አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስካልተወገደ ድረስ የኢትዮጵያ ስጋት መሆኑ ስለማይቀር መቼም ቢሆን በድል ሰክረን አንተኛም ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሙሉዓለም አድማሱ ገለጹ። ሜጀር ጄነራል ሙሉዓለም አድማሱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስካልተወገደ ድረስ የኢትዮጵያ ስጋት መሆኑ አይቀርም። የሽብር ቡድኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ስለማይተኛ እኛም መቼም ቢሆን በድል ሰክረን አንተኛም ብለዋል። ጦርነት ለሽብር ቡድኑ የመኖርና ያለመኖሩ ጉዳይ ስለሆነ ከዚህ በኋላም ቢሆን ወረራ ለማካሄድ ሊሞክር ይችላል ያሉት ሜጀር ጄነራል ሙሉዓለም፤ የሽብር ቡድኑ በአሁኑ ጊዜ በሰው ኃይል፣ በትጥቅና በመሳሪያ ተዳክሟል፤የሞራል ውድቀትም ደርሶበታል ነው ያሉት። በተቃራኒው በወገን ኃይል የድል … [Read more...] about “መቼም ቢሆን በድል ሰክረን አንተኛም” ሜጀር ጄነራል ሙሉዓለም አድማሱ
Archives for January 2022
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወዲህ ከ2 ሺህ 400 በላይ የኦነግ ሸኔ አባላት ተደምስሰዋል
በሁለት ሳምንት ውስጥ ብቻ 876 በሚሆኑ የየኦነግ ሸኔ አባላት ላይ ተወስዷል የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ በክልሉ የልማትና የፀጥታ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። የአሸባሪውን ሸኔ አጥፊ ቡድን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተቀላቀሉ ወጣቶች ከአባገዳዎች ጋር በመነጋገር 312 ወጣቶች እጅ እንዲሰጡ መደረጉ ተነግሯል። የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ባለው ስራም በሁለት ሳምንት ብቻ 876 የሚሆኑ የቡድኑ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱም በመግለጫው ተነስቷል ። ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወዲህም ከ2 ሺህ 400 በላይ የቡድኑ አባላት ሲደመሰሱ፥ በህብረተሰቡ ጥቆማ 540 የሚሆኑት በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው የተባለው። የአካባቢ ጥበቃ ስራን በተመለከተም፥ ለምርትና ምርታማነት ወሳኝ ሚና የሚጫወተው የአካባቢ ጥበቃ ስራ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ … [Read more...] about ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወዲህ ከ2 ሺህ 400 በላይ የኦነግ ሸኔ አባላት ተደምስሰዋል