
ሙሉ በሙሉ ሸዋ፣ የኬሚሴ እንዲሁም ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ በርካታ የደቡብ ወሎ ዞን አካባቢዎች ነፃ መውጣታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍም ድሉ ቀጣይ መሆኑን አሳውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተሰራው ጠንካራ ሥራ ጠላት የዘረፈውን አራፎግና ተበታትኖ ነው የወጣው ሆኖም የጠላት ኃይልን እየተከተልን እየደመሰስነው ነው ብለዋል።

እየከፈልን ያለነው መስዋዕትነት ልንደፍር ልንሰርቅና ሌሎች ወንጀሎችን ልንፈፅም ሳይሆን ኢትዮጵያን ለማዳን ነው ብለዋል።
አሁን ላይ አብዛኛው የአማራ ክልልና የአፋር ክልል ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥቷል፤ ድሉ ይቀጥላል እናንተም ታሸንፋላችሁ ሲሉ የወገን ጦርን አብስረዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያን ሠንደቅ ለአንዲት ተወካይ እንስት ኮማንዶ በመሸለም እንዲህ አሉ፤ “የኢትዮጵያ ባንዲራ በሌቦች፣ በዘራፊዎ፣ በሽፍታዎች አይደፈርም፤ በኮማንዶዎች ይጠበቃል፤ ይቺን ባንዲራ ሕይወታችሁ እስካለ ጠብቋት”።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply