
ሲኤንኤን (CNN) “አሰቃቂው ዕይታ” የሚል ርዕስ የሰጠውን እና በሁመራ ተፈፅሟል ያለውን ግርፋት፣ ጅምላ እስር እና ግድያን በተመለከተ የምርመራ ዘገባ አቅርቧል።
እነዚህ ግርፋት፣ ጅምላ እስር እና ግድያ የተፈፀሙት “በኢትዮጵያ ሠራዊት እና አጋሮቹ” ሲል በገለጻቸው ኃይሎች መሆኑንም ምስክሮቹን ጠቅሶ ደምድሟል።
የዚህ የምርመራ ዘገባ መነሻ የሆነው በሱዳን ድንበር አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ላይ የሚንሳፈፉ አስከሬኖች ዳግም መገኘታቸው እንደሆነ ሚዲያው ጠቅሷል።

ይሁን እንጂ የዘገባው አዘጋጅ የሆነችው ሱዳናዊቷ ጋዜጠኛ ኒማ ኤልባጊር ለምስክርነት የመረጠቻቸው ሰዎች ገለልተኛ አለመሆን እና የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ደጋፊዎች መሆናቸው የዘገባውን ተዓማኒነት አጠያያቂ አድርጎታል።
በተለይ ተፈፅመዋል የተባሉትን ግድያዎች በዝርዝር የሚናገረው እና የሞቱ ሰዎች አስከሬን ያለበትን ቦታ አንድ በአንድ የሚመራው ‘ገሬ’ የተባለ ግለሰብ የአሸባሪው ቡድን ደጋፊ መሆኑን በገሃድ አሳይቷል።
ግልሰቡ ከፊት በኩል “ለካቲት 11” (ህወሓት የተመሠረተበትን ቀን የሚጠቁም) ከኋላ በኩል ደግሞ “ወይንቕንቕ” (የአሸባሪው ህወሓት አይበገሬነትን የሚገልጽ) ጽሑፍ ያለበትን ኮፊያ አድርጓል።
‘ገሬ’ ለበርካታ ዓመታት ኑሮውን በሱዳን ያደረገ የትግራይ ተወላጅ እና ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የሚሰደዱ የትግራይ ተወላጆችን የሚቀበል መሆኑን ጋዜጠኛ ኒማ ገልጻለች።
ይህ ሰው ኑሮውን በሱዳን ካደረገ መቆዩቱን የምትገልጸው ጋዜጠኛዋ፣ “ሁመራ ውስጥ በኢትዮጵያ ወታደሮች እና አጋሮች ተፈፅሟል” ላለችው ግርፋት፣ ጅምላ እስር እና ግድያ ምስክር አድርጋ ያቀረበችበት አመክንዮ ለማንም ግልጽ አይደለም።
ሌላኛው አስከሬን በጫነች ጀልባ ላይ ከጋዜጠኛዋ እና ሌሎች ምስክሮች ጋር የሚታየው ግለሰብ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂ መሆኑን ካደረገው ኮፊያ መረዳት ይቻላል።
ቀድሞውኑ መንግሥትን ለመፈረጅ የሌለ ምክንያት እየፈጠሩ ክሶችን የሚያቀርቡ ወገኖችን ሰብስቦ ለእንደዚህ ዓይነቱ ከፍተኛ ውንጀላ የተሞላበት ዘገባ በምስክርነት ማቅረብ የሲኤንኤንን አቅጣጫ አመላካች ነው።
ሲኤንኤን እስካሁን በገለልተኛ አካል ያልተረጋገጠውን “የሁመራ ጭፍጨፋን” በተደጋጋሚ ሲያራግብ፣ የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጭምር እያጣራው ስለሚገኘው የማይካድራ ጭፍጨፋ እስካሁን ትኩረት ሲሰጠው አይታይም።
ከማይካድራ ጭፍጨፋ በተጨማሪ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች በአፋር ክልል ጋሊኮማ ስደተኞች ጣቢያ ላይ ስለፈፀሙት አረመኔያዊ ድርጊት ትንፍሽ አላለም።
በቅርቡ እንኳ በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ጭና ቀበሌ የተፈፀመውን እና ከ200 በላይ ሰዎች የተጨፈጨፉበትን ድርጊት በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲዘግቡት ሲኤንኤን ጉዳዬ አላለውም።
በዚህ ሐቅን በረሳው ዘገባው ሲኤንኤን በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳደር ሞክሯል።
ነገር ግን ይህ ሙከራው ከአንድ ሚዲያ የሚጠበቀውን የጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባርን የጣሰ መሆኑን በግልጽ ያመላከተ ነው። (ኢቢሲ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ኒማ ኤልባጊር በሱዳንና በግብጽ የተገዛች ከእውነት የራቁ ወሬዎችን ለCNN በማቀብለ የምትታወቅ ቅጥረኛ ሾተላይ ናት። የሚያሳዝነው ግን የዜና አውታሩ ይህን ወሬ ሳያጣራ ማናፈሱ ነው። አልፎ ተርፎም የእንግሊዙ ባርላማ እውነት ነው ብሎ ማመኑ ይባስ የድንቁርናቸው ጥግ ያሳያል። በመሰረቱ የወያኔ ዓላማ በውሸት ላይ ተመርኩዞ የአለምን እይታ መሳብ ነው። ግፍ እየሰሩ ግፍ ተሰራብኝ ማለት። ማንም ነጭ ማንም አረብ የፈለገውን ይበል የኢትዮጵያ ህዝብ በትግራይ ወራሪዎች ላይ ገሃድ የወጣውን ጭካኔና ገመናቸውን ተረድቷል። በዘር የሰከረው ይህ ስብስብ በገባባቸው የወሎ፤ የጎንደር፤ የአፋር መንደሮች ላይ ያደረሰው ጥፋት ሆን ተብሎ ሰውን ለማስራብና ለመከራ ለማጋለጥ የተደረገ ድርጊት ለመሆኑ እልፍ ነው ማስረጃው። ግን ወያኔ ከጦር ሜዳ የሞቱበትን ሰብስቦ ወንዝ ላይ እያሰረ በመጣል ሬሳ መጣ ካሜራ ይዛችሁ ጠብቁ በማለት ለሱዳናዊያን በመንገር ይህን የመሰለ ሸርና ሴራ በሙታን ላይ መፈጸሙ ከሰው ባህሪ የወጣ የፍጥረት አተላ ቡድን እንደሆነ ያስረግጣል። የወያኔን ክፋትና ሴራ ቀስ በቀስም ቢሆን አፍሪቃዊያንና ሌሎችም የዓለም ህዝቦች እየተረድት ነው። የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጸመብኝ ይላል ይህ ሰው በላ ቡድን። እውነቱ ግን ከዘመናት በፊት ጀምሮ ዘር አጥፊ የሆነው ድርጅት የትግራዪ ወያኔ ሃርነት (ባርነት) ነው። ተንኮላቸው ጤነኛ የሆነ ሰው ከሚያስበው የከፋ በመሆኑ ረጋ ተብሎ ካልተጤነ በቀላሉ ለማየት ያስቸግራል። ይህ የሃገርና የህዝብ ነቀርሳ ቡድን በትግራይ መሬት እስካለ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም አያገኝም። ይህን ለማድረግ መታጠቅ፤ መደራጀትና ወራሪን መመከት ቀዳሚ ተግባር ይሆናል። መንግስት ይደርስልኛል ብሎ እጅና እግርን አጣጥፎ ከመቀመጥ ሴትም ወንድም ስልጠና ወስዶ በተቻለ መጠን ወያኔን ተጋፍጦ ራስንና ሃገርን ማዳን ወሳኝ ነው። ወያኔ ጦርነት ከእኔ በላይ ላሳር ነው ስለሚል የሚገባው ቋንቋ እሳትን በእሳት መከላከል ብቻ ነው። ወያኔ ይምረኛል ብሎ ማሰብ ከአንበሳ ጋር ተኝቶ አልበላም እንደማለት ነው። ሲርበው ይጎረድምሃል። ወያኔም አራዊት ነው። በአፋርና በአማራ ህዝብ ላይ የሰራውንና የሚሰራውን ማየት በቂ ነው።
ሱዳናዊቷ ጋዜጠኛ ነኝ ባይ የምታስተላልፋቸውን መረጃ ቢስ ዘገባዎች ሁሉ ከአሁን በፊትም ቢሆን ተመልክቻቸዋለሁ። የፈጠራና ለም ዕራባዊያን ፍጆታ ወያኔ የሰራቸው ዘገባዎች ናቸው። በምችለው ሁሉ የነገሩን እውነተኛነት ለማመሳከርም ጥሬአለሁ። ግን የፈጠራና የወያኔ ጫወታ ወሬ እንደሆነ ብቻ ነው የተረዳኝ። እዚህ ላይ የዜና ቀባይዋም ሆነ የዜና አውታሩ ባለቤት እንግሊዞችን ጨምሮ እንደ ተሸወድ በገሃድ ማየት ይቻላል። አንድ የእንግሊዝኛ ቃል አለ ይህን ጉዳይ በደንብ ሊገልጽ የሚችል፡ ቃሉም Hoodwink ይሉታል። ነገርየው እየሆነ ያለው ወያኔ ልክ እንዳለፈው ሁሉ ሰውን የማታለል ዘይቤ ነው። ያ እማ ባይሆን አንድ ወይም ሁለት ሬሳዎችን አስቀርቶ ከታሰሩበት ገመድ ጀመሮ እስከ መልካቸው ነገሮችን በማፈላለግና በማመሳከር ወያኔ በካሚዪን ጭኖ ውሃ ላይ እያሰረ የለቀቃቸውን አስከሬኖች ማንነት ማረጋገጥ በተቻለም ነበር። ግን እኮ የማይካድራን ጭፍጨፋ የፈጸሙት ናቸው ወንዙ ላይ አስከሬን ለቃሚና ፎቶግራፍ አንሺ የነበሩት? በሰው ደም እጅ የተነከረ ሰው ለቋሚም ሆነ ለበድን ምስክር መሆን አይችልም።
ከሁሉ የሚያሳዝነው የዜና አውታሩ ግርድፍና በውሸት የተቀነባበረ ወሬ ማናፈሱ ነው። ግን እኮ ይኸው የዜና አውታር አይደል እንዴ ቀዳሜ ዜና አቅራቢ ሆኖ የኢራቅን፤ የሊቢያን፤ የሶሪያን የአፍጋኒስታንን ወሬ ሲያናፍስ የኖረው። የዚህ የዜና አውታር ታማኒነት ከመነመነ ቆይቷል። አሁን ለይቶለት የውሸት የወያኔ ፕሮፓጋንዳ አናፋሽ መሆኑ የውድቀቱን ጥግ ያሳያል። እኔ በጣም የሚያሳዝኑኝ የወያኔ ጭፍን ደጋፊዎች ናቸው። ሰው እንዴት ነገርን በራሱ አስቦና አሰላስሎ ፈትኖ እውነቱን ከፓለቲካው የውሸት ቱልቱላ አይለይም? ወያኔ ለትግራይ ህዝብ የሰራው ትላንትም ሆነ ዛሬ ምን ነገር አለ? ማን እየሞተ ማን እየኖረ ነው በትግራይ መሬት ላይ? ግን ሰው ከዘር ሰልፈኝነት ወጣ ብሎ አለምንና ከባቢውን ማየት ካልቻለ ይህ ሁሉ ነገር አይታየውም። ለዚያ ነው የትግራይ ልጆች ዛሬም ወያኔን የሙጥኝ ያሉት። የፓለቲካ ፍልስፍናና ፓለቲከኞች አላፊዎች ናቸው። 70 ዓመት የተደከመበት የሩሲያው ፓለቲካ ሲንኮታኮት አይተናል። ታዲያ እንዴት የሰው ልጅ የብልጽግናም ሆነ የወያኔን የዘር ፓለቲካ እንዴት ተገን ያደርጋል? ይህ እብደት ነው። ሰው በረጋ መንፈስ የሰው ልጆችን መብትና ነጻነት አስመልክቶ ባሩድ ሳያሸት በሃሳብ ይፋተጋል። ግን ይህ በእኛ ሃገር አልተለመደም። ንፋሱና ገደሉ ሳይቀር ጦርነት ለምዷል። አራዊቶች የሰው አስከሬን መብላት ለምደዋል። እኛም የቁም በድኖች እርስ በእርሳችን ስንጠዛጠዝ በፊት የሚያለቅሱ አይኖች ዛሬም ያለቅሳሉ። ነጩና አረቡ አለም ደግሞ እኛ ጎን የተሰለፉ መስለው በፈካው እሳት ላይ ነዳጅ ያርከፈክፋሉ። የአሜሪካና የአውሮፓ ዋና ችግር ሱማሊያ፤ ኤርትራ፤ ጅቡቲ፤ ኢትዮጵያና ሌሎችም የአፍሪቃ ሃገሮች በአንድ አስበውና አልመው የጎለበተ ሃብትና ሰላም እንዲኖራቸው አይፈልጉም። ትላንትም ዛሬም ሴራቸው ይኸውን ነው። ለወያኔ የሳተላይት ስልኮችን፤ ሌሎችም የመገናኛ አውታሮችን፤ እሳትና መድሃኒቶችን የሚያቀብሉት በእርዳታ ስም የሚገቡት የእነዚህ ሃገሮች የስለላ መረብ ሰራተኞች ናቸው። ጥቁሩ ዓለም ከተኛበት ካልነቃ ገና ያፈራርሱናል። ከ 20 ዓመት በፊት ካቡል አፍጋኒስታን ላይ ቆመው የአፍጋንስታንን ህዝብ ከታሊባን ነጻ አወጣን ያሉን አሜሪካኖች እግሬ አውጪኝ ብለው ስፍራውን ሲለቁ አፍጋኒስታን ድጋሚ በታሊባን ተይዛለች። ኦሮማይ የሚያሰኘው ይህ ነው። ዛሬ ለወያኔ ደረሰበት ለሚሉት ግፍ የሚያላዝኑት አሜሪካኖች በየመን ህዝብ ላይ በተላላኪያቸው በሳውዲ የሚያዘንቡትን የመከራ ዶፍ የሚዘግበው የለም። ፓለቲካ የቀላዋጮችና የሌቦች ስብስብ ውጤት ነው። ህዝብ ገለ መሌ ሃገር የሚባለው ሁሉ ሽፋን ነው። እውነተኛ ዲሞክራሲም በምድር ላይ የለም። ይህን የሚረዳ ሰው ለሰው ልጆች መብትና ነጻነት ይታገላል እንጂ በዘሩ ሰክሮ የፓለቲካ እግዚኦታ በነጭ ፊት ተንበርክኮ አይለምንም። በቃኝ!