
እብሪተኛው የህወሓት ኃይል የትኛውንም አማራጭ ተጠቅሞ ወደ ሥልጣን መመለስ ወይም ኢትዮጵያን መበታተን የሚል ቀቢፀ ተስፋ ይዞ ነበር ወደ ወረራ የገባው፡፡
ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከለከለውን በርካታ ሚስማር መሰል ፍንጣሪ (flechette) የተሰገሰገባቸውን በከባድ መሣሪያ ጭምር የሚተኮሱትን የሚስማር ጥይቶች በንፁሃን ላይ ማርከፍከፉ ነው፡፡
በምስሉ ላይ ወራሪው ኃይል በአፋር ጭፍራ ከተማ በንጹኃን ላይ የተጠቀማቸው የሚስማር ጥይቶች ይታያሉ፡፡ ወራሪው ኃይል ይህን መሣሪያ በአፋር እና በአማራ ክልሎች ተጠቅሟል፡፡
ነዋሪዎች እንደመሰከሩት ሚስማሮቹን ከበርካታ ጉዳት ከደረሰባቸው ንፁሃን ሰዎች ገላ ላይ ነቅለዋል፡፡ ሰቆቃውን ተመልክተዋል፡፡
ኢትዮጵያ እንደዚህ አይነት መሣሪያዎች ጥቅም ላይ ላለማዋል ዓለም አቀፍ ስምምነት ፈርማለች። (አዲስ ሚዲያ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ሕወኣት ኑክለር ቦምብም ቢሰጠው እንኳን አፋርና ሃማራውን ከአድዋ ውጭ ያሉትንም የትግራይ ሕዝብ ካልደገፉት ይጨርሳል። ደም ያሰከረው ድርጅት መጨረሻው በHIV መሞት ነው።
ወያኔ በሰው ልጆች ሰውነት ላይ የምስማር ጥይት መቀርቀሩ አስገራሚ አይደለም። ይህ ቡድን እኮ ያለምንም ትንኮሳ ሰው ላይ ሮኬት የተኮሰ ቡድን ነው። አሁን አሁን ሃበሻው የተጃጃለ ይመስለኛል። እንዴት እንዲህ አይነት ድፍረት፤ በደልና ዘረፋ፤ ግድያና ሰቆቃ ሰው የሆነ በሰው ላይ ያደርሳል ሲሉ በተደጋጋሚ ይጠይቃሉ። ያበዳችሁት ጥያቄ የምታቀርቡት እናንተ ናችሁ። ወያኔ የሚሰራውን ጠንቅቆ ያውቃል። በወረራቸው ስፍራዎች ሰዎች እቃቸውንም ሆነ ያላቸውን ነገር እንዳያሸሹ የሚያረጋጋ ሃይል፤ ከዚያ ገዳይ ቡድን ከዚያ ጠቃሚ ነገሮችን የሚፈታና የሚዘርፍ ከዚያ የሚጭንና ወደ መቀሌ የሚያጓጉዝ ሃይል አሰማርቶ ነው በወሎ በጎንደር፤ በአፋርና በሽዋ ወገኖቻችን እንደ እባብ የቀጠቀጠው። የወያኔ ታጣቂዎችና ጄሌዎቻቸው ሰው መሆኗቸው ከቀረ ቆይቷል፡ ከደሙ ንጽህ ነኝ የሚሉትም የወያኔ ሰራዊትን ተሰባጥረው በሚኖሩበት ሥፍራ በቀረበ ቁጥር ባህሪያቸው እየተለወጠ መንገድ ሲመሩ፤ ሰው ሲያስገድሉ፤ የዘረፋው ተባባሪ ሲሆኑ ታይቷል። እጅና እግሩን አጣምሮ የተቀመጠውና በተቀናበረ የፓለቲካ አሻጥር በኦሮሞ አክራሪዎችና በወያኔ ጽልመታዊ ምህታት ለዘመናት የተመታው የአማራ ህዝብ ለመንቃት ጊዜ ፈጅቶበት አሁን እንሆ ቤቱን እያንኳኳ ለወሬ የማይመች ነገር ወያኔ ሲያደርስበት ሆ ብሎ ተነስቷል። የዛሬው ሆ ማለት በነቃ በተደራጀ፤ ለህግ በሚገዛና በሚመራ በአንድ እጅ ሥራውን በሌላ እጅ ራሱንና ቤተሰቡን የሚከላከልበት መሳሪያውን የሚታጠቅ የበሰለና የተቀናጀ ሃይል ከላይ እስከ ታችኛው በሚሩርበት ክፍል እስካልተዘጋጀ ድረስ የኢትዮጵያ ሰራዊት ያድነኛል ብሎ ቁጭ ማለት ራስን ለዳግም እልቂት ማደራጀት ነው። ገደሉን ወርደው፤ ጥሻውን ጥሰው፤ በሜዳው ተንከባለው ወያኔን እያሳደድ የመቱት የሃገሬው ኗሪዎች፤ ፋኖ፤ የአማራ ሚሊሻ እንጂ መደበኛው ጦር መቀሌን ጥሎ ከወጣ በህዋላ የት እንዳለ እንኳን አይሰማም ነበር። በህዋላ በእግር በፈረሰ ተፈልገው ዳግመኛ ውጊያውን ተቀላቅለው የሆነውን ያው እየተጋነነም ቢሆን የሰማነው በመሆኑ እዚህ ላይ አይደገምም። ለዚህ ነው አሁን ግንባታ ግንባታ መልሶ ማቋቋም ሲባል መቅደም ያለበት የአካባቢው ሰላምና የወያኔን የድጋሚ ወረራ መከላከል የሚችል ሃይል መገንባት ነው የምንለው። ወያኔ ቂመኛ ነው። የልጅ ልጅ ፈልጎ ይገላል። አዎን በመቀሌ የሚያደርገው ግፍ ሰው መሆንን ያስጠላል። እናቶችን ሰውን እንደ እንጀራ አዋጡ እያሉ ይገኛሉ። እንዴ በፊት የተወሰድት ልጆቻችን የት አሉ ሲሏቸው “እነርሱ ተቆርጠው ቀርተው ስለተከበቡ እነርሱን ለማስፈታት ተጨማሪ ሃይል ያስፈልገናል” በማለት ለሶስተኛ ጊዜ የትግራይን ወጣቶች በማሰባሰብና ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛሉ። እንደ ጀርመኑ ሂትለር ከጥፋት ላይ ጥፋት እየቆለሉ ውድቀታቸው የማይታያቸው ጥቂት የአድዋ ተወላጆችና ተባባሪዎቻቸው ዛሬም እንደ ጥንቱ በትግራይ ህዝብ ስምና ደም መነገዳቸውን ቀጥለዋል። ወያኔ ተለቅሞ ጣና ሃይቅ ውስጥ መጣል ያለበት የአውሬ ስብስብ ነው። አንዳቸውም ስለ ትግራይ አይገዳቸውም። ያ ሆኖ ቢሆን ኑሮ ራሳቸው ለ 27 ዓመት በናጠጡባት ኢትዮጵያ በስልጣን ዘመናቸው ለትግራይ ህዝብ ብዙ ባደረጉ ነበር። ሌላው ቀርቶ የሚጠጣ ውሃ እንኳን ያላቀረበ ድርጅት ለትግራይ ህዝብ ነጻነት እየታገልኩ ነው ቢል ያመኑበትንና ራሱን ቂላ ቂል ያደርጋል እንጂ የጠራ ንቃተ ህሊና ላላቸው መቀለዳቸው እንደ ግንብ ጉልህ ሆኖ ከፊት ይታያል። ማን እየተሰዋ፤ ማን እየበላ እንደኖርን እኛ ጠንቅቀን እናውቃለን። ነጻ እናወጣሃለን የተባለው የትግራይ ህዝብ ዛሬም ኑሮው ከእጅ ወደ አፍ ነው። በስሙ የነገድት ግን ከነቤተሰቦቻቸው በውጭ ሃገር በዘረፉት ሃብት ዘንጠው ይኖራሉ። ያ ነው ለህዝብ መቆም? ድንቄም ነጻ አውጪ። ባርነት አፍላቂ እንጂ!
ወያኔ ከተፈጠረ ጀምሮ ሥራው ሁሉ ደም ማፍሰስ ነው። ለዚህም ጉዳይ እንዲረዳው ወያኔ 4 ነገሮችን ከልቡ አምሮ ይጠላል።
1. የአማራ ህዝብን – የችግርህ ሁሉ መሰረቱ የአማራ የበላይነት ነው። አማራን ማጥፋትና ማቆዝቆዝ የትግራይን ህዝብ ከፍታ ላይ ያደርሳል በሚል ሸውራራ ፈሊጥ እልፎችን አፈር ውስጥ ጨምሯል። አሁን ላይ ያደረገውንና የሚያደርገውንም ቆመን እያየን ነው።
2. የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ – ወያኔ ቤ/ክርስቲያኗን የሚጠላት በኢትዮጵያ ህዝቦችን ህብረትና አንድነት በማመኗ ነው። ለዚያም ነው ይህችን ቤ/ክ ከአማራው ህዝብ ጋር በማጣመር ሲከፋፍላት፤ ሲዘርፋት፤ የራሱ የሆኑ ካህናትና ጳጳስትን መስቀልና ሽጉጥ እያስያዘ ህዝብን ሲያሰልልና ሲገድል የኖረው። ስንቶች ባህታዊያን ናቸው የተገደሉት? ስንቶች ደብርና ገዳማት ናቸው የተዘረፉት? ቤቱ ይቁጥረው
3. ሻቢያ – ወያኔ የንስሃ አባቱን ሻቢያን አምሮ ይጠላል። ለምን ብሎ ለጠየቀ መልሱ አንድ ነው። ፕ/ኢሳይያስ መለስንና ሌሎችን ተው የጎሳ ፓለቲካ ለኢትዮጵያ አይጠቅምም በማለት ሲመክሯቸው የራሳቸውን የቀጥር ጥላ የማያምኑት ወያኔዎች ቶሎ ኤርትራ ተገንጥላ የምትወስደውን ወስዳ ከቁራሽ በተረፈችው ኢትዮጵያ ያለምንም ተጽኖ ሊፈነጩ ስለፈለጉ ሻቢያን ወዲያውኑ በዚህም በዚያም ከጎናቸው አባረው ኢትዮጵያን መገሽለጥ ጀመሩ። ሴራው የገባው ሻቢያም ክፋትን ያቃመሳቸው ራሱ ስለሆነ ጠንቅቆ ያውቃቸዋልና በሞኞች የባድሜ ፍትጊያ እልፍ ወገኖቻችን አሽዋ ላይ ቀሩ። ወያኔና ሻቢያ መካረር የጀመሩት ገና በረሃ እያሉም ነበር። ግን በሰፋ ሜዳ ላይና በሚዘረፍ ሃብት ላይ የከተማ አለቆች ሲሆኑ ሲሰርቁ ባልተጣሉበት ጉዳይ ሲከፋፈሉ ተፋጅ። ዛሬም ወደፊትም ወያኔ በትግራይ መሬት እስካለ ድረስ መፋለማቸው አይቀሬ ነው።
4. ኢትዮጵያንና አንድነቷን የሚያስቀድሙ የትግራይ ተወላጆች – ወያኔ እነዚህን የትግራይ ልጆች ከበረሃ ጀምሮ ሲመነጥራቸው ኖሯል፤ አሁንም እየገደላቸው ይገኛል። ሌላው ቀርቶ ከወያኔ ሃሳብና እይታ ውጭ ገበሬም ሆነ ምሁር ከተነፈሰ ከተገኘ ራሱ ካልተገኘ ዘመድ አዝማድ ዘብጥያ ይወርዳሉ ያለዚያም ታፍሰው በዚህና በዚያ ሰበብ ይገደላሉ። የሆነው እና በመሆን ላይ ያለው ይህ ነው። እነዚህን የሰፋ እይታ ያላቸውን የትግራይ ተወላጆች የፈጠራ ስም በመለጠፍ፤ የተዛባ ወሬ በመንዛት፤ የሚሰሩበት መ/ቤት ድረስ በመሄድ ግርግር በመፍጠር፤ ከእድርና ከሌሎች ህብረቶች በማስወጣት ጭንቅ ውስጥ ይከቷቸዋል። ወያኔ ማለት የጀርመኑ ጌስታፓ፤ የጣሊያኑ ፋሽሽት ነው የምለው በዚህና በሌሎች ጉዳዪች ነው።
ስለሆነም የሚስማር ጥይት በሰዎች ሰውነት ላይ ወያኔ መሰካቱ እንደ አቅሚቲ ነው እንጂ ወያኔ የመርዝ ጋዝ ቢያገኝ ይጠቀምበታል። ወያኔ የድሮን፤ የአየር ሃይል፤ ሌላም የሩቅና የቅርብ ተተኳሽና ደርማሽ ነገር እጅ ቢገባ አስመራና የአማራ ክልል አመድ እንደሚሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም። ወያኔ ህሊና የጎደለው ድርጅት ነው። ለዚያ ነው በአስመራና በአማራ ክልል ላይ የተውሶ ሮኬት ያዘነበው። ለወያኔ ማን ይሙት ማ ግድ አይሰጠውም። ቆም ብለን ልናስብ ይገባል ይህ ድርጅት ካልከሰመ በቀጠናው ሰላም አይኖርም። የነገን ባላውቅም አሁን ባለኝ እይታ ሻቢያ እንዲህ ያለ ተንኳሽ ባህሪ አሁን አሁን አይታይበትም። የሃገሪቱ መሪም የውጭውን ሴራ ጠንቅቀው ስለተረድ ልክ እንደ ጉርምስና ዘመናቸው በዙሪያቸው ያሉትን በጡጫ የሚነርቱ አይሆኑም። ሁሉን በእርጋታና በማስተዋል ለማራመድ እየሞከሩ እንደሆነ የሚያመላኩት ነገሮች አሉ። ሰላም የሰው ልጆች መሰረታዊ መብት ነው። ግን የሚበጠብጥ እያለ ማን ጥሩ ይጠጣል? በእኔ እምነት አሁን ባለችው የሃበሻ ምድር ሁለት በጥባጮች አሉ። ወያኔና የወያኔ ተላላኪዎች። ዝግጅት፤ መንቃት፤ መደራጀት፤ መታጠቅና መሰልጠን፤ ዛሬም ሆነ ወደፊትም ለሚደርስ ያልታሰበ ወረራን ለመፋለም አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው። በቃኝ!