
በ10 ዓመቱ ወደ ውጪ ሸሽቷል የተባለው ሀብት ከባለፈው 44 ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ10 ዓመቱ እንደሚበልጥ የጥናት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ለሸገር ነግረዋል፡፡
በጉዳዩ የማክሮ ኢኮኖሚ ተንታኝና ተመራማሪው ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ከሸገር ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፦
በኢትዮጵያ በ10 ዓመት ውስጥ ብቻ 45 ቢሊየን ዶላር ከሀገር መውጣቱን ገልጸው ይህም የ10 ዓመቱን ወደ ውጪ የሸሸ ኃብት ከባለፈው 44 ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ10 ዓመቱ እንደሚበልጥ ተነግረዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ተመራማሪው በ44 ዓመት ውስጥ ከኢትዮጵያ የሸሸው ሀብት 31 ቢሊየን ዶላር ነው የተባለ ሲሆን፣ ይህም በጥናት ተረጋግጦ መታተሙን አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም በከተማው ውስጥ ከመደበኛው ሥርዓት ውጪም ከፍተኛ ዶላር እንደሚገላበጥ አስረድተዋል።
ለመሆኑ ዋናው ምክንያት ምንድነው?
ለዚህ የዶላርና የገንዘብ ፍልሰት (Capital Flight) ዋነኛው ገፊ ምክንያት በሀገር ውስጥ ያለው የደኅንነት ስሜት አለመኖር እና መንግስት በብርቱ ባለመቆጣጠሩ ነው ብለዋል።
ስለዚህ ምን መሰራት አለበት?
በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር አሁንም እንዳይሸሽ መንግስት ቀዳዳዎችን እየደፈነ ከፖሊሲ ባልተናነሰ ችግሮችን እየለየ መሰራት እንዳለበት ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የዶላር ግብይት ሥርዓት ላይ መሰረት፤ የማዕድን አካባቢዎችና የኬላ ቁጥጥር ላይ መስራት በአጠቃላይ ህግና ሥርዓት ላይ መስራት “ከኤክስፖርት የማይተናነስ [ገቢ] ሊያመጣልህ ይችላል።” ብለዋል።
የዶላር ገበያን ነጻ ማድረግ አማራጭ ነው?
ፕሮፌሰር አለማየው ገዳ ይህ አማራጭ “አጭበርባሪ ፖሊሲ” ሲሉ ይገልጹታል። “የህገወጡ ገቢያ ሁልጊዜ እንደ ጥላ ነው፤ ስትሄድበት ይሸሻሀል። ምን መረጃ ያስፈልጋል አየነው እኮ ላለፉት 4 ዓመታት፤ እንደው ጥናትም ሪሰርችም አያስፈልግም! ለምንድነው የማይቆመው? የማይቆመው … እዚያ ያለው ገቢያ በተፈጥሮው በህጋዊው ገቢያ አይስተናገድም ህጋዊውን ብጨምረው ያም ተመልሶ ይጨምራል” ሲሉ ያስረዳሉ።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply