የውጪና የውስጥ ደጋፊዎቹንና አይዞህ ባዮቹን፣ ለዘመናት ከኢትዮጵያ የዘረፈውን ገንዘብና የጦር መሣሪያ የተማመነው ት ህነግ በእብሪት ጦርነት ውስጥ በገባበት ወቅት የአክሱምን አየር ማረፊያ በግሬደር ማረሱ የቅርብ ጊዜ ፅታ ነው። ማሰብ የተሳነው ትህነግ ይህንን ያደረገው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና እና አየር ኃይል የአክሱምን ኤርፖርት ለጦርነቱ እንዳይጠቀሙበት በሚል የጨነገፈና ኋላቀር አስተሳሰብ ነበር። ጦርነቱ የተካሄደው ት ህነግ ፈጽሞ ባልጠበቀው፣ እነ ስዬ አብርሃ ባለቀሱበት የአየር የበላይነትና በድሮን ነበር። የአክሱም ኤርፖርት ግን ምንም ላይፈይድ ፈርሶ ቀረ፤ ሕዝቡ አሁን በውጤቱ እያማረረ ይገኛል። በከፍተኛ ደረጃ የከተማው የንግድ እንቅስቃሴ በቱሪዝም መስህቦች ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው በአጼ ዮሃንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የደረሰው ጉዳት የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ላይ … [Read more...] about በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ
News
ዜና
“የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል
ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በችግር ውስጥ የሚገኙበት ደብረብርሃን ከተማ ከአዲስ አበባ ዙሪያና ከኦሮሚያ ክልል ተጨማሪ ተፈናቃዮችን በመቀበሉ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት አስታወቀ። በደብረብርሃን ከተማ ከ1 ዓመት በላይ በመጠለያ ጣብያ የቆዩ ተፈናቃዮች የሚገኙ ሲሆን እስከአሁን ድረስ የደብረብርሃን ከተማ ህዝብና ከአንዳንድ ድርጅቶች ውጭ መንግስት ተገቢውን ድጋፍ እያደረገላቸው ባለመሆኑ ለችግር በመጋለጣቸውን ተፈናቅዮች ቅሬታቸውን ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል። በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት የተፈናቃዮች አስተባባሪ አቶ አንተነህ ገብረእግዚአብሄር በተለይ ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፁት በከተማዋ ከሰዎች ተጠግተውና ቤት ተከራይተው የሚኖሩትን ሳይጨምር ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ በ6 መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች … [Read more...] about “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል
ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል
በጦር መሳሪያ በመታገዝ በተለያዩ ቦታዎች እየተንቀሳቀሱ የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 4 ግለሰቦች ከ20 ዓመት እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ተስፋዬ ጌታቸው፣ ተገኝ ሞቲ፣ ባይሳ ተስፋዬ እና አዱኛ ኦልጅራ የተባሉት ተከሳሾች በቡድን ተደራጅተው በለሊት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች እየተንቀሳቀሱ በጦር መሳሪያ የታገዘ የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ተከሳሾቹ በተደጋጋሚ ጊዜ በፈፀሙት በጦር መሳሪያ የታገዘ የዘረፋ ወንጀል መዝገብ ተደራጅቶባቸውና አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸው ጉዳያቸውን ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ጌታቸው በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት፣ 2ኛ ተከሳሽ ተገኝ ሞቲ በ23 አመት ፅኑ እስራት እንዲሁም … [Read more...] about ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል
የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ
የሀገሪቱ ም/ፕሬዝዳንትና ጠ/ሚኒስትርን ጨምሮ 10 ከፍተኛ ባለስልጣናት የተሰረቀውን ቆርቆሮ ወስደዋል ተብሏል። የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር ጎሬቲ ኪቱቱ ከቤት ክዳን ቆርቆሮ ዝርፊያ ቅሌት ጋር በተያያዘ ፋሲካን በእስር ቤት ያሳልፋሉ። ሚኒስትሯ ለእስር የተዳረጉት በሀገሪቱ የተፈፀመው የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች ዝርፊያ ላይ ተሳትፈዋል በሚል እንደሆነ ቢቢሲ አስነብቧል። የክልሎች ሚኒስትር ጎሬቲ ኪቱቱ በኡጋንዳ ሰሜን ምስራቅ ክልል ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች የተዘጋጀውን 14 ሺህ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል ነው የተጠረጠሩት። ሚኒስትሯ ባሳለፍነው አርብ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ እስካሁን የጥፋተኝነት ውሳኔ ባሳያልፍባቸውም የዋስትና መብት ግን ከልክሏቸዋል። 10 የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የተሰረቀውን የቤት ክዳን ቆርቆሮ … [Read more...] about የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ
ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው
በማዕድን ዘርፍ ለማልማት ፈቃድ ከወሰዱ 250 መካከል እየሠሩ ያሉት 8% ብቻ ናቸው ብዙ ሃሜታ የሚነሳበትን የመዐድን ሚኒስቴርን ሲመራ የነበረው ታከለ ዑማ በበርካታ የሌብነት ወንጀል ብዙ ሲባለበት ቢቆይም አገር ለቅቆ መውጣቱ ይታወቃል። የእርሱን ከአገር መልቀቅ ተከትሎ ከመዐድን ሚኒስቴር አካባቢ የሚሰሙት መረጃዎች መሥሪያ ቤቱ ምን ያህል ሲመዘበር እንደቆየ አመላካች ሆኗል። የተያዙት ግለሰቦችም ስለዚህ ጉዳይና እስከ መንግሥት መዋቅር ስለ ዘለቀውን የሌብነት መስተጋብርም የሚሉት ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል። በየቤኒሻንጉል ጉሙዝ በማዕድን ልማት ለመሰማራት ፈቃድ ከወሰዱ ከ250 በላይ አልሚዎች መካከል ወደ ሥራ የገቡት 20 ብቻ እንደሆኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ በሕገ ወጥ መንገድ ወርቅ ሲያዘዋውሩ የተገኙ 45 የውጭ አገራት ዜጎች … [Read more...] about ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው
አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ
በአዲስ አበባ፣ በባህርዳር፣ በአዳማና በድሬዳዋ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችን ኢላማ ያደረገ ጥቃቶች በመፈጸም ሀገራዊ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረሐይል አስታወቀ፡፡ የጋራ ግብረ ሐይሉ ለመገናኛ ብዙኅን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአማራና በሌሎች ክልሎች ውስጥ መቀመጫቸውን ያደረጉ እንዲሁም አዲስ አበባ ጭምር የሚገኙ ምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶችን ያካተተ ህቡዕ መዋቅር በምስጢር ሲንቀሳቀስ እንደነበር ተደርሶበታል። ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው፣ ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያበይን፣ ዶ/ር መሰረት፣ ወርቁ ተስፋዬ ወ/ማርያም፣ ተስፋዬ የኋላሸት ፋሲል፣ ሰለሞን ልመንህ ከተማና መንበረ የተባሉ ግለሠቦችም በህቡዕ አደረጃጀቱ ሲሳተፉና ሲያስተባብሩ በቁጥጥር ስር … [Read more...] about አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ
በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል
በ10 ዓመቱ ወደ ውጪ ሸሽቷል የተባለው ሀብት ከባለፈው 44 ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ10 ዓመቱ እንደሚበልጥ የጥናት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ለሸገር ነግረዋል፡፡ በጉዳዩ የማክሮ ኢኮኖሚ ተንታኝና ተመራማሪው ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ከሸገር ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፦በኢትዮጵያ በ10 ዓመት ውስጥ ብቻ 45 ቢሊየን ዶላር ከሀገር መውጣቱን ገልጸው ይህም የ10 ዓመቱን ወደ ውጪ የሸሸ ኃብት ከባለፈው 44 ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ10 ዓመቱ እንደሚበልጥ ተነግረዋል። የማክሮ ኢኮኖሚ ተመራማሪው በ44 ዓመት ውስጥ ከኢትዮጵያ የሸሸው ሀብት 31 ቢሊየን ዶላር ነው የተባለ ሲሆን፣ ይህም በጥናት ተረጋግጦ መታተሙን አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም በከተማው ውስጥ ከመደበኛው ሥርዓት ውጪም ከፍተኛ ዶላር እንደሚገላበጥ አስረድተዋል። ለመሆኑ ዋናው ምክንያት … [Read more...] about በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል
አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም
የቀረቡ ጥያቄዎች በጥቅሉ፤ ከኦነግ ሸኔ፣ከአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ፣ከሰሜኑ የሰላም ስምምነት፣ከዜጎች መፈናቀልና ግድያ፣ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ዜጎች፣አርሶ አደሩ ምርቱን ለመሸጥ ከመቸገሩ ጋር በተያያዘ፣ወደ አዲስ አበባ ምርት እንዳይገባ ከመከልከሉ ጋር፣ከክልሎች የርስ በርስ መናበብ አለመቻል፣የሱዳን ወታደሮች ወረው የያዙትን የኢትዮጵያ መሬትና ያወደሟቸውን ንብረቶች የተመለከቱ ጥያቄዎች ቀርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች‼️ ሰላምና መረጋጋት* የአገራችን የሰላምና መረጋጋት አሁን ያለው ከነበርንበት የተሻለ ነው፤ወደተሟላ ሰላም ለመሄድ በጣም በርካታ ስራ ይጠበቅብናል፤ … [Read more...] about አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም
አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ
በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ ታሸጉ፤ 68 ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስነዋሪ ድርጊት እና ትውልድን በሚጎዳ ስራ ላይ የተሰማሩና ሲጠቀሙ የተገኙ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳውቋል። ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ በማህበረሰቡ ተቀባይነት የሌላቸው አፀያፊ ድርጊቶች ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲፈፅሙ በመገኘታቸው ቤቶቹ መታቸጋቸው ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እና የሠላምና ፀጥታ ቢሮ በጋራ በመሆን ትላንት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ነው ህገወጥ ተግባራት ሲፈጸምባቸው የተገኙት የምሽት ቤቶች እንዲታሸጉ … [Read more...] about አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ
የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ
ሕጉ ምን ይዟል ? ማንኛውንም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ምሕጻራቸው ኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው (LGBTQ+) ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ ያደርጋል። በጸደቀው አዲሱ ሕግ መሠረት የተመሳሳይ ጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋ የረጅም ጊዜ እስር ይጠብቀዋል። የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን በጉያው ያቀፈ፣ በቤተሰብ ደረጃ ያስጠለለ፣ ወዳጃቸው የሆነ ወይም አብሯቸው ያለ ሰው “እከሌ እና እከሌ” ብሎ ለሕግ አካላት ማንነታቸውን የማጋለጥ ግዴታን በሌሎች ላይ ይጥላል። በዚህ ሕግ ልጆችን ለዚሁ ለተመሳሳይ ጸታ ያጨ ወይም ያስተላለፈ የእድሜ_ይፍታህ ፍርድ ይጸናበታል። "በተመሳሳይ ጸታ መብት" ዙርያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግንኙነቱን የሚያበረታታ ማንኛውንም የሕትመት ውጤት … [Read more...] about የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ










