በሁሉም ክልሎች በችሎታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው 50 ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሁሉም ክልሎች በዓይነታቸው ልዩ የሆኑና የልህቀት ማዕከል የሚሆኑ 50 ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ ብለዋል። ትምህርት ቤቶቹ ቀጣይ የአገር መሪ የሚሆኑ ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎች የሚፈልቁበት በችሎታቸው ብቻ የሚመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው መሆናቸውንም ተናግረዋል። በትምህርት ቤቶቹ የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መሠረት ባደረገና የትምህርት ሚኒስቴር በሚያወጣውን መመዘኛ የሚያሟሉ ተማሪዎች የሚማሩባቸው እንደሆኑም ተገልጿል። በሁሉም ክልሎች በሚገነቡት እነዚህ የልህቀት ማዕከላት ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የሚመለመሉ ተማሪዎችን ተቀብለው የሚያስተምሩ ናቸው። በተያያዘ ዜና የትምህርት ሚኒስቴር … [Read more...] about በሁሉም ክልል 50 የልህቀት ት/ቤቶች ይገነባሉ፤ ለወደሙትም 1.6 ቢሊዮን ብር ተበጅቷል
Archives for January 2022
ውሃ ጥምን በኢትዮጵያዊ እስረኞች ስቃይ ‘የማርካት’ ፖለቲካዊ ቅዠት
ሪያድ ኢትዮጵያን በተለያዩ መስኮች በዘላቂነት እንደምትደግፍ የሳዑዲ ልማት ፈንድ መግለፁን ከወደ ሳዑዲ አረቢያ በዛሬው ዕለት ተሰምቷል። የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና የሳዑዲ ልማት ፈንድ ስራ አስፈፃሚ "ለሳዑዲ አረቢያና ኢትዮጵያ የጋራ ጥቅም የሚውሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል። እንደ ዘገባዎቹ የሳውዲ የልማት ፈንድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሱልጣን ቢን አብዱራህማን አል-ሙርሺድ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴን ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን፤ ሳዑዲ አረቢያ በሳዑዲ ፈንድ በኩል በኢትዮጵያ ባከናወናቸው የልማት ተግባራትና እየተከናወኑ በሚገኙ ፕሮጀክቶች ላይ ከመወያየት ባለፈም ስለ ቀጣይ የትብብር ዘርፎች መክረዋል ነው የተባለው። የትብብር መስኮቹ በዝርዝር ያልተገለፁ ቢሆንም የትብብር መስኮቹ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የብልጽግና ዘርፎች ላይ … [Read more...] about ውሃ ጥምን በኢትዮጵያዊ እስረኞች ስቃይ ‘የማርካት’ ፖለቲካዊ ቅዠት
“የፌደራል መንግሥቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ንቀት እያሳየ ነው፤ ህወሓትን ያለበት ድረስ ሂዶ ማጥፋት አለበት” – ባልደራስ
"ባልደራስ የራሱን ሚሊሻ አዘጋጅቶ ትህነግን ይግጠም" አስተያየት ሰጪዎች ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ፤ ማዕከላዊ መንግስት ህወሓትን “ያለበት ድረስ ሂዶ ማጥፋት አለበት” ሲል አስታወቀ። ፓርቲው የኢትዮጵያ መንግሥት የመከላከያ ሰራዊቱን ባለበት ጸንቶ እንዲቆይ ያስተላለፈውን ውሳኔንም ነቅፏል። የባልደራስን አቋም የተቃወሙ አስተያየት ሰጪዎች ባልደራስ ውጊያ ከፈለገ ራሱ ሄዶ ትህነግን ይግጠም ሲሉ መግለጫውን ነቅፈዋል ፓርቲው “መንግሥት ‘ምዕራፍ አንድ’ ያለውን ዘመቻ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሳያረጋግጥ ማቆሙ፤ ትልቅ አደጋ ያዘለ ነው” ሲል ስጋቱን ገልጿል። ህወሓት አሁንም የሀገሪቱን አንድነት ሊፈታተን በሚችል ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛል” ያለው ባልደራስ፤ መንግሥት “ዘመቻውን ያቆመበትን ምክንያት በተመለከተ በቂ ምላሽ አልሰጠም” ሲል ተችቷል። የፌደራል መንግሥቱ ለኢትዮጵያ … [Read more...] about “የፌደራል መንግሥቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ንቀት እያሳየ ነው፤ ህወሓትን ያለበት ድረስ ሂዶ ማጥፋት አለበት” – ባልደራስ
በሕዝብ ላይ የሚስማር ጥይት እስከማዝነብ የደረሰው የህወሓት የጭካኔ ጥግ!!
እብሪተኛው የህወሓት ኃይል የትኛውንም አማራጭ ተጠቅሞ ወደ ሥልጣን መመለስ ወይም ኢትዮጵያን መበታተን የሚል ቀቢፀ ተስፋ ይዞ ነበር ወደ ወረራ የገባው፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከለከለውን በርካታ ሚስማር መሰል ፍንጣሪ (flechette) የተሰገሰገባቸውን በከባድ መሣሪያ ጭምር የሚተኮሱትን የሚስማር ጥይቶች በንፁሃን ላይ ማርከፍከፉ ነው፡፡ በምስሉ ላይ ወራሪው ኃይል በአፋር ጭፍራ ከተማ በንጹኃን ላይ የተጠቀማቸው የሚስማር ጥይቶች ይታያሉ፡፡ ወራሪው ኃይል ይህን መሣሪያ በአፋር እና በአማራ ክልሎች ተጠቅሟል፡፡ ነዋሪዎች እንደመሰከሩት ሚስማሮቹን ከበርካታ ጉዳት ከደረሰባቸው ንፁሃን ሰዎች ገላ ላይ ነቅለዋል፡፡ ሰቆቃውን ተመልክተዋል፡፡ ኢትዮጵያ እንደዚህ አይነት መሣሪያዎች ጥቅም ላይ ላለማዋል ዓለም አቀፍ ስምምነት ፈርማለች። (አዲስ … [Read more...] about በሕዝብ ላይ የሚስማር ጥይት እስከማዝነብ የደረሰው የህወሓት የጭካኔ ጥግ!!
በእንግሊዝ ሮያል ሚሊታሪ አካዳሚ የወርቅ ጎራዴ ተሸላሚው ም/መቶ አለቃ ለገሰ
ምክትል መቶ አለቃ ለገሰ መብራት ፥ ለአንድ ዓመት ከስምንት ወር ትምህርታቸውን በመከታተል አመርቂ ውጤት ማምጣታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡ በሮያል ሚሊታሪ አካዳሚ ከ38 የአፍሪካ እና የአውሮፓ ሃገራት የተውጣጡ 250 ተማሪዎች መካከል የአንደኝነት ደረጃን በመያዝ የጥንታዊያን የምስራቅ አገሮች የወርቅ ጎራዴ እና ሜዳሊያ ተሸላሚ ለመሆን መብቃታቸውን እና ሜዲያሊያውንም መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡ ለሽልማቱ በመስፈርትነት የተቀመጡትን በአካዳሚክ፣ በሚሊታሪ እና የተግባር ትምህርት ካሉት ተማሪዎች ውስጥ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ለሽልማቱ መብቃታቸውን ነው ያስረዱት፡፡ ምክትል መቶ አለቃ ለገሰ መብራት ከኤታማዦር ሹሙ በተጨማሪ ከከፍተኛ ጄነራሎች ጋር ቆይታ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡ ጄነራሎችም በውጤቱ … [Read more...] about በእንግሊዝ ሮያል ሚሊታሪ አካዳሚ የወርቅ ጎራዴ ተሸላሚው ም/መቶ አለቃ ለገሰ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች ላይ መግለጫ ሰጠ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች የስነ-ስርዓት ሂደቶች ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ባለፈው ሶስት ዓመት ተኩል የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በተገቢው ደረጃ ለማከናወን በርካታ የለውጥ ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የለውጥ እርምጃዎች ትኩረት ያደረጉት በተቋማዊ እና በግለሰብ ዳኞች ደረጃ የፍርድ ቤቱን ነጻነት እና ገለልተኝነት ማስከበር ነው፡፡ በተጓዳኝም ለተጠያቂነት ተቋማዊ ስርዓቶች ተዘርግተዋል፡፡ በፍ/ቤቱ አመራሮች እና ዳኞች በኩል ሲደረግ የነበረው ጥረት ዋናው ግብ የሚሰጠው የዳኝነት ዘርፍ ቀልጣፋ፣ ተገማች እና ተደራሽ በማድረግ በፍርድ ቤቱ አገልግሎት ላይ የሕዝብ አመኔታ እንዲጨምር ነው፡፡ በዚህ ወር መጨረሻ በሚዘጋጀው “የፍርድ … [Read more...] about የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች ላይ መግለጫ ሰጠ
“በሸኔ አባላት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ከፍተኛ ግጭት ተሸጋግሯል”
በአሸባሪው ሸኔ አባላት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ከፍተኛ ግጭት መሸጋገሩንና መንግስት በቡድኑ ላይ የሚወስደው እርምጃም አጠናክሮ መቀጠሉን የኦሮሚያ ኮሚንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ አስታወቁ። አቶ ሀይሉ የክልሉን ሰላምና ልማት አስመልክተው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፤ የክልሉን ሰላም እያናጋ ያለው የሸኔ ሽብር ቡድን ከሁሉም በማስቀደም በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ በአባ ገዳዎችና በሀዳ ሲንቄዎች በተደረገው ጥሪ 312 የቡድኑ አባላት ተመልሰዋል። 540 የሚሆኑት ደግሞ በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከታህሳስ 16 እስከ 30 ዓ.ም በተወሰደው እርምጃ 876 አባላት ሲደመሰሱ ኮማንድ ፖስቱ ስራ ከጀመረ ወዲህ በጥቅሉ ሁለት ሺህ 439 የቡድኑ አባላት ተደምስሰዋል ብለዋል። በተመሳሳይ መልኩ ወደ ሰላማዊ መልኩ ወደ ሰላማዊ … [Read more...] about “በሸኔ አባላት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ከፍተኛ ግጭት ተሸጋግሯል”
ዘላቂ ወዳጅ የሌላት አሜሪካ ፊቷን በትህነግ ላይ እያዞረች ነው
ትህነግ ብዙ ወጪ ያደረገበት የሎቢ ሥራ ኪሣራ እየገጠመው ነው አሜሪካ ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ለመመለስ ፍንጭ አሳየች የኢትዮጵያ መንግሥት ከአሜሪካ የንግድ ልዑክ የተነሱበትን ቅሬታዎች በተመለከተ ተጨማሪ “አዎንታዊና ገንቢ” ዕርምጃዎችን የሚወስድ ከሆነ፣ ኢትዮጵያ ከተጠቃሚነት የተሰረዘችበትን የአሜሪካ መንግሥት ከቀረጥ ነፃ የንግድ ዕድል (አጎአ) በተመለከተ የንግግር ሒደት ውስጥ ለመግባት ፈቃደኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጋዜጠኞች ጋር በስልክ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ ኢትዮጵያ ከአውሮፓውያኑ ጥር ወር 2022 ጀምሮ ከአጎአ ተጠቃሚነት የታገደችው የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ከሰብዓዊ መብትና ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የተቀመጡ መስፈርቶችን ባለማሟላቷ መሆኑን መናገራቸውን ኋይት ሀውስ … [Read more...] about ዘላቂ ወዳጅ የሌላት አሜሪካ ፊቷን በትህነግ ላይ እያዞረች ነው
የወንጀል ክስ ማንሳት እና ማስቀጠል የሚቻለዉ መቼ ነዉ?
የክስ ማንሳት የፍሬ ነገር ይዘትና ስነ ሥርዓት በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 122 ስር በአምስት ንዑስ አንቀጾች ተጠቃሎ ይገኛል፡፡ በይዘቱም፡- • ከከባድ የሰው ግድያ እና ከከባድ ውንብድና ወንጀሎች ውጭ ዐ/ሕግ ከፍርድ በፊት ክስ ማንሳት ይችላል፡፡ • ክስ የሚነሳው በዐ/ህጉ ጥያቄ ወይም በሌላ የመንግስት አካል ትዕዛዝ ሊሆን ይችላል፡፡ • ክሱ የሚነሳው በፍ/ቤት ፈቃድ ሲሆን ፍ/ቤቱ ለመከልከልም ሆነ በመፍቀድ ምክንያቱን ማስቀመጥ አለበት፡፡ • በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 113 መሰረት አዲስ ክስ ካልቀረበ ተከሳሹ ለግዜው ይለቀቃል፡፡ • የክሱ መነሳት ዐ/ሕግ ክስን ከማንቀሳቀስ አያግደውም፡፡ የሚል ሀሳብ ያለው ነው፡፡ የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲቲዩት ባዘጋጀው ረቂቅ የወንጀል ስነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 119 ስር ዐ/ሕግ ከፍርድ ቤት በማንኛውም ጊዜ ክስ … [Read more...] about የወንጀል ክስ ማንሳት እና ማስቀጠል የሚቻለዉ መቼ ነዉ?
አሸባሪው የትግሬ ቡድን ያደረሰው ውድመት በሳይንሳዊ መልኩ እየተጠና ነው
የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ እየተካሄደ የሚገኘውን ጥናት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ኀላፊ አንሙት በለጠ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል መጠነ ሠፊ የሰብዓዊ ጥሰት፣ የንብረት ዘረፋና ውድመት ፈጽሟል ብለዋል። በሽብር ቡድኑ ምክንያት የደረሰውን አጠቃላይ ውድመት ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እየተጠና እንደሆነ አቶ አንሙት አስረድተዋል። በጥናቱ መሠረት ትክክለኛ ውድመቱ እንደሚገለጽ ነው የተናገሩት። ጥናቱ በጎደለው ልክ ለመሙላት አጋዥ እንደሚሆንም ጠቁመዋል። ከጥናቱ በኋላ የወደሙ መሰረተ ልማቶች ተመልሰው በሚገነቡበት ሁኔታ ላይም ስትራቴጂክ እቅድ እየተዘጋጀ እንደሆነ አመላክተዋል። አቶ አንሙት እንደተናገሩት የጥናቱ ዓላማ ቡድኑ ያደረሰውን ውድመት ትክክለኛ መረጃን መስጠትና በሰነድ ማስቀመጥ፣ የሽብር ቡድኑ ተጠያቂ … [Read more...] about አሸባሪው የትግሬ ቡድን ያደረሰው ውድመት በሳይንሳዊ መልኩ እየተጠና ነው