አንድ ሀገር በግዛቷ ውስጥ ማን እንደሚገባ፣ እንደሚወጣና እንደሚቆይ የመወሰን መብቷ የተጠበቀ ነው፤ የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንን ውሳኔውን ለማንም ማሳወቅ አይጠበቅበትም ሲሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ ከተልዕኳቸው ውጪ ሲንቀሳቀሱ ከአገር እንዲወጡ የተደረጉ የተመድ ሰራተኞችን በተመለከተ ለጸጥታው ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል። አምባሳደሩ በሰጡት ማብራርያ “የዛሬው ስብሰባ መነሻ ምክንያት የአንድን ሉዓላዊት ሀገር ውሳኔ የሚጋፋ የመወያያ አጀንዳ መፍጠሩ ተገቢ ካለመሆኑ በላይ ራስን በራስ በማስተዳደር በተወሰነ ውሳኔ ላይ እንዲሁም በሉዐላዊት አገር ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው” ብለዋል። በዓለም አቀፍ ህጎች መነሻነት ኢትዮጵያ ውሳኔውን መወሰኗንም አስታውቀዋል። የተለያዩ አገራት በተለያየ … [Read more...] about በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ማን እንደሚገባ፣ እንደሚወጣና እንደሚቆይ ለማንም ማሳወቅ አይጠበቅብንም
Politics
ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚደነግጡት መቼ መቼ ነው?
የኢትዮጵያ መንግስት በውስጥ ጉዳዬ ላይ ገብተዋል፣ ከተፈቀደላቸው ዓላማና ተግባር ውጭ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል ያላቸውን 7 በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ግከለሰቦችን በ72 ሰአታት ውስጥ የኢትዮጵያን ግዛት ለቀው እንዲወጡ ሲል አዟል። ይህንን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ “በኢትዮጵያ ውሳኔ ደንግጫለሁ” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ በአሸባሪው ህወሓት በርካታ ንጹሀን ሲገደሉ፣ ከ400 በላይ መኪናዎች በአሸባሪው ድርጅት ታግተው ሲቀሩ፤ አሸባሪው ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰራሁ ነው ሲል ድምጻቸውን አጥፍተው አሁን ላይ መንግስት የአገር ሉአላዊነትን በተጋፉ የድርጅቶቱ ሰራተኞች ላይ እርምጃ ሲወስድ ደንግጫለሁ ማለታቸው ተገቢነት የጎደለው ነው ሲሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ … [Read more...] about ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚደነግጡት መቼ መቼ ነው?
ለኤርሚያስ ክስ ትህነግ ወጪውን ሊሸፍን ነው
ኤርሚያስ ቃል በቃል የተናገረው ይህንን ነው፤ “ቲዲኤፍን (ስሙን የቀየረውንና በሃሺሽ ያበደውን የትህነግ ጭፍራ ማለቱ ነው) ምሳሌ ውሰዱ፤ የትግራይ ቲዲኤፍ ሕዝባዊ ኃይል ነው፤ (እነርሱ) ሳይነጋገሩ አይወስኑም፤ እንደ ቤስት ፕራክቲስ ነው የሚወሰደው፤ እደግመዋለሁ ቤስት ፕራክቲስ ነው”። ለአማራ ህዝብ እንዲተገብረው የሰጠው “ምክር” ይህንን ነው። በሌላ አነጋገር ኤርሚያስ እያለ ያለው፤ አገኘሁ ተሻገር ደብረጽዮንን፤ ጄ/ል ተፈራ ማሞ ፃድቃንን፤ ጄ/ል አዳምነህ መንግሥቴ ታደሰ ወረደን ወይም ምዕግበን፤ ግዛቸው ሙሉነህ ደግሞ ጌታቸው ረዳን መሆን አለባቸው ነው። “የህወሃት አገልጋይ” በሚል ልዩ መለያው የሚታወቅው፣ በበረከት ስምዖን አስተምህሮ ተቀርጾ የተሠራ የሚባለውና ከዚሁ ፈጣሪው ጋር ጥብቅ ትሥሥር እንደነበረው በርካታ መረጃ የሚቀርብበት ኤርሚያስ ለገሠ፤ በአበበ ገላው … [Read more...] about ለኤርሚያስ ክስ ትህነግ ወጪውን ሊሸፍን ነው
ኢትዮጵያን ለማፍረስ መስከረም 2013 በትህነግ የተዘጋጀው ሰነድ
“የትግል ልዩ ምዕራፍ እድገቶች እና የምከታችን ቀጣይ ስትራቴጂዎች፣ ስልቶች እና አቅጣጫዎች” በሚል ርዕስ ኢትዮጵያን በረቀቀ ስልት ለማፈራረስ ካልተቻለም የትህነግን ጡንቻ በማሳበጥ የመደራደር ዐቅሙን ለማጎልበት እንዲረዳ የወጣ ባለ 86 ገጽ ሰነድ እዚህ ላይ ይገኛል። “የትግል ልዩ ምዕራፍ እድገቶች እና የምከታችን ቀጣይ ስትራቴጂዎች፣ ስልቶች እና አቅጣጫዎች” Download ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ኢትዮጵያን ለማፍረስ መስከረም 2013 በትህነግ የተዘጋጀው ሰነድ
አረንጓዴ ቢጫ እና ቀዩ ሰንደቅ የአፍሪካዊያን የነጻነት ምልክት ነው
አፍሪካዊያን አያቶቻችን የደረሰባቸው ውርደት በእኛ ምድር ላይ አይደገምም ከሚሊዮኖች ደህንነት ይልቅ የግል ስልጣናቸው በሚያስጨንቃቸው ግለሰቦች በሰጡት የተሳሳተ መረጃ የተነሳ ለሚፈጠርብን ጫና አንበረከክም፤ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መስከረረም 17 ቀን 2014ዓም ግልጽ ደብዳቤ ጽፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ደብዳቤያቸው አሸባሪው ህወሓት እንደ አገር ያደረሳቸውን ግፎችና በደሎች ዘርዝረው አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ደብዳቤያቸውም ህወሓት እንደ አገር በፈጸማቸው ግፎችና ወንጀሎች የተነሳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ቡድን ብሎ እንደፈረጀው በማስታወስ፤ ይህ ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈጸም በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት መጀመሩን ጠቅሰዋል። ከዚህ ጦርነት በኋላም ይህ አሸባሪ ቡድን በአፋር … [Read more...] about አረንጓዴ ቢጫ እና ቀዩ ሰንደቅ የአፍሪካዊያን የነጻነት ምልክት ነው
ልደቱ ትህነግን ለማዳን ጥሪ አቀረበ፤ አማራ የኅልውና ችግር አልገጠመውም
“አማራውም ሆነ አፋሩ ምንም ዓይነት የኅልውና አደጋ አላጋጠመውም፤ ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም በትህነግ የደረሰበት ችግር የለም፤ አማራውም ሆነ አፋሩ በትህነግ በጅምላ አልተጨፈጨፈም፤ ማይካድራ፣ ጭና፣ አጋምሳ፣ ጋሊኮማ፣ ወዘተ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተፈጸመ ጭፍጨፋ ነው እንጂ በዲሲፒሊን የታነጸው ትህነግ እንዲህ ዓይነት ግፍ አይፈጽምም፣ በአጠቃላይ “ሒሳብ እናወራርድብሃለን” የተባለው የአማራው ሕዝብ በትህነግ ምንም ግፍ አልደረሰበትም፤ ወልቃይት የምዕራብ ትግራይ አካል ነው፣ ራያም የትግራይ ነው፤ ወዘተ። ስለዚህ ትህነግ ሳትሞት በሽግግር መንግሥት ምሥረታ የአፍ ለአፍ ትንፋሽ እንስጣትና እንታደጋት”።ልደቱ አያሌው ትህነግ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ሲገባ ለመታደግ ከሚረባረቡት “ቅምጥ” ቡድኖች መካከል በቀዳሚነት የሚሰለፈው ልደቱ አያሌው ነው። ከእርሱ ሌላ የቀድሞ የትህነግ … [Read more...] about ልደቱ ትህነግን ለማዳን ጥሪ አቀረበ፤ አማራ የኅልውና ችግር አልገጠመውም
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል መተከል ዞን ገባ
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ወደ ቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ እንደገባና አቀባበል እንደተደረገለት ቡለን ወረዳ አሳውቋል። የቡለን ወረዳ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ፥ "ለዘላቂ ሰላም የሚንቀሳቀሰው የአማራ ክልል ልዩ ሀይል በቡለን ከተማ አቀባበል ተደርጎለታል" ሲል ፅፏል። ወረዳው በአቀባበሉ ላይ የቡለን ወረዳ ወጣቶች፣ ነዋሪው፣ ማህበረስቡና የሴክተር መስርያ ቤት ሰራተኞችና አመራሩን ጨምሮ ከከተማው 1 ኪ/ሜትር ወጣ ብሎ በመሄድ አቀባበል አድርገዋል ሲል ገልጿል። የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ወደቡለን ወረዳ መግባቱ በወረዳው ያለውን የፅጥታ ችግር ለመፍታት፣ ማህበረሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ለማድረግ አስተዋጽዖ ያደርጋል ተብሏል። ቡለን ወረዳ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ውስጥ የፀጥታ ስጋት ካለባቸው ወረዳዎች አንዱ ሲሆን በተደጋጋሚ ጊዜ … [Read more...] about የአማራ ክልል ልዩ ኃይል መተከል ዞን ገባ
CNN ትህነግን እንደ ማስረጃ ጠቅሶ የሠራው ዘገባና ያፈተለከው ቅሌት
ሲኤንኤን (CNN) “አሰቃቂው ዕይታ” የሚል ርዕስ የሰጠውን እና በሁመራ ተፈፅሟል ያለውን ግርፋት፣ ጅምላ እስር እና ግድያን በተመለከተ የምርመራ ዘገባ አቅርቧል። እነዚህ ግርፋት፣ ጅምላ እስር እና ግድያ የተፈፀሙት “በኢትዮጵያ ሠራዊት እና አጋሮቹ” ሲል በገለጻቸው ኃይሎች መሆኑንም ምስክሮቹን ጠቅሶ ደምድሟል። የዚህ የምርመራ ዘገባ መነሻ የሆነው በሱዳን ድንበር አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ላይ የሚንሳፈፉ አስከሬኖች ዳግም መገኘታቸው እንደሆነ ሚዲያው ጠቅሷል። ኒማ ኤልባጊር ይሁን እንጂ የዘገባው አዘጋጅ የሆነችው ሱዳናዊቷ ጋዜጠኛ ኒማ ኤልባጊር ለምስክርነት የመረጠቻቸው ሰዎች ገለልተኛ አለመሆን እና የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ደጋፊዎች መሆናቸው የዘገባውን ተዓማኒነት አጠያያቂ አድርጎታል። በተለይ ተፈፅመዋል የተባሉትን ግድያዎች በዝርዝር የሚናገረው እና የሞቱ ሰዎች … [Read more...] about CNN ትህነግን እንደ ማስረጃ ጠቅሶ የሠራው ዘገባና ያፈተለከው ቅሌት
ልዩ ልዩ የጦርነት ጀብዱዎችና የትህነግ ግፍ
የአፋር ክልል ልዩ ሀይል አባል የሆነው ሁመድ አሊ የአፋር ክልልን ለመውረር የመጡ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎችን ሲፋለም ጥይት በመጨረሱ በታጠቀው ጊሌ ታንክ የማረከ ጀግና ወጣት ነው! ህጻናት የታቀፉ ወላጆችን በግፍ የረሸነው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ህጻን አማን እና ወንድሞቹን ያለወላጅ አስቀርቷል። ህጻና አማን በእናትና አባቱ አስከሬን መካከል በደም ተነክሮ ነው የተገኘው። የእናቱን ሞት አይቷል። የወላጅ እናቱን አስከሬን ታቅፎ ተገኝቷል። ይህ የጭካኔ ጥግ ሂሳብ እናወራርዳለን በሚል የአሸባሪው ቡድን አመራሮች ተናግረው በአማራ ክልል ወረራ ከፈጸሙ በኋላ የፈጸሙት የሽብር ተግባር ነው። "ኢትዮጵያዊያን እያለን አሸባሪው ህወሓት እንጂ አገር አትፈርስም"፦ ዘማቹ ረዳት ፕሮፌሰር የሕልውና ዘመቻ ጥሪውን ተቀብለው በግንባር የሚገኙት ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት … [Read more...] about ልዩ ልዩ የጦርነት ጀብዱዎችና የትህነግ ግፍ
የዳያስፖራ ትህነጎች ቀጣይ አጀንዳ
የትግራይ ዲያስፖራ የሳይበር ቡድን (Diaspora Cyber Team) ትላንት (Sep 5) ስብሰባ ነበራቸው።የእኛ ሰዎችም የሳይበር ውይይታቸውን ሰብረው በመግባት ታድመው ወጥተዋል። አጀንዳዎቹ:- 1- አለም አቀፍ ጫናዎችን በድጋሜ በአዲስ መልክ እንዴት እንፍጠር? 2- ትግራይ ውስጥ ቤተሰቦቻችን በርሃብ እያለቁ ነው። ለዚህስ መፍትሄው ምንድነው? 3- ህወሓት/የትግራይ መንግስት ምን ማድረግ አለበት? የሚሉ ናቸው። የተስማሙባቸው ነጥቦች:- 1ኛ) ጦርነቱ ትግራይ መሬት ላይ በነበረበት ወቅት ተዘረፍን ፣ ሴቶች ተደፈሩ ፣ በጅምላ ተገደልን ... ብለን የአለም አቀፍ መንግስታት ጫና እንዲፈጥሩ አድርገናል። አሁን ያንን መንገድ መከተል አዋጭ ስላልሆነ 5.2 ሚሊዮን ህዝብ በርሃብ እየተጎዳና እየሞተ እንደሆነ ፣ ወደ ትግራይ እየገባ ያለው የእርዳታ እህልም እጅግ … [Read more...] about የዳያስፖራ ትህነጎች ቀጣይ አጀንዳ










