• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮጵያን ለማፍረስ መስከረም 2013 በትህነግ የተዘጋጀው ሰነድ

September 26, 2021 11:13 am by Editor 1 Comment

“የትግል ልዩ ምዕራፍ እድገቶች እና የምከታችን ቀጣይ ስትራቴጂዎች፣ ስልቶች እና አቅጣጫዎች” በሚል ርዕስ ኢትዮጵያን በረቀቀ ስልት ለማፈራረስ ካልተቻለም የትህነግን ጡንቻ በማሳበጥ የመደራደር ዐቅሙን ለማጎልበት እንዲረዳ የወጣ ባለ 86 ገጽ ሰነድ እዚህ ላይ ይገኛል።

“የትግል ልዩ ምዕራፍ እድገቶች እና የምከታችን ቀጣይ ስትራቴጂዎች፣ ስልቶች እና አቅጣጫዎች” Download

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Politics Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    September 27, 2021 09:48 am at 9:48 am

    ወያኔዎች የክፋታቸው ጥግ ሰማይ ጠቀስም ቢሆን የሚደነቁ ናቸው። ይህ ሁሉ ሰነድና ዝግጅት ሲደረግ አንድም ሰው ሚስጢራቸውን አለማውጣቱ በራሱ የሚያስገርም ነው። በእርግጥ የኢሳያስ የስለላ መረብ ደርሶበት ለዶ/ር ደብረጽዪን በፊት ለፊት ተው ይህ ለጦርነት መዘጋጀታችሁ አያዋጣችሁም እንዳለው ተረድተናል። ይሁን እንጂ የሰሜን እዝ አፍንጫ ስር ነዳጅና የጦር መሳሪያ ሲያከማችሁ፤ ከማህል ሃገር የነበሩ በጡረታና በሌላም መልክ የተሰናበቱ ታጋዪችን ሲሰበስቡ አንድም የወገን ሰው አለመንቃቱ የቱን ያህል የወያኔ አሰራር የሰሜን እዝ ጦርን የራሱ ተላላኪና አራሽ ገበሬ አድርጎት እንደነበር በግልጽ ያሳያል።
    አሁን እንሆ ወያኔ የነደፈው የተባለነውን የተንኮል ጥራዝ አንብቦ ለተረዳ ከስልጣን ከተባረሩ በህዋላ ያዘጋጅት ሳይሆን ገና ቀደም ብሎ የነደፉት ለመሆኑ አመላካች ነገሮች ብዙ ናቸው። በእርግጥም ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ጊዜው አሁን ነው ማለታቸው የቱን ያህል የልብ ልብ እንደተሰማቸውና እኛ ብቻ የምስራቅ አፍሪቃ የወታደራዊ ሃይል የበላይ ነን ብለው እንደሚያምኑ በግልጽ ያሳያል። ቁም ነገሩ ትግራይ ለትግራይ በትግራይ ይበሉ እንጂ ለራሳቸው ስልጣን መራዘም የተነደፈ የፓለቲካ ሴራ ለመሆኑ የአለምን እይታና የፓከቲካ አሰላለፍ በተለይም የአፍሪቃ ሃገሮችን ድጋፍ ሰጭነትና ያለዚያም ኢትዮጵያን በመናዳችሁ አይናችሁን ላፈር መባሉን በግልጽ ያላካተተ በጅሎች ለጅሎች የተነደፈ ሰነድ እንደሆነ ልብ ያለው ያስተውላል። ግን ይህ ሁሉ እብደት መንግስት ነኝ በሚለው የዶ/ር አብይ በኩል የሚሰነዘርበትን የአልሞት ባይ ተጋዳይ ፍልሚያ ልብ ብሎ የመዘነው አይመስልም። አይ ወያኔ ሁሌ ጦርነት ከእኔ በላይ አዋቂ የለም ብሎ መደንፋት። ተራራ ያንቀጠቀጠው ትውልድ በተራሮች መካከል ተወሽቆ ሲቀጠቀጥ። አታድርስ ነው። ከዚህ ባሻገር ሰነድ ስለ ኤርትራና ኢሳያስ ዘባርቆ የዶ/ር አብይና የኢሳያስን ጥምረት ነካክቶ በጎን የሱዳን ድጋፍን አምኖ የተቀበለ የሙት ድርጅት የፓለቲካ ሰነድ ነው።
    ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል ድረስ እንጓዛለን እያለ የሚዝተው ጌታቸው ረዳ ሴኩቱሬ በመብረቃዊ ጥቃት ሁሉን ተቆጣጠርነው ብሎ እንደ ደነፋው አይነት የንፋስ ወሬ ነው። ባይገባው ነው እንጂ ጌታቸው ረዳ አሁንም የቆመበት ሥፍራ ሲኦል ነው። የስንቶችን ደም አፍሶ፤ ስንቶችን አስለቅሶና ዘርፎ ለመኖር ያወጣው ሰነድ ይኸው ህዝባችን እያየው ነው። የሚገርመው ግን የትግራይ ልጆች ከእውነት የራቀ ዝምታና በአንድ በኩል በዘርና በቋንቋ ብቻ መሰለፍ ነው። ለትግራይ ህዝብ የሚያስብና ህዝቤ ተራበብኝ የሚል ድርጅት የእርዳታ እህል እንዲያደርሱ የተላኩ ካሚዎኖችን አስቀርቶ ሾፌሮቹ ትግሉን ተቀላቅለዋል ብሎ ወሬ ያናፍሳል? ይህ እብደት አደለም የሚል ማንም የትግራይ ተወላጅ ራሱ ያበደ ብቻ ነው። ግን ወያኔ መንግስት ከሆነ በህዋላ የተወለድ የትግራይ ልጆች ወያኔ በትግራይ ህዝብ ላይ ያደረሰውን ያለፈ ገመና አያውቁም። የአሁኑን መከራ ግን እየተጋቱት ነው። ያኔ ታጋይ የነበሩትም በዘርና በቋንቋ ስለ ሰከረው ከአብሮ ከእብዶች ጋር እየተመሙ ነው። ወያኔ የትግራይን ህዝብ የራሱ መነገጃ ካደረገው ዘመናት ተቆጥረዋል። አሁን ረሃብ ያጠናወታቸው ስጋቸው ተሸብሽቦ አጥንታቸው ገጦ የሚታይ ፎቶ ለዓለም ቢለቀቅ ደስታውን አይችለውም። ያኔም በትግራይ ህዝብ ላይ የነገድበት በዚህ አይነት ሁኔታ ነው። ወደፊቱም የወያኔ ወረት የትግራይ ህዝብ ነው። የትግራይ ህዝብ መከራና ችግር ግን ለእነ ጌታቸው ረዳ ጭራሽ አይታያቸውም። እስቲ አመራር ላይ ካሉት መካከል ልጆቻቸው፤ ዘመዶቻቸው በጦር ሜዳ ላይ አሉ የምትሉ ካላችሁ ንገሩን? የስዬ አብርሃ ልጆች ትግራይ ውስጥ ናቸው? የጻድቃን ቤተሰቦች ይዋጋሉ። የዶ/ር ደብረጽዪን ዘመድና አዝማድ ውጊያ ሜዳ ላይ ናቸው? አይደሉም። የትግራይን ህዝብ በውሸት እያደነቆሩ ለዘመናት ሲያስገድሉትና አሁንም በእሳት የሚማግድት እነዚህ የሙታን ስብስቦች ናቸው። የትግራይ ህዝብ ሁሉን መዝኖ በመነሳት ከምድረገጽ ወያኔን እስካላጠፋ ድረስ መከራው ይቀጥላል።
    ያው መግቢያው ላይ እንዳልኩት ግን ወያኔ አስገራሚ ድርጅት ነው። ከ 250 ሺ በላይ ህዝብ በሰውርና በሚስጢር ያስታጠቀው ወያኔ የዶ/ር አብይን መንግስት ነኝ ባይነት ከመፈተን አልፎ አፋርና አማራ ክልል ድረስ ዘልቆ በመግባት ማበራየቱ በራሱ የመንግስት አይነት አቋምና መዋቅር በትግራይ መሬት መስርቶ እንደነበር ያሳያል። ተጨፈጨፉ፤ ተቆርጦ የቀረው ተለቀመ፤ እንደ ድቄት ተበተኑ፤ ለወሬ ነጋሪ የቀረ የለም ኸረ ምን የማይባል ነገር አለ የተባሉት ወያኔዎች የትግራይ ክልልን ባንዲራ የተቀቡ ታንኮች፤ የአየር መቃወሚያዎች፤ መድፎችና ዲሽቃዎች ይዘው የወሎን፤ የአፋርንና የአማራን ህዝብ ያለምንም ርህራሄ ሲገድሉና ሲዘርፉ አዲስ አበባ ላይ ተቀምጦ አካኪ ዘራፍ የሚለው የአብይ መንግስት የአህያ ባል ከጅብ አያስጥል አይነት ነው። ወያኔ ገና ብዙ ገመና የሚያደርስ ድርቡሽ ድርጅት ለመሆኑ አሁን በላሊበላና በሌሎች አካባቢዎች የሚያደርሱትና በማድረስ ላይ ያሉትን ጸረ ሰው፤ ጸረ እንስሳና ጸረ ሰብል የሆነ ተግባር ለትውልድ የሚረሳ አይሆንም። ስለሆነም የወያኔን የዘመናት ሴራ ጠንቅቆ ለሚረዳ ሰው ቀድሞም በህዝብ ላይ ያደረሱት አሁንም የሚያደርሱት ወደፊትም የሚያደርሱት ግፍና ዝርፊያ አብሯቸው የኖረ የፓለቲካ ባህሪያቸው እንጂ ከስልጣን ከተባረሩ በህዋላ የተከሰተላቸው እይታ አይደለም። ይህ በትህነግ ተዘጋጀ የተባለውም ሰነድ የሚያሳየው የክፋታችውን ጥግ ነው። ግን መቼ ይሆን ነገርን መርምረን፤ ሰውን በሰውነቱ ተቀብለን፤ እይታችን ሰፍቶ፤ ከዘርና ከክልል ፓለቲካ ርቀን እውነትን በማየት ለህዝባችን ተደራሽ የምንሆነው? ያ ቀን ይመጣ ይሆን ወይስ እድሜ ልካችን አማራ፤ ኦሮሞ፤ ትግሬ ገለ መሌ በማለት የደንበር ገተር የዘር ፓለቲካችን ይቀጥላል? ቆይቶ ማየት ነው። ለአሁን ይብቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule