• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ “ቀዩ ዘንዶ ግብረኃይል” ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅቡቲ ይጓዛል

November 29, 2021 03:03 pm by Editor 1 Comment

ከሁለት ጠቅላይ ግዛቶች የተውጣጡ አንድ ሺህ ወታደሮች ያካተተ “ግብረኃይል” ከአንድ ወር ተኩል በኋላ ወደ አፍሪካ ቀንድ እንደምታዘምት አሜሪካ አስታወቀች። ግብረኃይሉ “ቀዩ ዘንዶ” በሚል ስያሜ የሚጠራ ሲሆን በዜናው ጦሩ “ወደ ኢትዮጵያ ይሄዳል” በሚል የተነሳ ጉዳይ የለም። የተሰጠውም ተልዕኮ ለአፍሪቃ ቀንድ ግብረኃይል ተጨማሪ ድጋፍ ለመስጠት ነው ተብሏል።

ቅዳሜ ኅዳር 18፤ 2014 ዓም (ኖቬምበር 28፤ 2021) በተካሄደ ሥነሥርዓት ከ800 በላይ የሚሆኑ የቨርጂኒያ ግዛት ብሔራዊ አባላት ዘብ የተሸኙ ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ የኬንታኪ ግዛት ብሔራዊ ዘብ አባላት እንዲሁ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ይህ ከአሜሪካ የተላከው ግብረኃይል በምስራቅ አፍሪካዊቷ ጅቡቲ ከተቀመጠው የአፍሪካ ቀንድ ጥምር ግብረኃይል ጋር የሚቀላቀል ነው፡፡

ቤድፎርድ ከተባለችው የቨርጂኒያ ግዛት የተላከው ግብረኃይል ከኬንታኪው ጋር በመቀላቀል ወደ ቴክሳስ ግዛት በመሄድ ከ30 እስከ 45 ቀናት የሚወስድ ተጨማሪ ሥልጠና ይወስዳል፡፡ ይህ ሥልጠና ካበቃ በኋላ ነው ወደ ጅቡቲ ወታደሮቹ የሚላኩት፡፡

በዕለቱ የተሸኙት ወታደሮች ቤተሰቦቻቸውን በለቅሶ በተሰናበቱበት ወቅት “ሽኝት ቀላል ነገር አይደለም፤ ሁልጊዜ በጣም አስቸጋሪ ነው፤ በቤተሰቤ ሕይወት ውስጥ ቁልፍ የሆኑ ኩነቶች ያመልጡኛል” በማለት የግብረኃይሉ አዛዥ ሌተና ኮሎኔል ተናግረዋል፡፡

“ለቨርጂኒያ ብሔራዊው ዘብ 10 ዓመት ሳገለግል ይህ የመጀመሪያዬ ነው ወደ ውጭ አገር ስላክ” በማለት መጋቢ ሃምሳ አለቃ ካትሪን ተናግራለች፡፡ ከተጋቡ ሁለት ወራት የሆናትን ሚስቱንና ወላጆቹን ስሜት እየተናነቀው የተሰናበተው ሌላኛው ወታደር “ለዘመቻ መላክ በጣም ይደብራል፤ አባቴም ወታደር ስለነበር ሁኔታውን ይረዳል፤ ለሚስቴ ጥሩ እንክብካቤ ያደርግላታል ብዬ አስባለሁ” ብሏል፡፡

ዜናውን የተከታተሉ እንደሚሉት እነዚህ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እና ውጊያ የሚያደርጉ አይደሉም፤ በዜናው እንደተጠቀሰው ጅቡቲ ለሚገኘው ኃይል ድጋፍ ለማድረግ ነው፡፡ ነገርግን ወደ ኢትዮጵያ እንግባ እንኳ ቢሉ ለሕይወቱ ቅንጣት ከማይሳሳ መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ ጋር ነው በአገሩ መልከዓምድር የሚገጥሙት ብለዋል፡፡

ትህነግ ወደ ሚሌ ሊያደርግ ያቀደውን ጉዞ በጭፍራም ይሁን በባቲ መስመር እንዳይሳካ ሆኖ በከፍተኛ ሽንፈት ላይ ባለበት ወቅት ይህ የአሜሪካ ግብረኃይል ለዘመቻ መላኩ የትህነግን ክስረት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በአንጻሩ ትህነግን ለመታደግ ቢሆን ኖሮ ቢቻል ከዚህ በፊት ባይሆን አሁን በፍጥነት መላክ ነበረበት፡፡ ሆኖም ከአንድ ወር በኋላ መላኩ በዜና ዘገባዎችም እንደተገለጸው አሜሪካ የራሷን መከላከያ ኃይል ለማጠናከርና ካስፈለገም የዜጎቿን ደኅንነት ለማስጠበቅ የላከቸው ኃይል እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡

የቨርጂኒያው ኃይል የተሸኘበት ቤድፎርድ የተባለችው ከተማ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የነበራት ሕዝብ ብዛት 3200 የነበረ ሲሆን በወቅቱ ብዙ ወታደር ያጣች ከተማ ነች፡፡ እኤአ በ1944ዓም 150ሺህ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ፈረንሳይ ከዘመቱ በኋላ እዚያ በደረሱበት የመጀመሪያ ቀን 4500 ወታደሮች ሲሞቱ ከእነዚያ ውስጥ 19ኙ ከቤድፎርድ ከተማ ቨርጂኒያ ግዛት የተላኩ ነበሩ፡፡ በጦርነቱ በአጠቃላይ 35 ወታደሮች ከከተማዋ ብቻ ሞተዋል፡፡

የዛሬ 28 ዓመት የሶማሌውን አንጃ መሪ ጄኔራል ፋራህ አይዲድን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ከተላኩ የአሜሪካ ወታደሮች 19ኙ በሶማሊያ ኃይል ተገድለው 73ቱ ደግሞ መቁሰላቸው ይታወሳል፡፡ ከተገደሉት መካከል የተወሰኑት በሞቃዲሾ መንገዶች ላይ በመጎተታቸው አካላቸው ተቆራርጦና በጣም ከፍተኛ እንደደረሰባቸው የሚታወስ ነው።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: operation dismantle tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    November 29, 2021 03:53 pm at 3:53 pm

    አይ ለይቶላቸው ወደ መቀሌ ቢሄድ አይሻልም ነበር። አሜሪካ የውሸት ፕሮፓጋንዳዋ ተቀባይነት ሲያጣ አሁን ደግሞ እሳት ይዛ እሳት ልታቀብል መዘጋጀቷን ይህ ነገር ያሳያል። ለዚያ ነው አሜሪካኖች ዋና ስራቸው ተንኮልና ሃገር ማፍረስ ነው የምንለው። ይህ ዝም ብሎ ከሚያልፍ ወንዝ የተቀዳ ወሬ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ የሚፈጽሙት ተግባር ዋቢ ነው። ግራ ያጋባል የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ፓሊሲ ረጋ ብሎ ለተመለከተው። አንድ ጋ ሲባረሩ ሌላው ጋ እሳት ይጭራሉ። ዛሬ ዪክሬንን አፍንጫዋ ድረስ የሚያስታጥቁት አሜሪካኖች ራሽያ ዪክሬንን ብትወር ወታደሮቻቸው ዘር አይሉም። ያፋልማሉ እንጂ አይፋለሙም። እሾህን በእሾህ ያወጣሉ እንጂ እነርሱ እምብዛም አይሞቱም። ከሞቱም እየየውና ለቅሶው ለነጩ የተለየ ነው። አይ ሃገር። ሰላምና ዲሞክራሲን ለማስፈን እየተባለ የቆመን ማፍረስ፤ በፍርስራሹ ውስጥ ሴራን መንዛትና ምድሪቱ ለዝንተ ዓለም ለማኝና ችጋራም ሆና እንድትኖር ማድረግ ግባቸው ነው። ትላንት ለሌላው ሃገር ይተርፉ የነበሩት ሃገሮች በአሜሪካ ሴራና የኢኮኖሚ ማዕቀብ ተሽመድምደዋል። የሃገሬው ህዝብ የደነዘዘ በመሆኑ በአሜሪካ ህዝብ ስም መንግስታቸው የሚያደርገውን የፈጠራው ዜና ከሚያናፍሰው በስተቀር እውነቱን አያውቁም ማወቅም አይፈልጉም።
    አፍቃሪ ትህነግ አሜሪካኖች ወያኔን አዲስ አበባ ለማስገባት ያልሞከሩት ዘዴ የለም። ችግሩ ወይ ፍንክች ሲሆንባቸው ከማስፈራራትና የለሌ ወሬ ከመንዛት አልፈው አሁን ጦር መዘው መጣን እያሉን ነው። ይሁና። እየሞቱ መኖር ነው። ጊዜውን እንደሆነ ይኖርብናል እንጂ እኛ በጊዜአችን መኖር አልቻልንበት። አሜሪካ ለይቶላት ኢትዮጵያ ላይ ትንኮሳ ካደረገች ልክ እንደ አፍጋኒስታን ፊልሚያው የስውርና የግልጽ ነው የሚሆነው። አሜሪካ ሃገሮችን በማስፈራራትና መሪዎቻቸውን በመግደል ታደርግ የነበረው ዘረፋና መቆጣጠር አክትሟል። ይሞክራሉ ግን ያው ስኬት አይኖረውም። በተለይ ኢትዮጵያ ላይ እንዲህ አይነት ችግር ከፈጠሩ ውጊያቸው በዓለም ላይ ካሉ ሰላም ወዳድና አሜሪካ ጠል ሃገሮች ጋር ነው የሚሆነው። እኛ ያልነውን ካልሰማችሁ ወዪላችሁ የሚለው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፓሊሲ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን አይሰራም። አዎን እንራባለን፤ በዚህም በዚያም ሰዎችንና ሃገሮችን እያስታጠቁ እርስ በእርሳችን ያጋድሉናል ግን መጨረሻው ልክ በአፍጋኒስታን ከ 20 ዓመት በህዋላ እንደሆነው ሁሉ የሰው መሳቂያ ሆነው ነው የሚፈረጥጡት። የአሜሪካ ሴራ ማቆሚያ የለውም። የትኛውም የፓለቲካ ፓርቲ ስልጣን ላይ ይሁን አይቀየርም። ዛሬ ሱዳን ልቧን ነፍታ የኢትዮጵያን መሬት ወራ የያዘችውም በዚሁ በአሜሪካ አይዞህ ባይነትና ተንኮል ነው። በቅርቡ የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ የሆነው የሱዳን ወታደራዊ መሪ በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ ገብቶ ጉብኝት እንዲያደርግ የገፋፉት እነርሱ ናቸው። ሲሻቸውና የመገልገያ ጊዜው ሲያበቃ ልክ እንደ ፓናማው ጄ/ኖርዌጋ በዚህም በዚያም አሳበው እስር ቤት ይጨምሩሃል ወይም ከጄኔራል ኖሬይጋ በፊት እንደነበረው የፓናማ መሪ ህዝባዊ ተሰሚነት ካለህም ገድለው ሞተ ይሉሃል። Read ” Confession of an Economic Hit man” by John Perkins እውነቱ እሱ ነው። አሁን አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውም ዘይቤ በዚሁ መጽሃፍ ላይ ከተጠቀሱት ብልሃቶች የተወሰደና በዘመናዊው የኢንተርነት የአስረሽ ምቺው ውንብድናቸው የጣፈጠውን ነው። የእነ ዶ/ር ኤሌኒ ስብሰባ፤ የ 9ኙ የዲሲ የሽግግር መንግስት ድለቃ፤ የፊልትማን የኢትዮጵያ ምልልስ፤ የተመድ ድግግሞሽ ስብሰባ፤ ዜጎቼን አወጣለሁ፤ የኢትዮጵያ የአየር ክልል አደጋ አለበት ወዘተ እየተባለ የሚናፈሰውና የሆነው ሁሉ የዚሁ ሴራቸው ድምር ሂሳብ ነው።
    አሜሪካኖች ከግብጽ ጋር ምን እየመከሩ እንደሆነ የሚያውቅ አለ? አሜሪካኖች ለዘመናት ኤርትራን ፈርጀው ለችጋር ያጋለጧት በእውነት የኤርትራው መሪ ከሌሎች ሃገራት መሪዎች ከፍተው ነው? እንዴት ይህንና ሌሎች መሰል ነገሮችን የሚሰማ፤ የሚያነብ፤ የሚያይ ሰው ወንድሙንና እህቱን ይገድላል? አያሳዝንም? እስከ መቼ ነው የነጭ መፈንጫ የምንሆነው? ግን አይዞን እንኳን 500 ዓመት ያልሞላው የአሜሪካው መንግስት ይቅርና የሮም መንግስትም ተፍረክርኳል። በእንግሊዝ ግዛት ጸሃይ አትጠልቅም የተባለላት እንግሊዝ አሁን በአንዲት ደሴት መሳይ ሃገር ነው ተወስና ያለችው። ቀልደኛው በእንግሊዝ ግዛት ጸሃይ አትጠልቅም ሲሉት ” አይ ፈጣሪ እንግሊዞችን በጨለማ ስለማያምናቸው ነው” በማለት ነበር ያፌዜው። ግን እውነትነት አለበት። ዛሬ በምድር ላይ ላሉ ፍትጊያዎች ሁሉ ምንጮቹ እንግሊዞች፤ ፈረንሳዪች፤ አሜሪካኖች ቀዳሚዎቹ ናቸው። አሁን እጣው በሃበሻው ምድር ላይ ወጣና ያጫንቁን ጀመር። እናያለን ቀን የሚያመጣውን። እስከዚያው አይዞን። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule