የውጪና የውስጥ ደጋፊዎቹንና አይዞህ ባዮቹን፣ ለዘመናት ከኢትዮጵያ የዘረፈውን ገንዘብና የጦር መሣሪያ የተማመነው ት ህነግ በእብሪት ጦርነት ውስጥ በገባበት ወቅት የአክሱምን አየር ማረፊያ በግሬደር ማረሱ የቅርብ ጊዜ ፅታ ነው። ማሰብ የተሳነው ትህነግ ይህንን ያደረገው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና እና አየር ኃይል የአክሱምን ኤርፖርት ለጦርነቱ እንዳይጠቀሙበት በሚል የጨነገፈና ኋላቀር አስተሳሰብ ነበር። ጦርነቱ የተካሄደው ት ህነግ ፈጽሞ ባልጠበቀው፣ እነ ስዬ አብርሃ ባለቀሱበት የአየር የበላይነትና በድሮን ነበር። የአክሱም ኤርፖርት ግን ምንም ላይፈይድ ፈርሶ ቀረ፤ ሕዝቡ አሁን በውጤቱ እያማረረ ይገኛል።
በከፍተኛ ደረጃ የከተማው የንግድ እንቅስቃሴ በቱሪዝም መስህቦች ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው በአጼ ዮሃንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የደረሰው ጉዳት የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ላይ ጫና ፈጥሯል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በህወሓት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል በነበረው ጦርነት የወደመው የአክሱም ከተማ አጼ ዮሃንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ አሁንም ወደ ስራ አልተመለሰም። ከጦርነቱ አስቀድሞ ከተማዋ ከቱሪዝም ከፍተኛ ገቢ ታገኝ የነበረ ሲሆን “አሁን ግን ሁሉም ነገር ቆሟል” ሲሉ አስተያየታቸውን ለአዲስ ዘይቤ የሰጡ ነዋሪዎች።
የአክሱም ከተማ ነዋሪዎችም በስፋት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ኑሯቸውን የሚገፉት ስራ እና ሙያ ከሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ጋር የተቆራኘ በመሆኑ በአየር ማረፊያው መጎዳት በርካቶች ለከፋ የኢኮኖሚ ችግር ተጋልጠዋል።
የቀድሞ የአክሱም ከተማ የባህልና ቱሪዝም ባለሙያ አቶ ገብረመድህን ፍፁምብርሃን ለአዲስ ዘይቤ እንዳሉት “አውሮፕላን ማርፊያው ሙሉ በሙሉ በመውደሙ እና ወደ ስራ የሚመለስበት ተስፋም እስካሁን አለመታየቱ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል”።
የአውሮፕላን ማኮብኮቢያው፣ መቆጣጠርያ ጣብያው፣ የሶፍትዌር ማዕከሉ፣ የቢሮ እቃዎች እና የግቢው አጥርም ጭምር በጦርነቱ ሳቢያ እንዳልነበረ ሆኖ በመውደሙ በፍጥነት ወደ ስራ ለመመለስ አስቸጋሪ ያደርገዋል ሲሉ አቶ ገብረመድህን ያነሳሉ።
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሳይንስ መምህር የሆኑት ያፌት ታደሰ በበኩላቸው የአየር ማረፊያው መውደምን ተከትሎ በቦታው ሲሰሩ የነበሩ ሰራተኞች ወደ ሌሎች ተቋማት መዘዋወራቸውን ገልፀው ይህ መስተካከል አለበት ብለዋል።
አክሱም ከተማ በየዓመቱ እስከ 1 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ እና 30 ሺህ የሚደርሱ የውጭ ጎብኚዎች እንደአክሱም ፅዮን ያሉ ዓመታዊ ክብረ በዓሎችን ጨምሮ በአክሱም ከተማ አከባቢ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ይጎበኙ ነበር። አቶ ገብረመድህን ፍፁምብርሃን “ይህ አሁን ባለው ሁኔታ በአክሱም አይታሰብም” ይላሉ።
በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎች የንግድ እንቅስቃሴያቸው ከጎብኚዎች ጋር የተያያዘ በመሆኑ አሁን ላይ ስራቸውን አቁመው የሚገኙ ሲሆን መንግስት ችግሩን ለመፍታት ሊያስብበት ይገባል ሲሉ የባህልና ቱሪዝም ባለሙያው ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። (አዲስ ዘይቤ)
እነዚህና መሰል የጦርነቱ ቁስሎች ትህነግ ከእንግዲህ በትግራይ ምንም ዓይነት የማኅበረሰብ ድጋፍ የሌለው፣ አንቅሮ የተተፋ፣ የክፋት መገለጫ፣ ድርጅት ሆኖ ሞቱን የሚያፋጥን ይሆናል የሚሉ አስተያየቶች ጥቂት አይደሉም።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Tesfa says
“ከእነዚህም ከእነዚያም ወገን ከቶ እርቅ የሚፈልግ አንድም ሰው አልነበረም። ብቻ በየጊዜውና በየወሩ በያመቱ ሲዋጉ፤ ሲፋተኑ፤ ሲተራረድ፤ ሲተላለቁ ይኖሩ ነበር” ጦቢያ – አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ
ወያኔ በ 27 ዓመት ዘመኑ ያወደመውና በተኛበት የሰሜን እዝን አርዶ ለሶስት ያህል ጊዜ ጦርነት በአማራና በአፋር ክልሎች በመክፈት እልፎችን የገደለውና ንብረት በመዝረፍ ያወደመውን ሃይል አሁን ጉያው ውስጥ አስገብቶ እሽሩሩ የሚለው የድህነቱ መንግስት ጊንጥን ኪሱ ውስጥ እንዳስገባ አልተረዳም። ወያኔ የሰው ባህሪ የሌለው የአንድ አካባቢ ሰዎች ስብስብ ነው። እርቅን ሰላምን ጭራሽ አይፈልግም። ግን ለጊዜ መግዣ ያው እንዘጥ እንዘጥ በዚህም በዚያም ይባላል። ሲጀመር በነጭ ህሳቤ የሚመራ ማንም ሃይል ቢሆን አወዳደቁ የሮም ነው የሚሆነው። ነጩ ዓለም በይፋ የሚለፈውና በስውር የሚተበትበው መጠላልፍ ለየብቻ ናቸው። ጦርነትን የሚቆሰቁሱት ስለ ሰላም የሚሰብኩልን ናቸው። እስቲ ልብ ያለው ስለ ዪክሬንና ራሺያ በይፋ የዜና ማሰራጫቸው በኩል ሲግቱን የነበረውንና አሁን ሾልኮ በወጣው የፔንታጎን ሚስጢር ያለውን ልዪነት ይመልከት። ጥቁሩ ዓለም በራሱ አስቦ ለራሱ እስካልቆመ ድረስ በወረፋ ሲያጋድሉን እንደሚኖሩ የታወቀ ነገር ነው። ወያኔም ያን ያህል ገመና ያወረደው በአሜሪካ ቀስቃሽነትና አለሁ ባይነት ነው። አሁን በሱዳን መለዪ ለባሽ ሃይሎች የማናየው መገዳደል ወያኔና የድህነቱ መንግስት ካደረጉት ፍልሚያ ጋር ይመሳሰላል። በአንድ ሃገር ሁለት የጦር ሃይል። አይ አፍሪቃ ያለ ጠበንጃ ሃይል ነገር የማይሞላ የሚመስለን ለምን ይሆን?
ወያኔ አክሱም የአውሮጵላን ማረፊያ ጣቢያ ሲያፈርስ፤ ድልድይ ሲደረምስ፤ የትምህርት፤ የህክምና፤ የመኖሪያ ቤቶችን በእሳት ሲያጋይ አሜሪካ ትንፍሽ አላለችም፤ እንዲያውም በ CNN በኩል የለቀመውን አስከሬን ወደ ወንዝ እየጣለ ድራማ እንደሰራ ሁላችን አይተን ሰው ሞቶ እንኳን የማያርፍባት ሃገር የሃበሻ ምድር ብቻ ናት በማለት እንባችን አፍሰን ጸጥ ብለናል። በአስከሬን መነገድ። ዛሬ በትግራይ ልጆቻችን የት ናቸው ብለው የሚጠይቁ የሚደበደቡበት፤ ዛቻና ማስፈራሪያ እንዲሁም የእርዳታ እህል የሚከለከሉበት እውነታ ቁልጭ ብሎ ይታያል። የሚነግድት ግን አሁንም በዚህ ህዝብ ስም ስለ ትግራይ ብለን ነው ይህን ሁሉ የምናደርገው ይሉናል። ጌታቸው ረዳ ወፍሮ ስለሚታይ የትግራይ ህዝብን እንደ ደላው አድርገው የሚቆጥሩ ሙታኖች ናቸው። 99.9% የትግራይ ህዝብ መከራ ውስጥ ነው። አሁን እንሆ ለእርዳታ የተከማቸውን እህል ዳግመኛ ዘርፈው ስማቸው ሁሉ በአለም የዜና ማሰራጫዎች በሌብነት ይጠቀሳሉ። ግን ችግራችን ምንድን ነው? ጠለምት፤ ወልቃይት፤ ጠገዴ ገለ መሌ እያለን መገዳደላችን። ሃገሩ ሰፊ ለሁሉ የሚበቃ ሆኖ እያለ ለምን ሁልጊዜ መገዳደል አስፈለገን? መልሱ ቀላል ነው። እኛ ካልተተረማመስን እነርሱ በስልጣን መቆየት ስለማይችሉ ነው። ከበሮ እያስመታ፤ ክራር እያስከረከረ ሰውን በደመ ነፍስ አካኪ ዘራፍ እያሰኙ የአማራና የትግራይ መሪዎችን ነን የሚሉ ሁሉ ስክን ብለው ማሰብ ይኖርባቸዋል። ምድሪቱን የጉንድሾችና የአንካሶች ብቻ ለማድረግ ከሆነ ሥራችሁ እስከ አሁን የፈጸማችሁት በደል በቂ ነው። ይብቃ! የድሃ ልጆችን እየማገድ የራስ ዘመድ አዝማድን ወደ ጉያና ወደ ውጭ መላክ።
የድህነቱ መንግስት አሁን በአማራ ፋኖና በአማራ ልዪ ሃይል ላይ የሚነዛቸው ነገሮች ሁሉም እውነት ባይሆኑም እውነትነት ያላቸው ነገሮችም አሉ። በአንድ ሃገር ውስጥ ቀረጥ ሰብሳቢ መንግስት እንጂ ታጣቂ አይደለም። በአንድ ሃገር ውስጥ ኬላ ዘግቶ አታልፉም አታልፊም የሚል የሃገሪቱ መሪዎችና ባለስልጣኖች እንጂ በዚህም በዚያም ያሻውን የሚያደርግ ታጣቂ አይደለም። ግን ሁሉም ፋኖ ሽፍታ አይደለም። ሁሉም ፋኖ ዘራፊ አይደለም። ያኔ በጨነቀ ቀን ያለ ፋኖና የአማራ ልዪ ሃይል እርዳታ ዛሬ የሚፎክረው የሃገሪቱ ስራዊት ድል ባልቀናው ነበር። ከሚበላና ከሚጠጣ እንዲሁም መንገድ ከመምራትና አብሮ ከመፋለም ጀምሮ በጎኑ የተዋደቀውን ፋኖ በጥቅል ሽፍታ ብሎ መጥራትና አንገት ከሚቆርጠው የኦሮሞ ጨካኝ ስብስብ ከሸኔ ጋር ማወዳደር በእጅጉ የተጣረሰና ከእውነት የራቀ አይታ ነው። ግን ሊበሉት የፈለጉትን አሞራ ጂግራ ነው ይሉታል አይነት ስለሆነ ይህ ከመበላላቱ ፓለቲካ አንድ ሌላ ምዕራፍ ላይ እንደ ደረስን ማሳያ ነው። የልዪ ሃይሎችም መበተን ያለምንም ቅድመ ዝግጅት፤ እነርሱ ሲበተኑ የሚጠብቅ ወታደራዊ ሃይል ሳይኖር፤ በጠ/ሚሩ ዙሪያ ባሉ ጥቂት የወያኔ ዘመን ትራፊ ፓለቲከኞችና የኦሮሞ ስብስቦች የተወጠነ ድብቅ አጀንዳ ነው። በሸገር 10 ሺ ሰው ተፈናቅሎ ቤት ሁሉ እንዳይከራይ እየተደረገ ማዕድ አካፈልን ማለት መሳቂያ መሆን ነው። ሲጀመር ምድሪቱ የኢትዮጵያዊያን እንጂ የኦሮሞ የአማራ ገለመሌ የሚባል ነገር የለም። ማንም በፈለገው ሂዶ የመስራትና የመኖር መብቱ እስካልተጠበቀ ድረስ የድህነቱ መንግስት ከወያኔ ቢከፋ እንጂ የተሻለበት መንገድ አይታየኝም። ማን ነው ለኦሮሞ መሬቱ ያንተ ነው ያለው? ማን ነው ለአማራው፤ ለጉራጌው፤ ለአፋሩ ምድሪቱ ላንተ ብቻ ናት የሚለው? የእብድ ፓለቲከኞች ብቻ!
እውቁ የኮምፒውተር ሳይንቲስት Jaron Lanier “Ten arguments for deleting your social media accounts right now” በተሰኘው መጽሃፉና በሌሎችም ላይ አተኩሮ የሚነግረን የዛሬው ዓለም “እኛ የራሳችን አለመሆናችን ነው” ሰው የእቃ እቃ መጫወቻ የሆነበት ዓለም ላይ እንገኛለን። ስልጥነናል ይሉናል ግን ሴቷ ሴት አይደለሁም፤ ወንድ ወንድ አይደለሁም ጾታየን አላውቅም በሚሉ እብዶች ተከበናል። ለመኖር ራስን መሸጥ። በቀጥታና በእጅ አዙር በባርነት ቀንበር ውስጥ መሆን የእለት ተግባር ሆኗል። የራስን አስተሳሰብ እየተቀሙ፤ በአብለጭላጭ ቁሳዊ ፍቅር ታውረን የመንገዳገድ ጉዞ፤ ይህ ነው የ 21ኛው ክፍለ ዘመን ስልጣኔ። ሰው እንኳንስ የልቡን እይታ ይቅርና ቀለሙንና አጸደ አቋሙን እንኳን መለየት እየተሳነን መቷል። የአርቲፊሻል ክምር እንደ ሰርግ ቤት ኬክ፤ ቆይቶ ፍርክርክ ሊል መለጣጠፍ። አያድርስ!
ባጭሩ የወያኔን የቅርብ ጊዜ ጭካኔ ለማወቅ ” የተካደው የሰሜን ዕዝ” ጋሻዬ ጤናው የጻፈው ብቻ በቂ ይሆናል። ጡቷን ቆርጠው አንገቷን ቆርጠው ዛፍ ላይ ያንጠለጠሉት የዚያች ሴት ደም ዛሬም ይጮሃል። ግን እኮ እድሜ ለብልጽግናው መንግስት የሰሜኑ ጦር እልቂት በትክክል ለህዝብ አልተነገረም። እንዲነገርም የሚፈልጉ አይመስልም። ያው ጄ/ብርሃኑ ጅላ እንዳለው አሁን ትኩረቱ አማራ ላይ ነው። አሜሪካ የሰጣቸውም ተልኮ ይህኑ ነው። በጦርነቱ ጊዜ አሜሪካ አጥብቃ ለወያኔ ስትከራከር በጠላትነት የፈረጀችው ሁለት ሃይሎች አማራና የኤርትራ መንግስት ነበሩ፤ አሁንም ናቸው። አሁን ከኦሮሞ የፓለቲካ ሴራ ያመለጡ የሚመስላቸው ተለጣፊ ድርጅቶች ሁሉ በወረፋ ስፍራቸውን እንደሚይዙ የታወቀ ነገር ነው። የምድሪቱ ችግር እኛ ነን። ከመገዳደልና ከዘር ፓለቲካ እስካልወጣን ድረስ እየገደሉ መሞት ይቀጥላል። አሁን በሱዳን የምናየውም ከእኛው የተማሩትን ነው። ግን ለኢትዮጵያ መፈራረስና ለወያኔ መጎልበት ከግብጽና ከሱዳን የበለጠ ሴራ የሰራ ሃይል የለም። ይኸው በሰፈሩት መስፈሪያ መሰፈር አይቀርም። አምናለሁ ነገ ተነገ ወዲያ ዳግም ሱዳን ለሁለት ወይም ለሶስት ትከፈላለች። ደ/ሱዳንን አጡ አሁን ደግሞ ዳርፉርና ሌሎችም መንቀሳቀሳቸው አይቀሬ ነው። ሽራፊ ሃገር ይዞ የሚኩራራ ሁሉ ጎደሎ አካል እንዳለው ሰው ነው። የሚታይለት የጠፋ። ወያኔ በስልጣን እስካለ ድረስ በምንም ሂሳብ የትግራይ ህዝብ ሰላምና መረጋጋት አይኖረውም። የትግራይ ህዝብ ጠላት አማራም ኤርትራም አይደለም ወያኔ ራሱ እንጂ። ገና ብዙ ነገር ያፈርሳሉ። ምን አልባትም እንደ አፍጋኒስታኑ ታልባን ሞቱ አበቃላቸው ሲባል የድህነቱን መንግስት ገፍትረው ዳግመኛ አዲስ አበባ ይገቡ ይሆን? ከቆየን ቀን ያሳየናል። በቃኝ!