኢትዮ12)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Tesfa says
የዘገየ ንስሃ ለመቅሰፍት ይሆናል ይላሉ አበው። የት ነበራችሁ? እናቶች ደብረጽዪንን እየጮሁና እያለቀሱ ሲለምኑት። የት ነበራችሁ የሰላም ሚኒስቴሯ በእንባ እየታጠቡ ተው በማለት የወያኔን ጅንታዎች ሲማጸኑ። የት ነበራችሁ ከ 10 ሺህ በላይ የሰሜን እዝ ሰራዊት በተኙበት ሲታረድና ሲገደሉ? ጉራ ጉረኛን ይወልዳል። ንቀት ውድቀትን ይቀድማል። ወያኔ ውጊያ ላሳር ነው በማለት የውጭ ሃይሎችን ተማምኖ የከፈተው ይህ ዘር አጥፊ ውጊያ መከራ ያዘነበው ከትግራይ ህዝብ ይልቅ በወሎ፤ በጎንደር፤ በሽዋና በአፋር ነው። አሜሪካን ያመነ ውሃ የዘገነ እንዲሉ በሰውርና በይፋ አይዞህ እያሉ የሚያጫርሱን እነዚህ ሃገር አፍራሾች ለማንም አይገዳቸውም። ወያኔ ግን የጅሎች ጥርቅም ነው። በአፍጋኒስታን፤ በግብጽ፤ በሊቢያ፤ በሶሪያ፤ በየመን ከሆነውና ከሚሆነው የማይማር እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀል ባይ የብሄርተኛ ጥርቅም አፍሪቃዊም ሆነ ኢትዮጵያዊ ወኔ የሌለው በራሱ ታምቡር የሚጨፍር የደንበር ገተሮች ስብስብ ነው። 27 ዓመት አጥንቷ እስኪቀር የጋጧትን ሃገር ሲኦል ድረስ ወርደን እናፈርሳታለን ሲሉ የትግራይ ህዝብ ምን አለ? በወረራቸው ስፍራዎች ፋብሪካዎችን፤ ት/ቤቶችን/ኪሊኒክና ሆስፒታሎችን እያፈራረሰና እያቃጠለ እየነቀለ ትግራይን መንግስት አረጋለሁ በማለት ሊጥ ሳይቀር ሲያጓጉዝ ማን ትንፍሽ አለ? ዝምታ መተባበር ነው።
ወያኔ ዳግመኛ በኢትዮጵያ ምድር ላይ እድል ፈንታ የለውም። ትግራይን ገንጥለን ሃገር እናረጋለን ካሉም ይጓዙ። በምንም ዓይነት ሂሳብ ወያኔ የትግራይ ህዝብ የበላይ መሪ ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም አይመጣም። ወያኔ መጥፋት ያለበት ድርጅት ነው። እሱ ሲከስም የትግራይ ህዝብ ራሱ በራሱ በመረጠውና ሲፈልግ በሚያወርደው ሲመራ ያኔ አብሮ የመኖር ጭላንጭል ሊኖር ይችል ይሆናል። ገና እኮ ወያኔ ያደረሰው በደል በደንብ አልተሰላም። ገና እኮ ስንት የትግራይ ልጆች በዚህ ወረራ እንደ ረገፉ ቁጥሩ አልታወቀም። ወያኔ ሂትለራዊ እይታ ያለው ድርጅት ነው። ለወያኔ የሰው ሞት እንደ ደሮ ሞት ነው። ሃገሬ ናት ብሎ ለ 27 ዓመት ያስተዳደራትን መልሶ የሚያፈርስ በአለም ላይ ከወያኔ ሌላ አጥፊ ሃይል ተፈጥሮ አያውቅም። ራሳቸው ፋሽሺቶች ሆነው የፋሽሽቱ የአብይ መንግስት ሲሉ አለማፈራቸው። ማ ነው ሰውን በተኛበት ያረደው? ማን ነው ሴቶችን በደቦ የደፈረው? እነማን ናቸው ገበሬው በመከራ ያበቀለውን ያልደረሰ እህል በእሳት ያጋየውና የደረሰውን ወደ መቀሌ ያሸሽው? ስንቶች እናቶችና እህቶቻችን ነው የተገደሉት በትግራይ ወራሪ ሃይሎች? ስንቶች የቤት እንስ ሳት ውሾች ሳይቀሩ ነው የወያኔ ድርቡሾች የኢላማ መለማመጃ የሆኑት? የትግራይ ወራሪ ሃይል ማለት ጭንቅላት የሌለው በእጽ የደነዘዘ፤ በብሄር ጥላቻ የሰከረ፤ ከወርቃማው የትግራይ ህዝብ ተወለድ ብሎ የሚያምን የዘራፊዎች ስብስብ ነው። ትግሬዎች በኢትዮጵያ ላይ ችግር ፈጣሪ ሲሆኑ ወያኔ የመጀመሪያው አይደለም። በፊትም ተፋልመዋል። ታሪክን ዞር ብሎ ላየ የሚያመላክተው ያን ነው። የሃገር አፍራሽ መንጋ አሁን ተጠራርቶ በ 11 ኛው ሰአት ላይ ሰላም ቢል ለእኔ አይደንቀኝም። የዋሽንግተኑ ሴራ አለመስራቱን ብቻ ነው የሚያሳየው። የሮበርት ሙጋቤን ሃገር በልዪ ልዪ ሴራ የኢኮኖሚ አውታሩን ያሽመደመድት አሜሪካኖች የኢትዮጵያንም ኢኮኖሚ ያዘኑ መስለው ሊንድት ቃጥተዋል።
ረጋ ብሎ ለተመለከተ ዛሬ በኢራንና በአሜሪካ ያለው እሰጣ ገባ ምንጩ በ 50 ዎቹ የተጀመረ ነው። የኢራን ህዝብ ልክ እንደ ዶ/ር አብይ የመረጠውን መንግስት አሜሪካና እንግሊዝ አውርደው የራሳቸውን አሻንጉሊት መንግስት እንዳስቀመጡ ታሪክ ያሳየናል። ዛሬ ግን ያ ቀርቶ ሌላ ዘፈን መቶ – ማንም ማንንም አይፈራም። በጉልበትና በአሻጥር የሚሆኑ ነገሮች ሁሉ እየተነቃባቸው ነው። እርዳታ ሰጪ ድርጅቶ፤ በልዪ ልዪ ስም ወደ ሃገር የሚገቡ ቡድኖች ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአሜሪካው የስለላ መረብ ሰራተኞች እንደሆኑ ዓለም እያወቀ ነው። ዓለምን እንደ ፈለጉ ማተራመስ አልተቻለም። አሁን በቤንዚዌላ ላይ የሚደረገው ሴራና የኢኮኖሚ ማ ዕቀብም ከዚሁ የክፋት ጆኒያቸው የተቆነጠረ ነው። በምንም መለኪያ ቢሆን ለሰላምና ዲሞክራሲ ቆመናል የምትል እንደ አሜሪካ ያለች ሃገር ከደም አፍሳሹና ከዘረኛው ወያኔ ጋር አትሰለፍም ነበር። ግን ለእኛ እምብዛም ግልጽ ያልሆነልን ለአሜሪካኖች ግን ፍንትው ብሎ የታያቸው አንድ ነገር በምድራችን ላይ አለ? አሜሪካ ለራሷ ጥቅም ብቻ የቆመች ሃገር ናት። ጥርሱ የወላለቀውን አሮጌ ወያኔ ለመጠገን እንዲህ ያስደረጋት ሌላ ጉዳይ አለ። ጊዜ እሱን ይገልጥልናል እንጂ ወያኔን ለማዳን ብቻ ነው ብዬ አላምንም።
ወያኔዎችና የወያኔ ተከታዪች እውነትን የካድ በቋንቋና በዘራቸው የሰከሩ፤ ቆመንለታል ለሚሉት የትግራይ ህዝብ ያልቆሙ በሰው ደም ነጋዴዎች ናቸው። ሰላምን ማንም አይጠላም። ግን ወያኔ ከምድረገጽ መጥፋት ያለበት ድርጅት ነው። እግራቸው ሻባ የሆነ፤ ቆለጣቸው ከስራ ውጭ የሆነ፤ ማህጸናቸው የተበላሸ፤ ሰዶማዊ ድፍረት ተደፍረው ዛሬም በህይወት ያሉ የሚያነቡ፤ አያትና አባቶቻቸው ጀግኖች ስለነበሩ ገና ልጅና የልጅ ልጆቻቸውም ለወያኔ እንቅፋት ይሆናሉ ተብሎ ታፍነው የት እንደገቡ የማይታወቁ፤ በትግራይ ገደላማና የጉድጓድ እስር ቤቶች ተቀብረው የቀሩ ኸረ ስንቱ ይወራል። ይህ ድርጅት ነው ለትግራይ ህዝብ መንግስት ሆኖ የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲና ሰላም እንዲያገኝ የሚያስችለው? ጭራሽ። የሰላም ጥሪው ቅድመ ሁኔታውን እንደገና አጢኖ ፓርላማ ተከራክሮበት የኢትዮጵያ ህዝብ ሰምቶት የሚደረግ እንጂ ከላይ ባሉ አመራሮች ብቻ የሚፈጸም መሆን የለበትም። በዚህ ጉዳይ ላይ ማንም ነጭ መግባትም የለበትም። በተለይ አሜሪካ። አሜሪካና ወያኔ አንድ ናቸው። በቃኝ!
Tilahun Gudina says
Ethiopia mengizem ashenafi nat shinfet letelatochuwa yehun