ምክትል መቶ አለቃ ለገሰ መብራት ፥ ለአንድ ዓመት ከስምንት ወር ትምህርታቸውን በመከታተል አመርቂ ውጤት ማምጣታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡
በሮያል ሚሊታሪ አካዳሚ ከ38 የአፍሪካ እና የአውሮፓ ሃገራት የተውጣጡ 250 ተማሪዎች መካከል የአንደኝነት ደረጃን በመያዝ የጥንታዊያን የምስራቅ አገሮች የወርቅ ጎራዴ እና ሜዳሊያ ተሸላሚ ለመሆን መብቃታቸውን እና ሜዲያሊያውንም መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡
ለሽልማቱ በመስፈርትነት የተቀመጡትን በአካዳሚክ፣ በሚሊታሪ እና የተግባር ትምህርት ካሉት ተማሪዎች ውስጥ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ለሽልማቱ መብቃታቸውን ነው ያስረዱት፡፡
ምክትል መቶ አለቃ ለገሰ መብራት ከኤታማዦር ሹሙ በተጨማሪ ከከፍተኛ ጄነራሎች ጋር ቆይታ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
ጄነራሎችም በውጤቱ እጅግ ደስተኞች መሆናቸውን በመግለፅ ፥ አገሩ ከእርሱ ብዙ የምትጠብቅ በመሆኗ ከዚህ ከፍ ያለ መልካም ተግባር ማከናወን እንዳለበት መልዕክት እንዳስተላለፉላቸው ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ (AMN)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply