
በሁለት ሳምንት ውስጥ ብቻ 876 በሚሆኑ የየኦነግ ሸኔ አባላት ላይ ተወስዷል
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ በክልሉ የልማትና የፀጥታ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። የአሸባሪውን ሸኔ አጥፊ ቡድን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተቀላቀሉ ወጣቶች ከአባገዳዎች ጋር በመነጋገር 312 ወጣቶች እጅ እንዲሰጡ መደረጉ ተነግሯል። የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ባለው ስራም በሁለት ሳምንት ብቻ 876 የሚሆኑ የቡድኑ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱም በመግለጫው ተነስቷል ።
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወዲህም ከ2 ሺህ 400 በላይ የቡድኑ አባላት ሲደመሰሱ፥ በህብረተሰቡ ጥቆማ 540 የሚሆኑት በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው የተባለው።
የአካባቢ ጥበቃ ስራን በተመለከተም፥ ለምርትና ምርታማነት ወሳኝ ሚና የሚጫወተው የአካባቢ ጥበቃ ስራ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በነገው እለት በይፋ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡ በክልሉ የመኸር ምርትን የመሰብሰብ ስራው ጋር ተያይዞ በአመርቂ ሁኔታ መከናወኑን ነው ሃላፊው ያነሱት።
በዚህም 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር ላይ ከተዘራው ሰብል እስካሁን 5 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር ሰብል ተሰብስቧል ብለዋል። በመስኖ ስንዴ ልማት ዘርፉም 350 ሺህ ሄክታር ለማልማት ታቀዶ እስካሁን 302 ሺህ ሄክታር ማልማት መቻሉን አንስተዋል። ለተፋሰስ ልማቱም ቦታዎች መለየታቸውን ገልጸው፥ ነገ የልማት ስራው በይፋ ይጀመራልም ነው ያሉት። በዝናብ እጥረት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ሰብአዊ ድጋፍ የማድረስ ስራም ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ “በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን እስካሁን በተካሄደ ኦፕሬሽን 433 የአሸባሪው ሸኔ ቡድን አባላት ሲደመሰሱ 115ቱ ተማርከዋል፤ የቡድኑ የመረጃ እና የሎጅስቲክስ ክንፍ የሆኑ ወደ 623 የሚደርሱ አባላትን በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል”።
“አሁን ላይ ቡድኑ በዞኑ የሚያካሂደው መስፋፋት ሙሉ በሙሉ እየደረቀ ሲሆን፤ በአጭር ጊዜም ዞናችንን ከአሸባሪው ሸኔ ነፃ በማድረግ ለሕዝባችን የተሟላ ሰላም እናረጋግጣለን” በማለት የሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ደቻሳ ተናግረዋል ተናግረዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply