በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው 98 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሐመድ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመውጣቱ አስቀድሞ የክልሉ ፖሊስ የተጠናከር የክትትል ስራ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ኮሚሽነሩ እንዳሉት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ወጥቶ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የክልሉን ሠላም ለማስጠበቅ ለፀጥታ አስከባሪ ኃይሉ ተጨማሪ አቅም ሆኖታል። ግለሰቦቹ በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉት ከአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደነበራቸው ፖሊስ በደረሰው መረጃ መሰረት ከጥቅምት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባደረገው ኦፕሬሽን ነው ብለዋል፡፡ አሸባሪው … [Read more...] about በቤኒሻንጉል ከትህነግና ሸኔ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው 98 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
Archives for November 2021
“የዛሬዋ ኢትዮጵያ አይደለም የትላንትናውን ትህነግ የዘመነውን ትህነግ ለመቀበል አትችልም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
* "በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈዋል" * የ፷፪ ዓመት ሽማግሌ ከትግራይ ለትህነግ ዘምቷል በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከአሸባሪው ቡድን ጋር መሳተፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በጦርነቱ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ እና የኢትዮጵያውያ ዝርያ የሌላቸው ነጮች እና ጥቁሮች ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሳትፈው መስዋትነት መክፈላቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያረጋገጡት። “በወሎ ግምባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈውበታል። የኢትዮጵያ ዝርያ የሌላቸው ሰዎች ተሳትፈው መስዋዕትነት ከፍለዋል። ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ሰው ኢትዮጵያ መጥቶ በደሴ … [Read more...] about “የዛሬዋ ኢትዮጵያ አይደለም የትላንትናውን ትህነግ የዘመነውን ትህነግ ለመቀበል አትችልም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ