• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ልዩ ልዩ የጦርነት ጀብዱዎችና የትህነግ ግፍ

September 9, 2021 12:53 pm by Editor 1 Comment

የአፋር ክልል ልዩ ሀይል አባል የሆነው ሁመድ አሊ የአፋር ክልልን ለመውረር የመጡ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎችን ሲፋለም ጥይት በመጨረሱ በታጠቀው ጊሌ ታንክ የማረከ ጀግና ወጣት ነው!

ህጻናት የታቀፉ ወላጆችን በግፍ የረሸነው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ህጻን አማን እና ወንድሞቹን ያለወላጅ አስቀርቷል።

ህጻና አማን በእናትና አባቱ አስከሬን መካከል በደም ተነክሮ ነው የተገኘው። የእናቱን ሞት አይቷል። የወላጅ እናቱን አስከሬን ታቅፎ ተገኝቷል። ይህ የጭካኔ ጥግ ሂሳብ እናወራርዳለን በሚል የአሸባሪው ቡድን አመራሮች ተናግረው በአማራ ክልል ወረራ ከፈጸሙ በኋላ የፈጸሙት የሽብር ተግባር ነው።

“ኢትዮጵያዊያን እያለን አሸባሪው ህወሓት እንጂ አገር አትፈርስም”፦ ዘማቹ ረዳት ፕሮፌሰር

የሕልውና ዘመቻ ጥሪውን ተቀብለው በግንባር የሚገኙት ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት አልማው “እኛ ኢትዮጵያዊያን እያለን አሸባሪው ህወሓት እንጂ ኢትዮጵያ አትፈርስም፤ ይህም በተግባር እየታየ ነው” ሲሉ ተናገሩ።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት አልማው አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ የቀረበውን የክተት ጥሪ ተቀብለው በማይፀብሪ ግንባር ተሰልፈዋል።

“ለአገር ሉዓላዊነት መከበር ኢትዮጵያዊ ሁሉ መታገል አለበት” የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፣ “በግንባሩ እየተፋለምኩ ያለሁት የአገሬን ሉዓላዊነት ለማስከበር ነው” ሲሉ ለኢዜአ ገልጸዋል።

በተሰለፉበት ግንባር የመከላከያ ሠራዊቱ፣ የፀጥታ ኃይሎች እና የአካባቢው ሕዝብ በጠላት ላይ ድል እየተቀዳጁ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

መላው ሕዝብ በድል አድራጊነት መንፈስ ለአገር ሉዓላዊነት እና አንድነት በመዋደቅ ለግለሰቦች ሥልጣን ሲል ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሣውን አሸባሪ ቡድን በያለበት መታገል እንዳለበት አመልክተዋል።

አሸባሪው ህወሓት ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማት፣ ቤተ-እምነቶችን እና የሕዝብ መገልገያ መሠረተ ልማቶችን እያወደመና እየዘረፈ የሚገኘው አሸባሪው ቡድን የሚነዛውን የሐሰት ወሬ መከተል እንደማያስፈልግ አስገንዝበዋል።

“የኢትዮጵያ ሕዝብ ድል እያደረገ እንደሆነ መታወቅ አለበት” ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ ሁሉም ዜጋ ባለው አቅም በግንባር በመገኘትና ደጀን በመሆን ለአገሩ ነፃነት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቡድኑ ምንም የማያውቁ ህፃናትን ለጦርነት እያሰለፈ ለሞት እየዳረጋቸው እንደሆነም አክለዋል። (ኢብኮ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News, Politics

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    September 10, 2021 12:12 pm at 12:12 pm

    ወያኔ ማለት አረመኔ ማለት ነው። እንኳን ሃሽሽ እያጨሰና አፍልቶ እየተጋተ እንዲሁም የእንስሳ ክምችት ነው። ያለ እኛ ላሳር ይሉን የነበሩት እነዚህ ሙታኖች ሰውና ሃገር ይዘው መሞታቸው ብቻ ነው የሚያሳዝነው። ያለ ልቡ ከመንገድ ላይ በወያኔ ካድሬዎች እየተጠለፈ ለጦርነት የሚማገደው የትግራይ ወጣት ያሳዝናል። ወያኔ ግፈኛ ነው በቅርቡ በጦር ሜዳ የለቀመውን አስከሬን በገመድና በሌላም ነገር ተብትቦ ወንዝ ላይ በመልቀቅ ለዓለም ህዝብ የዘር ማጥፋት እየተፈጸመብን ነው በማለት በሱዳን በኩል ገብታ ሁኔታውን በዘገበችው ጭፍን የCNN ጋዘጠኛን ሪፓርት ለተመለከተ ወያኔ በእዝ ሰንሰለቱ እንዴት አድርጎ ሰውንና መንግስታትን እያታለለ እንደሆነ ማየት ይችላል። ጋዜጠኛዋ አንድ እውነትነት ያለው ነገር ብቻ ተናግራለች። የሙታን መርማሪ የሆኑ ሰዎች በነገሩኝ መሰረቱ ሰዎቹ ከሞቱ ቆይቷል በማለት አላዝናለች። ይህ ሁኔታ ወያኔ ሬሳ አከማችቶ በሚመቸው ጊዜ ሬሳውን እያሰረ እንደለቀቀ ማጠናከሪያ መረጃ ነው። ወያኔ በቁም ሰው ብቻ ሳይሆን በሟችም የሚነግድ እኩይ ፍጡር ነው። በራሳቸው የሴራ ግድያ የሞተውን ጄ/ ሃያሎምን ሆለታ ላይ የነበረውን የጦር ት/ቤት በስሙ ሰይመውታል። በባህርዳር ራሳቸው የገደሉትን ሙለዓለምን የሙሉዓለም አዳራሽ መታሰቢያ አቁመውለታል። ብዙ ማለት ይቻላል።
    አሁን እንሆ በወሎ በጎንደርና በአፋር ወረራ እየፈጸመና እየተደበደበ ያለው ወያኔ ያለ እኛ ወንድ፤ ያለ እኛ የጦር አውቂ በማለት ራሱን አሳምኖ በአዲስ አበባ ዳግም ራሱን ሚኒሊክ ቤተመንግስት ለማስጠልል ያልሞከረው ሴራ የለም። ግን አልተሳካም። ጄ/ባጫ ደበሌ እንደተናገሩት “ውጊያው በመንግስትና በሌቦች መካከል ነው”። ወያኔ በራያና ቆቦ በሌሎችም የወሎ ቦታዎች የሰራው ግፍ ጭራሽ አያቀባብርም። ያው ገጣሚው እንዳለውን ነው።
    የታሪክ ሃገር ናት የፍቅር ከተማ
    ወሎ አይወለድም ፈሪና ገገማ
    ወያኔ ገገማ ነው። የወሎን ህዝብ ያለ ልቡ ለማንበርከክ ያደረገው ሙከራ ከሽፏል። በአፋር በኩል በአፋር ጀግኖች ድባቅ ተመትቷል። ጠባብ፤ ሰነፍ፤ የማይዋጋ፤ የሃገር እና የህዝብ ጠላት እየተባለ በወያኔ ካድሬዎች ዘንተ ዓለም የሚፈረጀው የአማራ ህዝብም በቃኝ ከአሁን ወዲያ በማለት በልዪ ልዪ መንገድ ተደራጅቶ ወያኔን መልሶ አፍንጫውን ሲያደማው እያየን እየሰማን ነው። ለዚህ መሰለኝ ዘፋኙ እንዲህ ያለው።
    ጠባብ ነው እያሉ ሲንቁ ሲንቁ
    ነፍጠኛ ነው ብለው ሲንቁ ሲንቁ
    ወንድ ነን ባዪቹ በወንዶች አለቁ
    ትህነግ የአማራን ህዝብ ገና ከጅምሩ ጀምሮ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው በማለት ፈርጆ አማራው ከቀረው ወገኑ ጋር አብሮ እንዳይኖር በየቦታው እሳት እያቀጣጠለ እያጫረሰን እንደነበርና እንዳለ ልብ ያለው ያስተውላል። እነዚህ አሪዎሶች ከራሳቸው ሆድ እቃ ውጭ ስለ ሌላው ሰው ጉዳት ደንታ የላቸውም። የደነዘዙ በድኖች ናቸው። ዛሬ በአሜሪካ የተጠለሉት አቶ ስዬ አብርሃ፤ የድሮው አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ያሉት ሾተላዎች በሩቅ ሆነው በዚህና በዚያ ነገር እየተበተቡ የትግራይን ህዝብ እያስጨረሱ ናቸው። የእነርሱ ልጆችና ቤተሰቦች ግን በአሜሪካ የተደላደለ ህይወትና ኑሮ ከኢትዮጵያ በዘረፉት ሃብት እየኖሩ ይገኛሉ። ብርሃነ ገ/ክርስቶስ በብራስል አምባሳደር ሆኖ ሲሰራ የፈጸመው ግፍ መፈጠርን የሚያስጠላ ነው። ያ የኢትዮጵያ ቆንስላ የተባለው ቦታ ከላይ እስከ ታች በወያኔ ሰዎች የተሞላ ነበር። በሰውር የምዝበራ ብልሃት ይህ ሰው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር እየወጣ በተሰጠው ገንዘብ አዲስ አበባ ላይ የእምነ በረድ ደረጃ ያለው የተንጣለለ ቤት ሰርቷል። በአሜሪካ ከፈታት ሚስቱ ጋር የተካፈለው እልፍ ገንዘብ ዛሬ ለእርሱና ለእርሷ መጦሪያ እየሆነ ነው። እናውቃለን ያንድ ዲፕሎማት ደሞዝ ምን ያህል እንደነበረና አሁንም እንደሆነ። እነዚህ ናቸው ታዲያ ለትግራይ ህዝብ ገለ መሌ የሚሉን። የሩቅ ጡሩንበኞች። ለራስ ብቻ ኗሪዎች። ዛሬ ማንም የማይበግረው የትግራይ ጦር እያሉ ሲያሞካሹት የነበሩት ድንጋይና ድላ በያዘ ፋኖ ሲማረክ ምን ይሰማቸው ይሆን። ግፍ ቁርጠኞችን ይፈጥራል። የሆነው እንደዛ ነው። ወደ 50 ዓመት ለሚጠጉ ዘመናት አማራን ያሰቃያው ወያኔ ዋጋውን እያገኘ ነው። እኔ የሚገርመኝ እንገነጠላለን ሲሉ ነው። አርጎት ነው። ከማህል ሃገር ከአፋር፤ ከአማራ ከኦሮሞ ባጠቃላይ ከጠቅላላው የሃገሪቱ ዳር ድንበር ተሟጣችሁ ውጡና የናፈቃችሁትን ሃገር ሁኑ። ማን ይለማመጣቹሃል። ሃገር አፍራሽ እንደሆናችሁ እኮ ህዝቡ ገና ድሮ ገብቶታል። አፍናችሁ ይዛቹሁ አላናግር ብላችሁት እንጂ። በእናቱና በአባቱ ሬስ መካከል ከሞት የተረፈው ያ ህጻን ገና አድጎ ይፋረዳቹሃል። እናንተ ወራዶች፤ ከሰው ተራ የወጣችሁ አውሬዎች። ለዓለም ህዝብ ተራብን፤ የዘር ማጥፋት ተፈጸመብን እያላችሁ ግፍ ፈጻሚዎች። ፈጣሪን የማትፈሩ ጣረሞቶች። ከምድረገጽ ያጥፋችሁ። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule