• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ውሃ ጥምን በኢትዮጵያዊ እስረኞች ስቃይ ‘የማርካት’ ፖለቲካዊ ቅዠት

January 28, 2022 11:46 am by Editor Leave a Comment

ሪያድ ኢትዮጵያን በተለያዩ መስኮች በዘላቂነት እንደምትደግፍ የሳዑዲ ልማት ፈንድ መግለፁን ከወደ ሳዑዲ አረቢያ በዛሬው ዕለት ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና የሳዑዲ ልማት ፈንድ ስራ አስፈፃሚ “ለሳዑዲ አረቢያና ኢትዮጵያ የጋራ ጥቅም የሚውሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።

እንደ ዘገባዎቹ የሳውዲ የልማት ፈንድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሱልጣን ቢን አብዱራህማን አል-ሙርሺድ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴን ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን፤ ሳዑዲ አረቢያ በሳዑዲ ፈንድ በኩል በኢትዮጵያ ባከናወናቸው የልማት ተግባራትና እየተከናወኑ በሚገኙ ፕሮጀክቶች ላይ ከመወያየት ባለፈም ስለ ቀጣይ የትብብር ዘርፎች መክረዋል ነው የተባለው።

የትብብር መስኮቹ በዝርዝር ያልተገለፁ ቢሆንም የትብብር መስኮቹ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የብልጽግና ዘርፎች ላይ እንደሚሆኑ ነው የተገለፀው። 

የሪያድ ውሃ-ጥም እና ስሁት ጎዳናዎቿ 

በቀጣዮቹ ሃያ ዓመታት ውስጥ ለመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካና ማህበራዊ ቀውስ መንስኤ የሚሆነው ጦርነት ወይም ሽብርተኝነት እንዳይመስላችሁ” ይላል Jon B. Alterman ከ10 አመት በፊት ይፋ ያደረጉት ጥናታቸው። “Clear Gold” በሚል ርዕሳቸው የውሃን ቀጣይ ውድነት በሚጠቁም ጥናታቸው አልተርማን “የመካከለኛው ምስራቅ ስትራቴጂያዊ ከባድ ካርድ በመሆን ለፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ ዋነኛ መነሾ የሚሆነው ውሃ እና የውሃ እጥረት ነው” ነበር ያሉት። 

የሳዑዲ ውሃ ጥም

በአንድ ወቅት 500 ቢሊዮን ሜኪዩብ የከርሰ ምድር ውሃ ክምችት የነበራት ሳዑዲ አረቢያ 98 በመቶ የውሃ አቅርቦቷን ከዚሁ የውሃ ሐብቷ ነበር የምታገኘው። የዜጎቿ ዕለታዊ የውሃ ፍጆታ ከአውሮፓ ስታንዳርድ በእጥፍ ከፍ ያለ መሆን፤ በዛ ላይ ደግሞ በ 1980ዎቹ ጀምሮ አገሪቱን የሩዝና የእርሻ ደሴት ለማድረግ የተጀመሩ ሰፋፊ ፕሮጀክቶች የከርሰ ምድር ውሃዋን አሟጠጠውና ከባድ አደጋ ተደቀነባት። 

ይህን ተከትሎም 2015 ላይ 80 በመቶው የሳዑዲ የከርሰ ምድር ውሃ ማለቁን ጥናቶች አረጋገጡ። ናሽናል ጂኦግራፊክ ጭምር ይህንኑ ጥናታዊ ሪፖርት መዘገቡ ይታወሳል።

ይባስ ብሎም የሳዑዲው ኪንግ ፈይሰል ዩኒቨርሲቲ በ2016 ያወጣው ሪፖርት የሳዑዲ የከርሰ ምድር ውሃ በ 13 አመታት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንደሚያልቅ ደምድሟል። ይኸውም በ2020ዎቹ መሆኑ ነው። 

የገጠማትን የውሃ ቀውስ ለመቅረፍ በተለያዩ አገራት ከገዛችው ውሃ ገብ የእርሻ መሬት በተጨማሪ የባህር ውሃን ለማጣራትም ሰፊ ርብርብ ማድረግ ከጀመረች ሰነባብታለች። ጨዋማ የባህር ውሃን አጣርታ ለመጠቀምም በየዓመቱ 3 ቢሊዮን ዶላር እያወጣች ነው የምትገኘው። በዓለማችን ከሚደረገው የባህር ውሃ የማጣራት ስራ ግማሹን መጠን የሚሸፍነው የሳዑዲ ዲሳሊኔሽን ነው። 

ተከዜን በፖርት ሱዳን ወደ ሪያድ የማሻገር ህልም 

የናይል ዋነኛ ገባሮች የሆነውን የተከዜ-አትባራ ወንዝ በመጥለፍ ወደ ሪያድ-ሳዑዲ አረቢያ በቀይ ባህር በኩል ለማሻገር ሳዑዲዎች ዓቅደው ነበር። ዕቅዱ የታሰበው በሳዑዲ ምኞትና በግብፅ ማን አለብኝነት ነበር። ጊዜው ደግሞ የ1980ዎቹ መጨረሻ። ዳንኤል ክንዴ የተባሉ ምሁር በ1999 እኤአ ባወጡት ፅሁፋቸውም እንደሚከተለው አስቀምጠውታል። 

▮…“በሰዓት 4.5 ሚሊዮን ሊትር የሚሆን ውሃ ከአትባራ (ተከዜ) በመጥለፍ ወደ ቀይ ባህሯ የወደብ ከተማ ፖርት ሱዳን ከዚያም ወደ ሪያድ ሳዑዲ አረቢያ በቀይ ባህር በኩል ለማሻገር በግብጽ ሙሉ ድጋፍ የ2 ቢሊዮን ዶላር ስራ በአርቃቂዎች ተጀምሮ ነበር፡፡ እንደ ዕቅዱ ከሆነ ሱዳን በሁለት መልኩ የምትጠቀም ሲሆን አንድም ከአትባራ (ተከዜ) በስተምስራቅ የሚገኘውን ጠፍ መሬት ለማልማት የሚያስችላት ሲሆን እንዲሁም በቀይ ባህር ዳርቻ ያሉ ፏፏቴዎችን በመጠቀም በሰዓት ከ7,000 ኪሎዋት በላይ ኤሌክትሪክ ለማምረት ያስችላታል፡፡ ሳዑዲዎቹም ግብፅን እና ሱዳንን (በዚህ ፕሮጀክት ምክንያት) ለሚያጡት የመስኖ ውሃ በግብርና ካፒታል ኢንቨስትመንት እና  በኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ያካክሱታል…”

ይህ ህልም ታዲያ ኢትዮጵያ ተከዜ ወንዝ ላይ በገነባችው ግድብ ህልም ሆኗል። ደግመው እንሞክር ቢሉም ማብሪያ ማጥፊያው ከተከዜው ግድብ ነውና። 

ታዲያ እነ ሳዑዲ ይህን ወይም ይህን መሰል ፕሮጀክት አሁንም አያስቡም አይባልም፡፡ ዕድል እየተጠባበቁ ቢሆን እንጂ። ሳዑዲ ትልቁ ስጋቷ ውሃ ጥም ነው። ከነዳጅም ከወርቅም በላይ ውሃ ትሻለች። 

በግዛቷ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ዜጎችን በማሰቃየት የጀመረችው ሩጫም የውሃ ጥሟን ለማርካት መሆኑ በግልባጩም ቢሆን ሐቅ ነው። ሪያድ የጀመረችውን ሤራ ትታ ወደ ትብብር ብትመለስ ከኢትዮጵያ ጥቅሟን እንደምታሳካ ማን በመከራት?! ሳዑዲ የማታ ማታ ስትለማመጠን መገኘቷ ለማይቀረው ካሁኑ የብርሃኑን መንገድ ብትመርጥ ያዋጣታል። 

Esleman Abay  የዓባይ ልጅ

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

(ፎቶ ከፋይል ክምችት)

Filed Under: Left Column, Politics Tagged With: operation dismantle tplf, saudi arabia, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule