• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የምስራቁና የምዕራቡ ድል በመሃል አገር ይደገማል

December 2, 2021 10:40 am by Editor 1 Comment

በምሥራቅና በምዕራብ የተገኘው ድል በመሐል ሀገር እንደሚደገም  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄንን የተናገሩት በሦስተኛው ቁልፍ ግንባር ተገኝተው ከሠራዊቱ ጋር በመከሩበት ጊዜ ነው። 

ከሰሞኑ በሚሠሩ ኦፕሬሽኖች በወራሪው አሸባሪ የተያዙ ተጨማሪ ከተሞች ነጻ እንደሚወጡ የገለጡ ሲሆን ለወረራ የገባው አሸባሪ ምንም ነገር ይዞ እንዳይወጣ ሕዝቡ ተደራጅቶ ማስቀረት እንዳለበት ጥሪ አድርገዋል። 

ጠላት ፈርሷል፤ ተበትኗል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ አሁን ጠላት ያለው አማራጭ የሰረቀውን አስረክቦ እጁን መስጠት ነው ብለዋል።

 የሰረቀውን አስረክቦ እጁን ከሰጠ ምርኮኞችን ተከባክቦ መያዝ የጀግና ባህላችን ነው ብለዋል።

ከአሸባሪው ሕወሓት ነጻ በወጡ አካባቢዎች በአስቸኳይ መስተዳድሩን በቶሎ መልሶ ማቋቋም እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነዋል። ወታደሩ በከፍተኛ ሞራል ላይ ነው ሲሉም የወገን ኃይል ያለበትን ገልጠዋል።

 ሕዝቡ እስካሁን ላደረገው ተሳትፎ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን አንድነታችን የተጠበቀ ይሁን፤ የአሉባልታ ወሬ ወጀብ አይውሰደን፤ አንድ ሆነን የማትደፈር ሀገር ለልጆቻችን እናስረክብ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልእክት አስተላልፈዋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    December 2, 2021 02:32 pm at 2:32 pm

    ይገርማል። ሰው ረጋ ብሎ የሃገራችን የኋላ ታሪክ ለመዘነ ይበልጡ የሽብርና የመገዳደል ታሪክ ነው። ይህን የተረዱ ይመስለኛል የቀድሞው መሪ ኮ/መንግሥቱ ሃ/ማሪያም እንዲህ በማለት አንድ ወቅት ላይ የተናዘዙት። ” አያቴ ሰላምን አያውቅም፤ አባቴ ሰላምን አያውቅም፤ እኔ ሰላምን አላውቅም፡፤ ምን አልባትም ልጆቼ” በማለት ምጽአታዊ እይታቸውን የተናገሩት። ይሁን እንጂ ሞልቶ የሚፈስን ግፍ ለመታገል የሚደረገው የሞት ሽረት ውጊያ አማራጭ የሌለው ነው። የወያኔን ግፍ ሰው ሁሉ አሁን ስለነቃበት በቀረርቶ፤ በዘፈን፤ በግጥም፤ በጽሁፍ፤ በድራማና በሌሎችም ልዪ ልዪ መንገዶች እየተጋፈጡት ይገኛል። የከተማውን ልተውና በገጠር ከተባሉ ጥቂት ስንኞች ላካፍላችሁ።
    ግርምም ይለኛል ድንቅ ያደርገኛል ያሰብኩት እንድሆን
    ሰው በገዛ ሃገሩ ተፈናቃይ ሲሆን።
    ሌላው የወያኔን ዘራፊነት ለማሳየት
    መጫን ቢቻል ኑሮ ውሃን በመኪና መቀሌ በገቡ አባይና ጣና።
    ታዲያ በዚህና በዚያም የፓለቲካ ግርግር ውስጥ ሚዛናዊ ሆኖ ዘርና ቋንቋን ወይም ሃይማኖትን ተገን ሳያረጉ ሰው ለሆነ ሁሉ ሰው ሆኖ መቆም እየከበደ ሂዷል። ዝተት ሃሳብ ይዘው የሚወላገድትን ከነሸክማቸው በመተው በእውነት ለሃገር እናስባለን የሚሉትም ቢሆኑ የሚያሰሟቸው አንዳንድ ድምጾች ከእውነት የራቁና አክራሪነት የታከለባቸው ናቸው። ዝንተ ዓለም ንገስ በሚል ህብረተሰብ መካከል ተወልደን ሰው ዘላለማዊ እንዳለሆነ መረዳት ይከብደናል መሰል የመሪ አምልኮ እናበዛለን። አሁን ህልም አየሁ፤ ትንቢት መጣልኝ፤ ከፈጣሪ ትላንት የተቀበልኩት ራዕይ ይህ ነው እያሉ ጠ/ሚሩን ቋሚ ሃውልት አስመስለው የሚያገዝፉ ሁሉ ቱልቱላዎች ናቸው። ጠ/ሚሩ ስጋና ደም ያለው እንደ እኛ ሰው ነው። ይሳሳታል፤ በጎና መልካም ነገርም ያደርጋል። እነዚህ የነገን ዛሬ ላይ ቆመን እናውቃለን የሚሉት አጭበርባሪዎች እንኳን የነገን ይቅርና ጧት ላይ የበሉት ቁርስ እንኳን ተረስቷቸዋል። ዝም ቢሉ እንዴት ይመረጥ ነበር። ለዚህ ማስረጃው በዋይት ሃውስ ነብይት ብርቱካን ከያኔው ፕሬዚደንት ትራምፕ ጋር ያደረገቸው የጸሎትና የወደፊት አመላካች ነገር ዋና ማሳያ ነው። አንድም አልሰመረም።
    አሁን እንሆ ራሳቸው በለኮሱት የመከራ እሳት የሚለበለቡት የወያኔ ወራሪ ሃይሎች ይህ ሁሉ ክፋት ከመድረሱ በፊት ተው ተብለው አልመከረም በማለታቸው የደረሰ የጋራ የመከራ ዶፍ ነው የሚወርድብን። አንዲት በመንግስት ተማረከች የተባለች የ 14 ዓመት ልጅ በግድ ነው ከቤት የወሰድኝ ስትል ጋዜጠኛው እናትሽ ምን አለች ሲሏት አለቀሰች ነው ያለቸው። ወያኔ ለትግራይ ህዝብ ከፍታ ቆሟል ብለው የሚያምኑ የትግራይ ልጆች እብዶች ናቸው የምለው ለዚህ ነው። የትግራይ እናቶችና አባቶች እንባ የአፋርና የአማራ እናቶችና አባቶች ከሚያነቡት እንባ አይለይም። ተያይዞ ማልቀስ ነው። ወይ ማን አያይዞን አይፈቀድልን፤ በርቀት በያለንበት ማንባት ነው። የእብዶች ፓለቲካ ውጤቱ እብደትን በሌላ እብድ መተካት ነው።
    አሁን በተሰመረው የፓለቲካ አሰላለፍ ላይ በጭፍን ዶ/ር አብይን የሚጠሉ ሰዎች በተለይም የፕሮቴስታን ወይም የኦርቶዶክስ አማኝ ነን የሚሉ የሚያናፍሱትን ሳነብና ስመለከት እብደታችን ጣራ መድረሱን እረዳለሁ። እኔ ማንም ምን ቢል አቶ ሽመልስም ሆነ የአዲስ አበባ ከንቲባዋ፤ ወይም ሌሎች አመራር ላይ ያሉ ኦሮሞዎች ሆን ብለው አማራን ያስገድላሉ ብዬ አላምንም። ይመስለኛል ጦርነቱ ከወያኔ ጋር ብቻ አይደለም። ከፕሮቴስታንት እምነት አጥባቂዎችና፤ የኦርቶዶክስ እምነት አክራሪዎችም ጭምር እንጂ። ሲጀመር prosperity gospel እና prosperity party አይገናኙም። በወንጌል የተሰለፉት አጭበርባሪዎችና አውሮጵላን ይገዛልኝ የሚሉ የምድር ኗሪዎች ሲሆኑ የፓለቲካው ፓርቲ ደግሞ የድሃ ቤቶችን የሚጠግን፤ ከሃገር የተፈናቀሉትን የሚረዳ፤ ሃገሩንና ወገኑን ከልባቸው ሊያገለግሉ የተነሱ የሰዎች ስብስብ ነው። በዚህ ስብስብ መካከል እሾህ አይኖርም ግን አልልም።
    በዚህ ዙሪያ ላይ ዶ/ር ደረጀን ከበደን ለማስጠንቀቅ በየሥፍራውና በተለያዪ ሰዎች የተሰጠውን አይቻለሁ፤ አንብቤአለሁ። ችግሩ ሰዎቹ የተጣሉት ከሰውዬው ጋር እንጂ ከሃሳቡ ጋር አለመሆኑ ነው። በእኔ እይታ ዶ/ር ደረጀ በጠ/ሚሩ ላይ ያለውን ጥላቻ በመረጃ ቢያቀርብ የሚሻል ይመስለኛል። ለእኔ አማራ አማራ የሚለው የአንድ ወገን እይታውና በጠ/ሚሩ ላይ ያለው አጠቃላይ አመለካከቱ አይዋጥልኝም። ለሰማይ ያደረ ሰው በዘሩና በቋንቋው አይሰለፍም። ከዚህ በላይ ግን የሚያስገርመኝ መልስ ሰጪዎቹ ናቸው። ለምሳሌ መስፍን ጉቱ ወንድ ከሆንክ ለምን እዚህ አትመጣም ብሎ ሲናገር ስሰማ እውነትም አለሙ ሁሉ ገምቷል ነው ያሰኘኝ። ቀጥሎም ከአሁን በህዋላ ጠላቶችህ እኛ ነን ሲል ደግሞ እጅግ መውረድን ያሳያል። የኬፋ፤ የሶፊያና የሌሎችንም ወንጌል ሰባኪና ሌላም ነን የሚሉትን አይቸዋለሁ። እግዚኦ ያሰኛል። ዶ/ር ደረጀ ለዘመናት ህይወትና ኑሮውን ለአገልግሎት የሰጠ፤ በሰቆቃ የኖረና ያን ያለፈ ለመሆኑ የሚያውቁት ይመሰክራሉ። አሁን በሽምግልና ዘመኑ እንዲህ በሰው ላይ መረባረብ ምን ይባላል። ግን እንኮ በዚህም በዚያም የሚንጫጫውና ሃሳቡን ሳይሆን ዶ/ር ደረጀን ለማጥቃት ያሰፈሰፈው ሁሉ ራሱን ዞር ብሎ ቢመለከት ማፈር በቻለ ነበር። ጊዜው ያስረሽ ምችው ነው። prosperity party እና prosperity gospel ልዪነት እንዳላቸው እንኳን የማይገባቸው ናቸው የሚለፈልፉብን። የብልጽግና ወንጌል ምዕመናኑን አምጡ፤ አውሮፕላን ግዙልኝ፤ ያን ካረጋችሁ ያላችሁ ይበዛል፤ በሚሉ አታላዪች የተሞላ ነው። ልብ ላለው ሁለቱ አይገናኙም። መቼ ይሆን ሰውን ከማስፈራራት፤ ከመሳደብና የሌለ ስም ከመስጠት የምንቆጠበው። አሁን ሥራዋን በመተው የወያኔን ሴራ ከዘሯ በተሻገረ እይታ አይታ ለዓለም በማሳየት ላይ ያለችው ሄርሜላ አረጋዊን መሳደብ፤ እንደበድብሻለን ዋይ እንገልሻለን፤ አልፎ ተርፎም በቤተሰብ ግፊት እይታዋ እንዲቀየር የሚሞክሩ ሁሉ የዚህ የሙታን ጥርቅም አካሎች ናቸው። በቅርቡ ጋዜጠኛው ለነበራቸው ቃለ ምልልስ ካመሰገናት በህዋላ የማንን ዘፈን ላዘፍንሽል ሲላት “የዘሩባቤል ሞላን – ምንድን ነው ዝምታሽ” በማለቷ ፈልጌ አዳመጥኩት። የገባት ልጅ መሆኗ ያኔ ደግሞ ለእኔም ገባኝ።
    በመዝጊያ መፈለግ ያለበት መፍትሄ ከዘመን ዘመን በየምክንያቱ የሚያገዳድለን ነገር እንዴት ነው መቆም ያለበት ነው። የዛሬው ድል የነገ ሌላ የጦርነት ጊዜ ነውና። እውቁ አሜሪካዊ ጄኔራል Smedley Darlington Butler – war is a racket በተሰኘው መጽሃፉ ላይ ጦርነት እንዴት የሸማቾችና የአትራፊዎች ገቢያ እንደሆነ ያሳየናል። እንዴት ሰው ሆኖ ቆሞ የሚሄድ በየመን ላይ የሚዘንበው መከራ ትምህርት አይሆነውም? እንዴት የሶማሊያ ለሶስት መከፋፈል ትምህርት አያገኝም። በነጭና በዓረብ እየተነድ እስከ መቼ ነው እንዘጥ እንዘጥ የሚለው ህዝባችን እየደማና እየተራበ? አይበቃም እብደቱ? የምስራቅና የምዕራቡ ድል በማህል ሃገርም ይደገማል? ቤቱ የተቃጠለበት አንድ ገበሬ ሥራ ውሎ ሲመጣ ቤትህ እኮ ተቃጠለ ቢሉት አይ “የቤቴ መቃጠል ለቱሃኑ በጀ” አለ ይባላል። እንዲህ ነው። የእኛ ነገር ትልቁን ቤት አፍርሰን ሜዳ ላይ ለመተኛት ያለን ናፍቆት። ኸረ ተው መገዳደል ይብቃ? አሜሪካና ጃፓን እንኳን ታርቀው በሰላም እየኖሩ አይደል እንዴ። እንዴት በፈጠራ ጥላቻ እንዲህ ሰው ይለቅ። ክራራይሶ ያሰኛል። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule