ሙሉ በሙሉ ሸዋ፣ የኬሚሴ እንዲሁም ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ በርካታ የደቡብ ወሎ ዞን አካባቢዎች ነፃ መውጣታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍም ድሉ ቀጣይ መሆኑን አሳውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተሰራው ጠንካራ ሥራ ጠላት የዘረፈውን አራፎግና ተበታትኖ ነው የወጣው ሆኖም የጠላት ኃይልን እየተከተልን እየደመሰስነው ነው ብለዋል። እየከፈልን ያለነው መስዋዕትነት ልንደፍር ልንሰርቅና ሌሎች ወንጀሎችን ልንፈፅም ሳይሆን ኢትዮጵያን ለማዳን ነው ብለዋል። አሁን ላይ አብዛኛው የአማራ ክልልና የአፋር ክልል ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥቷል፤ ድሉ ይቀጥላል እናንተም ታሸንፋላችሁ ሲሉ የወገን ጦርን አብስረዋል። በመጨረሻም የኢትዮጵያን ሠንደቅ ለአንዲት ተወካይ እንስት ኮማንዶ በመሸለም እንዲህ አሉ፤ … [Read more...] about “ይቺን ባንዲራ ሕይወታችሁ እስካለ ጠብቋት” የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ
operation dismantle tplf
ሸዋሮቢት ከተማ በአሸባሪው ትህነግ ታጣቂዎች በቡድን የተደፈሩት እናት ራሳቸውን አጠፉ!
"መግደልም መድፈርም መብታችን ነው" – “ተገድደነው የዘመትነው” የሚሉት የትህነግ ታጣቂዎች ዕድሜያቸው 50ዎቹን ያለፈው የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዋ አዛውንት በአሸባሪው የህወሓት ታጣቂዎች በቡድን ከተደፈሩ በኋላ ራሳቸውን አጥፍተዋል። ፖሊስና የአካባቢው የዓይን እማኞች በሥፍራው ለሚገኙት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች እንደገለጹት፤ ዕድሜያቸው 50ዎቹን የተሻገረውና የሸዋሮቢት ከተማ ቀበሌ 02 ነዋሪ የነበሩት ወይዘሮ ሞሚና አህመድ (ስማቸው የተቀየረ) በአሸባሪው የህወሓት ታጣቂዎች በመደፈራቸው የልጄን ዓይን ከማይ ብለው ራሳቸውን አጥፍተዋል። ወ/ሮ ሞሚና የማገዶ እንጨት በመሸጥና እንጀራ በመጋገር የሚተዳደሩ ሲሆን፤ የ15 ዓመት ታዳጊ ልጅ እንዳላቸው የሸዋሮቢት ከተማ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሀላፊ ኮማንደር አህመድ መሐመድ ለኢፕድ ገልጸዋል። ዛሬ ትህነግን … [Read more...] about ሸዋሮቢት ከተማ በአሸባሪው ትህነግ ታጣቂዎች በቡድን የተደፈሩት እናት ራሳቸውን አጠፉ!
ቀጣይዋ ትግራይ = “ትግ-ሶቶ”
መውጫው እንደመግቢያው ቀላል አልሆነም። በትግሬ ልሂቃን እብደት፣ ማኅበራዊ መሠረታቸው ላይ የእሳት ቀለበት ሰርተዋል። በእያንዳንዱ የትግሬ ጎጆ የመከራ ዜና፣ የመርዶ መልዕክት ገብቷል። በጦርነቱ እና ከጦርነቱ ጋር ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች አራት መቶ ስድሳ ሺህ ትግሬዎች ረግፈዋል። ይህን እኔ ሳልሆን ያልኩት የሳልሳዊ ወያኔ (ሳወት) መሪ ተስፋ ኪሮስ ሳህለ ነው። ያለምንም ጥርጥር ጦርነቱ በሕዝባቸው ላይ የትውልድ ክፍተት ፈጥሯል። ምናልባትም አንድ ወንድ አምስት ሴቶችን እንዲያገባ በልዩ ሁኔታ የቤተሰብ ሕጉ ካልተሻሻለላቸው በስተቀር የትውልድ ክፍተቱን በቀላሉ አይሞሉትም። ወያኔ ራሱ በለኮሰው እሳት “እወክለዋለሁ” የሚለውን ሕዝብ የእሳት ቀለበት ውስጥ አስገብቶታል። ከዚህ ጦርነት የሚተርፍ ቢኖር እንኳ በርካታ የትግራይ ከተሞችና መንደሮች የአዛውንት እና የሕጻናት ስብስብ … [Read more...] about ቀጣይዋ ትግራይ = “ትግ-ሶቶ”
ባለፉት 3 ዓመታት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ 49%ው በዲጂታል ወያኔ የተከፈቱ ናቸው
ባለፉት 3 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ አካውንቶች ናቸው ተባለ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በወጣው መግለጫ 122,000 ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ ብሏል። ከእነዚህ የሀሰት መረጃ ከሚያሰራጩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ መሆናቸውን አጀንሲው ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪም የህውሐት ቡድን በ2013 ዓ.ም ጦርነት በከፈተበት ህዳር ወር ብቻ 17,000 የሚሆኑ ሀሰተኛ የቲዊተር አካውንቶችም በዲጂታል ወያኔ ቡድን ተከፍተው ነበር ተብሏል።የኤጀንሲው የግልጽ ምንጭ መረጃ ኦፕሬሽን ማዕከል ኃላፊ የሆኑት አቶ አሸናፊ ኃይሉ በቡድኑ በተከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች … [Read more...] about ባለፉት 3 ዓመታት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ 49%ው በዲጂታል ወያኔ የተከፈቱ ናቸው
የምስራቁና የምዕራቡ ድል በመሃል አገር ይደገማል
በምሥራቅና በምዕራብ የተገኘው ድል በመሐል ሀገር እንደሚደገም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄንን የተናገሩት በሦስተኛው ቁልፍ ግንባር ተገኝተው ከሠራዊቱ ጋር በመከሩበት ጊዜ ነው። ከሰሞኑ በሚሠሩ ኦፕሬሽኖች በወራሪው አሸባሪ የተያዙ ተጨማሪ ከተሞች ነጻ እንደሚወጡ የገለጡ ሲሆን ለወረራ የገባው አሸባሪ ምንም ነገር ይዞ እንዳይወጣ ሕዝቡ ተደራጅቶ ማስቀረት እንዳለበት ጥሪ አድርገዋል። ጠላት ፈርሷል፤ ተበትኗል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ አሁን ጠላት ያለው አማራጭ የሰረቀውን አስረክቦ እጁን መስጠት ነው ብለዋል። የሰረቀውን አስረክቦ እጁን ከሰጠ ምርኮኞችን ተከባክቦ መያዝ የጀግና ባህላችን ነው ብለዋል። ከአሸባሪው ሕወሓት ነጻ በወጡ አካባቢዎች በአስቸኳይ መስተዳድሩን በቶሎ መልሶ ማቋቋም … [Read more...] about የምስራቁና የምዕራቡ ድል በመሃል አገር ይደገማል
“ከደሙ ንጹህ ነኝ” ሲነቃ – “የሽግግሩ አመራርና አሻጋሪ” ሲዶለት – ድራማው እንደ ወረደ
ማስታወሻ እንደ መጠቆሚያ - የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግ) በሚል ስያሜ ራሱን ጠርቶ ተመሥርቶ፣ በዚሁ ስም ከበረሃ ተነስቶ አገር የመራበትና የፈጸማቸው ተግባራት በሙሉ የቅርብ፣ በዚህ ትውልድ ላይ የተፈጸመ ነው። ያለ ነጋሪና መስካሪ ይህ ትውልድ በአይን ብረቱ ያያቸው፣ በጆሮው ያደመጣቸውና በጋራ ሲመክርባቸው የነበሩ ናቸው። አሁንም ጉዱ አላለቀም። እንደውም የአሁኑ “ተያይዘን እንጥፋ ወይም ልሳፈርባችሁና ልዝረፋችሁ” የሚል መፈክር ይዞ ዘጠና አምስት መቶኛ ሕዝብ በአምስት መቶኛ አጣፍቶ ለመንገስ አልሟል። ይህ ኃይል ዛሬ የሚያወራው፣ የሚሰብከውና የሚጫወተው ከዚህ ግብሩን በደንብ ከሚያውቀውና “በቃኝ” ብሎ ካፈናጠረው ትውልድ ጋር መሆኑን ይዘነጋል። በዚህ ከሥር እንዳለ በቀረበው የትርጉም መረጃ ኤፍሬም ይስሃቅ አምላካዊ ቅባ ቅዱስ የሚቀባው የሉሲፈር ሽል ብርሃነ፣ … [Read more...] about “ከደሙ ንጹህ ነኝ” ሲነቃ – “የሽግግሩ አመራርና አሻጋሪ” ሲዶለት – ድራማው እንደ ወረደ
መንግሥት ለመገልበጥ በኤፍሬም ይስሐቅ መሪነት የተሳተፉ ክስ እንዲመሰረትባቸው ተጠየቀ
በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ ሰብሳቢነት በተመራውና በአሸባሪነት የተፈረጀውን ሕወሃት ለመደገፍ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች በአሜሪካ ክገር ምርመራ ተካሂዶ ክስ እንዲመሰረትባቸው ተጠይቋል። ህወሃትን ለመደገፍና በህዝብ የተመረጠን መንግስት ከስልጣን ለማውረድ በተጠራው ስብሰባ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች ምርመራ እንዲካድባቸውና ክስ እንዲመሰረትባቸው የጠየቁት በአሜሪካ አገር ያሉ አራት የትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ናቸው። ብርሃኔ ገብረክርስቶስ፣ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ፣ ዶ/ር እሌኒ ገ/መድህን፣ በቀለ ገለታ፣ ዶ/ር ታደሰ ውሂብ ፣ ኩላሂ ጃለታ፣ ዶናልድ ይማማቶን ጨምሮ 14 ግለሰቦች ናቸው በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ ምርመራ ተደርጎባቸው ክስ እንዲመሰረትባቸው የተጠየቀባቸው። ግሰለቦቹ እንዲከሰሱ የሚጠይቀውን ማመልከቻ ድርጅቶቹ ለአሜሪካ ጠቅላይ … [Read more...] about መንግሥት ለመገልበጥ በኤፍሬም ይስሐቅ መሪነት የተሳተፉ ክስ እንዲመሰረትባቸው ተጠየቀ
በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ “ቀዩ ዘንዶ ግብረኃይል” ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅቡቲ ይጓዛል
ከሁለት ጠቅላይ ግዛቶች የተውጣጡ አንድ ሺህ ወታደሮች ያካተተ “ግብረኃይል” ከአንድ ወር ተኩል በኋላ ወደ አፍሪካ ቀንድ እንደምታዘምት አሜሪካ አስታወቀች። ግብረኃይሉ "ቀዩ ዘንዶ" በሚል ስያሜ የሚጠራ ሲሆን በዜናው ጦሩ "ወደ ኢትዮጵያ ይሄዳል" በሚል የተነሳ ጉዳይ የለም። የተሰጠውም ተልዕኮ ለአፍሪቃ ቀንድ ግብረኃይል ተጨማሪ ድጋፍ ለመስጠት ነው ተብሏል። ቅዳሜ ኅዳር 18፤ 2014 ዓም (ኖቬምበር 28፤ 2021) በተካሄደ ሥነሥርዓት ከ800 በላይ የሚሆኑ የቨርጂኒያ ግዛት ብሔራዊ አባላት ዘብ የተሸኙ ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ የኬንታኪ ግዛት ብሔራዊ ዘብ አባላት እንዲሁ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡ ይህ ከአሜሪካ የተላከው ግብረኃይል በምስራቅ አፍሪካዊቷ ጅቡቲ ከተቀመጠው የአፍሪካ ቀንድ ጥምር ግብረኃይል ጋር የሚቀላቀል … [Read more...] about በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ “ቀዩ ዘንዶ ግብረኃይል” ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅቡቲ ይጓዛል
የተለያዩ ሀገራትን የገንዘብ ኖቶች ለማባዛት በዝግጅት ላይ የነበሩ የዉጭ ሀገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አንድ ካሜሩናዊ እና አንድ ኮቲዲቫራዊ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አማዶ ፔንሲኦን ውስጥ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አዲስ ብራይት ፔንሲኦን ውስጥ ነዉ የኢትዮጵያና የተለያዪ ሀገራት የገንዘብ ኖቶችን በማዘጋጀት ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡ የግለሰቦቹን ህገወጥ እንቅስቃሴ ሲከታተል የነበረዉ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተጠርጣሪዎቹን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥቆማ በመስጠት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሲዉሉ 107,330 ትክክለኛ የኢትዮጵያ ብሮች ፣ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ባለ 200 በርካታ ፎርጅድ የኢትዮጵያ ብሮች፣ ዱቄት መሳይ ኬሚካል፣ ፈሳሽ ኬሚካሎች፣ ከተር ወይም የወረቀት መቁረጫ፣ … [Read more...] about የተለያዩ ሀገራትን የገንዘብ ኖቶች ለማባዛት በዝግጅት ላይ የነበሩ የዉጭ ሀገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
“ሀገርን ማክበር የሚለው ሀሳብ የሚጀምረው የሀገርን ህግ ከማክበር ነው” – ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ያወጣውን ክልከላ የሚተላለፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ መንግስት አሳሰበ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ከቀናት በፊት፦ "ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችን እና ውጤቶችን በተመለከተ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ፣ በየትኛውም የመገናኛ አውታር መስጠትና ማሰራጨት ክልክል ነው። በየግንባሩ የሚገኙ የሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ከተሰጣቸው ሥምሪትና ተልእኮ ውጭ ማንኛውንም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችን እንዲሁም ውጤቶችን የሚመለከቱ መግለጫዎች መስጠት የተከለከለ ነው። የጸጥታ አካላትም ይሄን ተላልለፈው በሚገኙት ላይ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ታዟል። " የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል። በዛሬው ዕለት መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ መንግስት … [Read more...] about “ሀገርን ማክበር የሚለው ሀሳብ የሚጀምረው የሀገርን ህግ ከማክበር ነው” – ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ










